Breaking News
Home / Amharic / በአዲስ አበባ ጉዳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) አቋም !

በአዲስ አበባ ጉዳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) አቋም !

አብን ስለ አዲስ አበባ መግለጫ አወጣ! በአዲስ አበባ ጉዳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) አቋም ስለመግለጽ
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አዲስ አበባን በተመለከተ ከዚህ በፊት አቋሙን ግልጽ አድርጎ እንደነበር ይታወቃል። የአዲስ አበባን ጉዳይ በታሪክ ማንፀሪያ ስንመለከታት የቀደምት ነዋሪዎቿ መሆኗ የሚካድ ኃቅ አይደለም። አዲስ አበባ ዛሬ የተፈጠረች፤ ድንገት እንደ ችግኝ የበቀለች ከተማ አይደለችም። አዲስ አበባ በረራ ሆና የአጼ ዳዊት ቀደምት ከተማ እንደነበረች የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ይሁን እንጂ አሁን ባለችበት ቁመና ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን ተሰባስበው፣ ተከባብረው፣ ተሳስበውና ኃብት ንብረት አፍርተው በጋራ የከተሙባት ከተማ ሆና ትገኛለች። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ «አዲስ አበባ የእኛ ናት» የሚሉ ተሥፋፊዎች ከተማይቱ የምትታወቅበትን የሁሉም ቤትነት መልካም ገጽታ ለመረበሽ ተቃርበዋል። ይህ አካሄድ ፍፁም ተገቢ ካለመሆኑ በተጨማሪ በሰላም ተረጋግቶ የሚኖረውን የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚያውክ በመሆኑ በአጭር ሊቀጭ የሚገባው አደገኛ አካሄድ ነው።

አዲስ አበባ እንደ ሌሎች በፌዴራሊዝም የሚተዳደሩ የዓለም ከተሞች ሁሉ ራሷን በራሷ በቀጥታ በሕዝብ በተመረጠ ከንቲባ ማስተዳደር ያለባት መሆኗን አብን ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ባላጸደቀው እና ይሁንታውን ባልሰጠው የጫካ ሰነድ (ሕገ መንግስት) ውስጥ የተሰነቀረውን የኦሮሚያ «ልዩ ጥቅም» የሚባል የአፓርታይድ ሕግ የማንቀበለው መሆኑን ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ ለዚህ ዘመን የማይመጥን የድንጋይ ዘመን ሕግ መሆኑንም መላው ሕዝባችን እንዲገነዘበው ለማሳወቅ እንወዳለን። ከዚሁ ጋር በተያያዘ «የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም» የሚባል አንዱን ለይቶ ጠቃሚና ሌላውን ባይተዋር የሚያደርግ መብትን የሰጠው የሕግ አንቀጽ የአገራችንን ሕዝቦች መስተጋብር የሚያናጋ ከመሆኑም በላይ የሕገ መንግሥት ማሻሻል አስገዳጅነትንም የሚጠቁም መሆኑን እናምናለን።

አብን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልመከረበት እና ይሁንታውን ያልሰጠው ሕገመንግሥት እንዲሻሻል አበክሮ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ይህን የአፓርታይድ ሕገመንግሥት ለማሻሻል በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችን ይቆም ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
ሚያዚያ 15/2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.