“አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊከሰት ለሚችል የከፋ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው” – ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ********************** አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊከሰት ለሚችል የከፋ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አሳሰቡ። የዓለም ጤና ድርጅት በ33 የአፍሪካ አገራት ውስጥ 633 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸውንና እስካሁን 17 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አድርጓል። ቫይረሱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ …
Read More »Amharic
ቻይናዉያን ከኢትዮጵያ አንወጣም አሉ !
188 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል!
ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱ ከተነገረ በሗላ በአዲስ አበባ ከተማ በጤና መጠበቂያ ቁሶች እንዲሁም በግብርና ምርቶች ላይ ያለአግባብ ዋጋ ጨምረው የተገኙ 188 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል። አንዳንድ ፋርማሲዎች 5 ብር የነበረውን የአፍ መከላከያ እስከ 200 መቶ ብር፣ ነጭ ሽንኩርት ከ100 – 110 ብር የነበረውን ከ250 – 290 ብር፣ ሙዝ በኪሎ 25 ብር የነበረውን 60 ብር፣ በርበሬ 90 ብር የነበረውን …
Read More »ዓባይ በካይሮ ከተማ እንዲህ ተንጣሎ ይታያል ! ፎቶዉን ተመልከቱና ፍረዱ።
የኢትዮጵያና የግብፅ የቃላት ጦርነት በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ 11 March 2020 ብሩክ አብዱ የግብፅ መንግሥት የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግድቡ ወደ ግብፅ የሚፈሰውን የውኃ መጠን በመቀነስ፣ የታችኞቹ የተፋሰስ አገሮች ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያሳድራል ስትል በተደጋጋሚ አቤቱታ ያሰማል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም የሚቀርቡበት ትችቶች በጥናት የተመለሱ፣ ሁሉንም በሚያግባባ መንገድ ግኝቶቹ መሰራጨታቸውን በመጥቀስ ሲያጣጥል ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ …
Read More »የድያስፖራ ባንክ ሊከፈት ነው
አቶ ጋሻው የትዋለ ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ ኔዘርላንድስ ከሚገኘው ማስትሪች ስኩል ኦፍ ማኔጅመንት በፕሮጀክት አፕሬዛል፣ እንዲሁም ማኔጅመንት ዲፕሎማ፣ አውስትራሊያ ከሚገኘው የካንቤራ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ የታክስ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ በኮርፖሬት ቢዝነስ ስትራቴጂ፣ በፕሮጀክት ፕላኒንግና ማኔጅመንት በርካታ ሥልጠናዎች ተከታትለዋል፡፡ በኢንግሊዝ፣ በኔዘርላንድስና በቤልጂየም፣ እንዲሁም በአፍሪካ በኡጋንዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያና በታንዛኒያ የተከታተሏቸው የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን ይናገራሉ፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችንና የኮርፖሬት ቢዝነስ ስትራቴጂዎችን በዋናነት የንግድ፣ የታክስ፣ የፋይናንስ፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ የዳበረ ልምድ አላቸው፡፡ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ክልሎችን በመወከል፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የጥናትና የባለሙያዎች ቡድን ጋር በቅርበት በመሥራት፣ የአገሪቱን የታክስና የፋይናንስ ጉዳዮች ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት አንፃር በማጥናትና በመገምገም የፖሊሲ ሐሳቦችንና ስትራቴጂዎች ላይ የዳበረ ልምድ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያን የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ፕሮጀክት በማዘጋጀትና ፕሮግራሙን በመምራት፣ እንዲሁም እንዲተገበር በማስተባበር ተሳትፈዋል፡፡ በአጠቃላይ ከ27 ዓመታት በላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችንና የኮርፖሬት ስትራቴጂዎችን ከማመንጨት ልምዳቸው በመነሳት፣ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ከሐሳብ ጀምሮ አሁን እስከሚገኝበት ደረጃ ድረስ በአደራጅነትና በመሥራችነት የሚሳተፉት አቶ ጋሻው፣ የሚመሠረተው የዳያስፖራ ባንክ ዓላማዎቹንና የወደፊት እንቅስቃሴዎቹን በተመለከተ ብርሃኑ ፈቃደ አነጋግሯቸው የሚከተለውን አጠናቅሯል፡፡ ሪፖርተር፡– የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ? አቶ ጋሻው፡– ከማክሮ ኢኮኖሚ የዕድገትና ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አንፃር ፈጣን፣ ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት በማምጣት የአገሪቱን የመካከለኛ ገቢ ራዕይ እ.ኤ.አ. በ2025 ዕውን ለማድረግ ሲታሰብ፣ በአንድ በኩል የአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ እየጨመረ መምጣቱ በሌላ በኩል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክን ለማቋቋም እንደ ዋና ገፊ ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በመንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያም የማክሮ ኢኮኖሚው ቁልፍ ችግር የውጭ ምንዛሪ እጥረት መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾችን በተመለከተ የፊስካል ፖሊሲውና የሞኒተሪ ፖሊሲው መስተጋብር የተጣጣመ አለመሆን ዋናው ቁልፍ ችግር ሲሆን፣ በዚህ ረገድ በተለይ የወለድ ምጣኔ፣ የዋጋ ግሽበት ምጣኔ፣ የቁጠባ ምጣኔ፣ የታክስ ምጣኔ፣ የኢንቨስትመንት ምጣኔ፣ የጉልበትና የገበያ ዋጋ ምጣኔና የጥቁር ገበያ ምጣኔ፣ የተጣጣመና የተመጣጣነ አለመሆን ነው፡፡ በአጠቃላይ የምርት ፍላጎትና አቅርቦት፣ የገንዘብ አቅርቦትና ፍላጎት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና ፍላጎት የተጣጣመና የተመጣጣነ አለመሆን የማክሮ ኢኮኖሚው ቁልፍ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም የአገሪቱን የኢኮኖሚ ምኅዳርና የውጭ ምንዛሪ ቋት ለማስፋት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ማቋቋም አስፈልጓል፡፡ በሌላ በኩል አንዱ ቁልፍ ችግር የድህነት ጉዳይ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ ዝቅተኛ ገቢ ዝቅተኛ ቁጠባ፣ ዝቅተኛ ቁጠባ ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት፣ ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት ዝቅተኛ ገቢ የሆነውን የድህነት አዙሪት አከርካሪውን ለመስበር መሠረተ ሰፊ የሆኑ አዋጭ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ፋይናንስ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ለመጨመር፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ለማቋቋም አስፈልጓል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የዓለም ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር፣ ከኢንዱስትሪ መር ወደ አገልግሎት ዘርፍ መር፣ አገልግሎት ዘርፍ መር ወደ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መር፣ ከቴክኖሎጂ ዘርፍ መር ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ መር በፍጥነት በመሸጋገር ሒደት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የጀመረችውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የለውጥ ጉዞ ወደፊት ማራመድ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የብልፅግና ጉዞን ወደፊት ለማራምድና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አብዮት በማቀጣጠል ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግር በፍጥነት ለማምጣት የትውልደ ኢትዮጵያውያውን ዳያስፖራዎች የልማት ተሳትፎ በባንኩ ምሥረታ ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑ ከዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር፣ በተለይም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በሒደት ላይ የምትገኝ ስለሆነ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የማክሮ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ዘርፉን ደረጃ በደረጃ ለነፃ ገበያው በሯን ክፍት በማድረግ፣ ተጠቃሚነቷን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ባንኩን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ለባንክ ኢንዱስትሪያችን የቴክኖሎጂ ፍላጎት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም የደረሰችበትን ከፍተኛ የባንክ ኢንዱስትሪ የቴክኖሎጂ ደረጃ በመተግበር የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ የባንክ ኢንዱስትሪውን የፈጠራና የሙያ ብቃት ጥራት ፍላጎት፣ የባንክ ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሙያ ብቃትና ጥራት የሚፈልግ ከመሆኑ አንፃር ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ ቅን ታማኝና ተጠያቂ አመራሮችና ባለሙያዎች በማደራጀትና በማሰማራት፣ አዲስ ባንክ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ስፔሻላይዜሽንና ዳይቨርሲፊኬሽን (ብዝኃነት) በማስፈለጉ ከከፍተኛና መሠረተ ሰፊ በሆኑ ውስን የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባንክ ማቋቋም በማስፈለጉ ነው፡፡ ከፍተኛ የውጭ ምንዘሪ ፍላጎት ያላቸውን ግዙፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች ፋይናንስ ማድረግ በማስፈለጉ፣ በዚህ ረገድ ግዙፍና መሠረተ ሰፊ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ማለትም የህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ የሳይበር ቴክኖሎጂ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ፣ የሕክምና ኢንዱስትሪ፣ የኃይል ኢንዱስትሪ፣ የፊልም ኢንዱስትሪ፣ የግብርና ኢንዱስትሪና የምሥራቅ አፍሪካ የመሠረተ ልማትን ፋይናንስ ለማድረግ ነው፡፡ ሪፖርተር፡– የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ ከሌላው መደበኛ ባንክ በምን ይለያል? አቶ ጋሻው፡– የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ ከስያሜው ጀምሮ ዳያስፖራውን የሚመለከት ሲሆን፣ ከ70 በመቶ በላይ ዳያስፖራው ላይ አተኩሮ የሚሠራ ይሆናል፡፡ ባንኩ ለዳያስፖራው የአገሩ የኢኮኖሚ ልማት ዓርማ ወይም ምልክት በመሆን፣ ዳያስፖራው በአገሩ ዕድገትና ልማት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ አገሪቱ ከድህነት ቀለበት ለመውጣት የምታደረገውን እልህ አስጨራሽ መራራ ትግል አከርካሪውን ለመስበር በሚደረገው ጉዞ ዘመን ተሸጋሪ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ጥናቶች ኢንደሚያመለክቱት አገሮች እንደ ራሳቸው የመንግሥት አወቃቀርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ኢኮኖሚያቸውን ጥቃቅን፣ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ በማለት ይከፋፍላሉ፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክን ለመመሥረት አራት አማራጮች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው አማራጭ ከጥቃቅን ጀምሮ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ማካተት፣ …
Read More »