Breaking News
Home / Amharic / ታፍነው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች መፈታታቸው ተሰማ።

ታፍነው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች መፈታታቸው ተሰማ።

*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ትናንት መጋቢት 01/2011 ዓ/ም በጋዜጠኛና ሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ አዘጋጅነት የተጠራውን ስብሰባ ታድመው በሰላም ወደየቤታቸው ሲመለሱ በፖሊስ ተደብድበውና ታፍነው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ በጠዋት ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል። ወጣቶቹ መለቀቃቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። አብን የወጣቶቹ መለቀቅ ተገቢና ትክክል መሆኑን ያሰምርበታል። ለወደፊትም መንግስት በሰላማዊ ዜጎች ላይ መሰል አፈናና እስር ከማድረግ እንዲቆጠብ ይጠይቃል።

ወጣቶቹ ያነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎችንም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በውል በማጤን መፍትሔ እንዲያበጁላቸውም አብን ጨምሮ ያሳስባል። ንቅናቄያችን በትናንትናው ውይይት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ያነሷቸውን ጥያቄዎች በሙሉ ይደግፋል። ለማስታዎስ ያህል፦

1) የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ላይ ከሚያደርጓቸው ማናቸውም ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ፤

2) በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ ተንኳሽ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ፤

3) አዲስ አበባ በሕገወጥ ከንቲባና ካቢኔ መመራቷ ተገቢ ያለመሆኑን፤ እንዲሁም

4) የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ ሆነ ብሎ ለማዛባት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኩል የተደረገውን በመቶ ሺሆዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለፈቃዳቸው በማስገደድ በሕገወጥ መንገድ ማስፈር ወንጀል በመሆኑ ተገቢው እርምት እንዲደረግ፤

የሚሉ የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄዎች መፍትሔ እንዲሰጥባቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር በጽናት የሚታገል መሆኑን ደግመን እናሳውቃለን።

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.