Breaking News
Home / News / ጠቅላይ ሚንስትሩ በምርጫ ዙሪያ ነገ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ይወያያሉ

ጠቅላይ ሚንስትሩ በምርጫ ዙሪያ ነገ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ይወያያሉ

የኮሮና ወረርሽኝ በቀጣዩ ምርጫ ዝግጅትና አፈጻጸም ላይ ባስከተለው ጫናና በመፍትሔዎቹ ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ዋዜማ አረጋግጣለች።

ውይይቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አገራዊና ክልላዊ ምርጫው አስቀድሞ በተያዘለት መርሐ ግብር ሊፈጸም እንደማይችል መወሰኑን ተከትሎ የሚነሡትን አንኳር ጥያቄዎች እንደሚዳስስ ይጠበቃል።

ተወያዮቹ ቀጣዩ ምርጫ ሊካሄድባቸው የሚችሉትን መጻኢ ሁኔታዎች፣ እንዲሁም ከምርጫው መራዘም ጋራ ተያይዞ ሕገ መንግሥቱ ግልጽ ምላሽ የማይሰጥባቸውን ሁኔታዎች በጋራ መግባባት መመለስ የሚቻልበትን ሁኔታ እንዲነጋገሩ እቅድ ተይዟል።

ሆኖም ይህ ውይይት ቀጣይነት እንዲኖረው ስለመታሰቡ ልናረጋግጥ አልቻልንም። ምንጮቻችን የነገው ስብሰባ የውይይቱን ቀጣይነት ሊወስን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። [ዋዜማ ራዲዮ]

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.