Breaking News
Home / Amharic / የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ!

ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኞ እለት (የካቲት 11/2016) ምሽት ላይ ነበር። ስሟን የማልጠቅሳት ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ተጓዥ ማታ 5 ሰአት ወደ አሜሪካ ላለባት ጉዞ ቀደም ብላ 2 ሰአት ቦሌ ኤርፖርት ትደርሳለች።

በፍተሻው ወቅት “ሻንጣሽን ከፍተሽ አሳዪን፣ ማሽኑ የሆነ ነገር ያሳየናል” በማለት ሻንጣዎቿን አስከፈቱ። በዚህ ወቅት የያዘችውን የግል መገልገያ ጌጣጌጥ እና በህጋዊ መንገድ የያዘችውን ዶላር ይመለከታሉ። ቀጥላም ሁኔታውም ስታስረዳኝ እንዲህ ብላለች:

“እነዚህ ለብዙ አመታት ያደርግኳቸው ከቤተሰቦቼ እንዲሁም ከባለቤቴ የተሰጡኝ ጌጣጌጦች ናቸው። የሌላ ሀገር ዜግነት ላለው ዶላር እስከ 10,000 በህጋዊ መንገድ ይፈቀዳል፣ እኔ የያዝኩት ከዚህ በጣም ያነሰ ነበር። ጌጣጌጥ ደግሞ ማስመስገብ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር። ስለዚህ ፈታሿን ይቅርታ ከዚህ በሗላ አስመዘግባለሁ አልኳት፣ ከዛም በሊፍት አድርጋ ለብቻዬ የሆነ ቦታ ወሰደችኝ።”

“በዚህ ወቅት ሌሎች ሰራተኞች ‘በጥሺላት’ እና ‘በቃ ስጫት’ ይሉኝ ነበር። እኔም ግራ ገብቶኝ የእኔ መሆኑን ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ጌጣጌጡ የሚታይበት የድሮ ፎቶ ላሳያችሁ ብላቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም። ከዛም ተለቅ ወዳለች ሌላ ሴትዮ ጋር ወሰደችኝ። የሴትዮዋ መልስ ደግሞ ‘የሀገሪቱን ሁኔታ አታውቂም? ሀገሪቷ እኮ ወርቅ ያስፈልጋታል!’ ነበር።”

“በዚህ ሁሉ መሀል ይቺ ትልቅ ሴትዮ ተስማሚ፣ ካልሆነ በሙሉ ይወረሳል አለችኝ። ምን ማለት ነው ስላት በግልፅ ወርቁን አካፍዪ አለችኝ። በዚህ ወቅት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። እንደማይለቁኝ ስለገባኝ፣ ስልክ እንዳወራም ስለከለኩሉኝ ብዙ ትዝታዬ ያለበትን ጌጣጌጤን ከሚወስዱ ከእሱ ውጪ እንስማማ አልኳቸው።”

“ከዛም ወደ ቦርሳዬ እየጠቆመች ‘እሺ ዶላር ይዘሽ አይቻለሁ፣ እሱን አምጪ አለችኝ’። የያዝኩት ዶላር እና ብር ደግሞ የራሴንም፣ የዘመድ እና ጓደኛም ብዙ ትርፍ ሻንጣ ስለያዝኩ ለእሱ የምከፍለው ነው አልኩ። ክፈችው ብላ ትንሽ አስቀርታ የምትፈልገውን ወሰደች። ተባብረንሽ ነው የለቀቅንሽ ብለው ሂጂ አሉኝ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ የመጨረሻ ተሳፋሪ ሆኜ ወደ ጉዞዬ ቀጠልኩ።”

Note 1: ከበርካታ ወራት በፊት እንዲህ አይነት ኤርፖርት ላይ በፀጥታ እና ፍተሻ አካላት በተለይ ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ዝርፊያን መረጃ አቅርቤ ነበር። ይህ ተጨማሪ ማሳያ ነው።

Note 2: በኤርፖርት ያሉ እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲነሱ አንዳንዶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያያይዙታል፣ ነገር ግን የኤርፖርት ጥበቃ የሚከናወነው በአየር መንገዱ ሳይሆን በሌሎች የመንግት የደህንነት እና የፅጥታ አካላት ነው።

Photo: File

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

One comment

  1. ማን ሂዳለው በዚህ ግዜ..??? ገንዘቡን አጥቁሮ ሊዝናና ወይንም በዚህ ግዜ ኮንድሚንየም ለመግዛት ለሚሄደው ይበለው፣
    ምን አንገብጋቢ ነገር ኖሮ ማለፍ የማይቻል..???
    ለለቅሶ ወይንም ለሐዘን አማራ ክልል መሄድ የማይቻልበት ግዜ ነው!
    ታድያ…. ለሚሄደው ላዝን ነው..???
    ገንዘቡን ለፋኖ ቢያዋጣ ተግሉን ያፋጥነዋል፣ ሰለዚህ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዞች አሰቡበት ብዬ ምክሬን እሰጣለሁ።
    ኢ/ር መኳንንት

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.