ሰበር ዜና —– ታከለ ኡማና እስክንድር ነጋ ተገናኙ —— ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዲፈቀዱ ተስማሙ ——- በዛሬው ዕለት፣ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት፣ እንደመነሻ ሃሳብ ሆኖ፣ በአዲስ አበባ ጉዳይ ልዩነቶች እንዳሉ፣ ልዩነቶች ግን በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው ተስማምተዋል፡፡ በቀጣይነትም፣ ወደዋናው አጀንዳ …
Read More »News
ዖሮሞ ያልሆኑ ሰዎች በኦሮሞ ሲፈናቀሉ ተመልከቱ። ኣቢይና ለማ ይህን እያዩ ትንፍሽ አይሉም!
https://www.facebook.com/Adugenetee/videos/440297196515587/
Read More »ለውጭ ምንዛሪ ክምችት ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ::
ለውጭ ምንዛሪ ክምችት የተለየ መፍትሔ ካልተገኘ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር ሌላ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ 31 March 2019 ዮሐንስ አንበርብር የልማት ባንክ የማይመለስና አጠራጣሪ ብድር 18.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል በሦስት ወራት 344 ሚሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል በቀጣዮቹ ወራት በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ካልተገኘ በስተቀር፣ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በዘለለ የኢኮኖሚውን ፍላጎት ማስተናገድ እንደማይቻልየብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ መጋቢት19 ቀን 2011 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት። የባንኩ ገዥ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ለውጭ ገበያ ከምታቀርባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ1.64 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አመልክተዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በ2010 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው መጠን ጋር ሲነፃፀር በ9.4 በመቶ ያነሰ እንደሆነገልጸዋል። ከግለሰቦችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተላከ የሐዋላ ገቢ በአጠቃላይ 3.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ አስረድተዋል። በተቃራኒው ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸው ምርቶች 10.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉን፣ ይህም ወጪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.3 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጣው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ለነዳጅ ግዥ የተከፈለው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ አስታውቀዋል። በተጠቀሱት ወራት ወደ አገር ለገቡ ሸቀጦች የተከፈለው የውጭ ምንዛሪና ወደ ውጭ ከተላኩ ሸቀጦች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መሀል የ8.9 ቢሊዮን ዶላርየንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሚታይ የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ የተገለጸው ጉድለት የተሸፈነው ከአገልግሎት (በዋናነት ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት)፣ከውጭ በሐዋላ ከተላከ ገቢና ከውጭ ከተገኘ ዕርዳታና ብድር መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት የ2.6 ወራት ፍላጎትን ለመሸፈን ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ገልጸዋል። የንግድ ማኅበረሰቡ የውጭ ምንዛሪ በተመለከተ የሚያቀርበውን እሮሮ በመጥቀስ የምክር ቤቱ አባላት ስለመፍትሔው ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን፣ የባንኩ ገዥበሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ያለው የውጭ ምንዛሪ መጠን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስና የግሉን ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ የሚችልበትሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ እየዋለ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከተለያዩ አገሮች ጋር ተነጋግረው ማምጣት የቻሉት2.7 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥረት እንደተገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመሳሳይ ጥረት ተደርጎ በቀጣዮቹ ወራት ተመሳሳይ ሀብትካልተገኘ ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ እንደማይቻል ገልጸዋል። “ይህ ካልሆነ ልናደርግ የምንችለው ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለነዳጅና ለመድኃኒት ግዥ ብቻ በጥንቃቄ ማዋል ነው፤” ብለዋል። ከዚህ በመለስ ኢኮኖሚውንለማንቀሳቀስ የአምስትና የአሥር ዓመታት ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ አስረድተዋል። በተመሳሳይ ቀን ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ መንበረ ሥልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አረንቋ ውስጥ ወድቆእንደገጠማቸው ገልጸዋል። ኃላፊነቱን በተቀበሉ በሳምንቱ የቀረበላቸው የ20 ቢሊዮን ብር የደመወዝ ጥያቄ እንደነበርና ይህንን የአገሪቱ አቅም መመለስ እንዳልቻለ፣ በርካታ ሜጋፕሮጀክቶች ግንባታቸው ቆሞ አገሪቱን ለተጨማሪ የሀብት ብክነት ሰለባ አድርገዋት እንደነበር አስታውሰዋል። ችግሩን ለማስተካካል ባከናወኗቸው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ተግባራት ኢንቨስትመንትንና ትንንሽ ብድሮችን ሳይጨምር ሦስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀብትማግኘት እንደቻሉ፣ አገሪቱ የተበደረቻቸውን ግዙፍ የውጭ ብድሮች ክፍያ መፈጸም ባለመቻሏ ሊፈጠር የሚችለውን ቀውስ ቀድሞ ለመከላከል ከቻይናመንግሥት ጋር ባደረጉት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ፣ መከፈል የተጀመረው ከ400 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ ብድር የመክፈያ ጊዜ በሰፊ ርቀት እንዲራዘምመቻሉን መግለጻቸው ይታወሳል። የብሔራዊ ባንኩ ገዥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ያነሱት ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገባበትን አጣብቂኝ የተመለከተነበር። በተሰጠው ተልዕኮና ተግባራቱ ምክንያት ባለሙያዎች የፖሊሲ ባንክ በማለት የሚገልጹትና ከመቶ ዓመታት በላይ የአገልግሎት ቆይታው የሚታወቀው ልማትባንክ፣ በኪሳራ ውስጥ መውደቁንና በፍጥነት መታደግ ካልተቻለ ህልውናውን ሊያጣ እንደሚችል ይናገር (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ገዥው እንደገለጹት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2011 በጀት ዓመት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ፣ አጠቃላይ የብድር ክምችቱ 46.17 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል። ከዚህ ውስጥም የማይመለስና አጠራጣሪ ብድሩ የአጠቃላይ ብድሩን 39.45 በመቶ እንደደረሰ ይፋ አድርገዋል። ይህም ማለት ልማት ባንክ ካበደረውአጠቃላይ ብድር ወስጥ 18.1 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ሊመለስ የማይችልና መመለሱ አጠራጣሪ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ባንኩ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ውስጥ 344 ሚሊዮን ብር እንደከሰረ፣ ለምክር ቤቱ አስታውቀዋል፡፡ የማይመለስና መመለሱ አጠራጣሪ ከሆነው የባንኩ ብድር ውስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው ለሰፋፊ እርሻዎች የተሰጠው ብድር እንደሆነ የተናገሩት ገዥው፣አብዛኞቹ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ ለሌላ ዓላማ እንዳዋሉትና የእርሻ መሬቱ በሚገኝበት አካባቢ የጥበቃ ቤት እንኳን ያልገነቡ መኖራቸውን ገልጸዋል። ተበዳሪዎቹን ተከታትሎ ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ የገለጹት ይናገር (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሁን ባለው ቁመና ብድሮቹን የማስመለስም ሆነበኢኮኖሚው ውስጥ የተሰጠውን ተልዕኮ የመወጣት አቅም እንደሌለው ተናግረዋል። በመሆኑም ባንኩን አፍርሶ እንደገና መሥራት እንደሚያስፈልግ፣ ይህ ካልሆነ ግን በራሱ ጊዜ በቅርቡ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። …
Read More »ግንቦት 20 በመጋቢት 24 ተተክቶላችኋል::
From: Agegnehu Kassa ግንቦት 20 በመጋቢት 24 ተተክቶላችኋል ። እኛ አማሮች ከአጋሮቻችን ጋር ይህን የዘር ፓለቲካ በፅኑ እንዋጋለን ። መዳረሻችንም አብን ነው ። Why አብን ??? **አብን የሚያምንበትና ለመታገል የሚንቀሳቀሰው አማራን አዳክሞ ኢትዮጵያን ለመበተን ከሚታገል የመለስና መለስ ወለድ የኦሮሞ ተስፋፊ ሜንጫዎችና ደጋፊዎቻቸው ጋር መሆኑ = (by the way እን ማዴቦ ፡ ቦንገርና ቀርሴሞ ፡ ባሸራቃጭነትና ባንዳነት እዚህ ቡድን ውስጥ ይጠቃለሉ) …
Read More »