Breaking News
Home / Amharic / የደህዴን (የደቡብ ህዝቦች ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) መግለጫ::

የደህዴን (የደቡብ ህዝቦች ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) መግለጫ::

#የደህዴን (የደቡብ ህዝቦች ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) መግለጫ ።
#Ethiopia : አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲናና አለም አቀፍ ግዙፍ ተቋማት ማዕከል መሆኗን ያነሳው መድረኩ፥ አዲስ አበባ የመላ ኢትዮጵያውያን ብሎም የነዋሪዎቿ መሆኗንም አውስቷል፤ ሌሎች ጉዳዮች ህገ-መንግስቱንና ህጉን ተከትለው የሚፈጸሙ መሆኑን በመጥቀስ። ስለሆነም በአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ በህገ-መንግስቱ ጭብጦች ላይ በመመስረት ትግል ማድረግ እንደሚገባ፤ በምንም መንገድ በዚህ ሰአት የጭቅጭቅ የንትርክና የጥል አጀንዳ ሊሆን የሚችልበት ምከንያት እንደሌለው ስለሆነም በነዋሪው ዘንድ ጥርጣሬን እየፈጠሩ ያሉ ውዥንብሮችን የሚችሉ ጉዳዮችን እውነቱን በማስረዳትና የተሳሳተውን አስተሳሰብ በማረም ረገድ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ ከግዝያዊ ስሜት ቀስቃሽና የሃሰት ውዥንብሮች በፀዳ መንገድ አሁን በሀገሪቱ ብሎም በአዲስ አበባ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በአግባቡ ወደሚቀጥለው የዕድገትና ብልጽግና መስመር እንዲገባ፥ በጥንቃቄ መጠበቅና ማስቀጠል የህዝቦች የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳት በትክክለኛ መንገድ የመምራት እና ሀገርና ወገንን የማዳን ሀላፊነትና ግዴታ እንዳለበት አስታውሷል።
ከዚህ አኳያ ደኢህዴን ከሌሎች ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር የአላማ አንድነቱን በማጠናከር የከተማውን ሰላም ልማት ለማፋጠን እና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ኢትዮጵያዊ አንድነት ይበልጥ በሚያጠናክር መልኩ ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፤የተለያዪ ሚድያ አውታሮች የማህበራዊ ሚድያ አክቲቪስቶችን ጨምሮ የከተማውን ሰላም ፤ልማትና ብልፅግና የሚያጎለብቱ እንጂ አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዳዮችን ማስወገድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.