Breaking News
Home / Amharic / የኦሮሞ መስፋፋት እየቀጠለ ነው:: በአዲስአበባ ቤቶች እየፈረሱ ነው !

የኦሮሞ መስፋፋት እየቀጠለ ነው:: በአዲስአበባ ቤቶች እየፈረሱ ነው !

የኦሮሚያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ተነሽ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ካሳ ወይም ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ቤታቸውን በሦስት ቀን ውስጥ እንዲያፈርሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂ ተሰጣቸው

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
አዲስ አበባ ፍላሚንጎ አካባቢ እስከ ግሪክ ትምህርት ቤት ድረስ ባለው አካባቢ ለሚገነባው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ቦታውን እንዲለቁ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መካከል 15 የግለሰብ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ የቀበሌ ቤቶችም ተነሽ ናቸው ተብሏል፡፡

ይህንን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የፃፈው የቂርቆስ ከፍል ከተማ ወረዳ 01 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሲሆን በተባለው ቀን የማይነሱ ከሆነ ለሚወሰደው እርምጃ ኃላፊነት እንደማይወስድ በደብዳቤው ጠቅሷል ፡፡
ነዋሪዎቹ ከ 8 ወራት በፊት የምትክ ቦታ እንደመረጡና እስከ አሁን ግን በጉዳዩ ላይ ምንም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ቤቱንም እንዳላገኙ ተናግረዋል ፡፡ ጽ/ቤቱ የካሳ ክፍያቸው በዝግ አካውንት እንደገባ የነገራቸው ቢሆንም ነዋሪዎቹ ግን ይህንን አካውንት እንደማውቁትና ለዚህም ምንም አይነት ፊርማቸውን እንዳልሰጡ ይናገራሉ ፡፡

ነዋሪዎቹ በመነሳታቸው ምንም ቅሬታ ባይኖራቸውም በዚህ ፍጥነትና የተባለው ምትክ ቦታም ሆነ ካሳ ሳሰጣቸው ወዴትም መሄድ እንደማይችሉ መናገራቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል ፡፡

ጉዳዩን የሚመለከተው ቂ/ቆ ክፍለከተማ ቢጠየቅም በዚህ ጉዳይ መልስ የሚሰጠው የኦ/ክ/ፕ/ጽ/ቤት ነው በማለት መልስ ሳይሰጥ ቢቀርም በተመሳሳይ የክልሉ ጽ/ቤትም ለቀረበለት ጥያቄ ምንም ምላሽ እንዳልሰጠ ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል ፡፡

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.