Breaking News
Home / Amharic / Time Bomb በአንቀፆቹ ውስጥ የቀበረ ህገመንግስት ይሄን ያክል ቀን መነታረክ ራሱ አስገራሚ ነው። Apartheid Laws.

Time Bomb በአንቀፆቹ ውስጥ የቀበረ ህገመንግስት ይሄን ያክል ቀን መነታረክ ራሱ አስገራሚ ነው። Apartheid Laws.

Veronika Melaku

አማራ ያልተወከለበት ህገመንግስት !

በዚህ የተፃፈበትን ቀለምና ወረቀት እንኳን ያህል ዋጋ ለሌለውና ለሚሊዮኖች መፈናቀልና ለሺህዎች ሞት ምክንያት ለሆነ ተራና Time Bomb በአንቀፆቹ ውስጥ የቀበረ ህገመንግስት ይሄን ያክል ቀን መነታረክ ራሱ አስገራሚ ነው። 85 በመቶው ህዝቧ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ህዝብ እያላት ለየአንዳንዱ የካቢኔ አባሏ የ200 ሺህ ብር ስማርት ፎንና ታብሌት የምትገዛ አገር በእውኑ ታስገርማለች።
የሳምሰንግ ኩባንያ ዓመታዊ ገቢ ከ173 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል። ዛሬ የኢትዮጵያን ዓመታዊ የኤክስፖርት ገቢ ስንመለከተው 3 ቢሊዮን ዶላር እንኳን መድረስ አልቻለም። ኢትዮጵያን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ማነፃፀር ይቅርና ኢትዮጵያን ከአንዱ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ጋር ማነፃፀር ራሱ የጥንቸልና የዝሆን ንፅፅር ያህል ሆኖ በሚታይበት አገር ስለኢኮኖሚ እድገት እርግፍ አድርገው ትተው ጭልፊቶችን ለማስመረጥ ላይ አገሪቱ ቢዚ ሆናለች።
ጭልፊት ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ፣ የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል፡፡
አሁንም መፍትሄው ካለምንም ንትርክ ምርጫውን አራዝሞ ህገመንግስቱን መቀየር ነው።
አፄ ኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግሥታቸውን ሦስት ጊዜ አሻሽለዋል፡፡ የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 27 ጊዜ፣ የህንድ 122 ጊዜ፣ የስዊስ 80 ጊዜ፣ የጀርመን 50 ጊዜ ተሻሽለዋል፡፡ በፌዴራል አስተዳደር የሚስተዳደሩ አገሮች የፌዴራል አስተዳደር ሕጎቻቸውን ያሻሻሉበትን ጊዜ መቁጠር ያታክታል፡፡ ብልፅግና ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ ሕገ መንግሥቱንና የፌዴራል አስተዳደር ሕጎቹን ለማሻሻል የሚቸገርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ይሄን ተራና መርዛማ ህገመንግስት ቀይሮ የአገሪቱን ችግር ለአንድየና ለመጨረሻ ጊዜ መቋጨቱ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው::

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.