Breaking News
Home / Amharic / የኦሮሙማ መንግስት አማራ ክልል በወታደራዊ አስተዳደር እንዲመራ ወሰነ

የኦሮሙማ መንግስት አማራ ክልል በወታደራዊ አስተዳደር እንዲመራ ወሰነ

አገዛዙ የመጨረሻ ትዛዙን በአማራ ህዝብ ላይ ሰጠ።

” የአማራ ክልል መንግስትን ወይም አጋር ወዳጁ ብአዴን በወታደራዊ አስተዳደር የመቀየር ወይም መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ዝግጅት አብይ አጠናቀቀ” እርስ በራሳቸው የመፈነቃቀል ወይም የመዋዋጥ እንቅስቃሴ መጀመሩ አይቀሬነቱን የሚያሳይ ዝግጅት በግልፅ እየታየ መጥቷል።

የኦሮሞ ብልፅግና የሚመራው አገዛዝ አማራ ክልሉን በወታደራዊ አገዛዝ ለመተካት አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል ፣ ብአዴን ወደ ግምጃቤት ይቀመጣል። የልፍኝ አስከልካዮች ከወራሪው ኦሮሙማ ጋር በመሆን መንገድ ይመራሉ። የአማራን ህዝብ በቁጥጥር ስር አውሎ የሚጨፈጭፉትን ጨፍጭፈው የቀረውን ረግጠው ለመግዛት ወስነዋል። በእቅዳቸው መሰረት ፣

1፦ ጀኔራል አበባው ታደሰ በዋና አዛዥነት የሚመራው ቡድን ሙሉ ስልጠና በመውሰድ በባህርዳር ከተማ መኮድ ማዘዣ ቢሮውን አድርጎ ከትሟል ፣

2፦ የአማራ ክልል መንግስትን በማስወገድ የመሪነቱን ስራ የሚሰሩ በአበባው ታደሰ ስር 78 (ሰባ ስምንት ) ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተገቢውን የአስተዳደር ስልጠና በመውሰድ ባህርዳር ከተማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም ገብተው በተዘጋጀላቸው ቦታ አርፈዋል ፣

3፦ ለጊዜው የተዘጋጀላቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

– 2:1፦ ሶሊያና ሆቴል ባህርዳር ቀበሌ 14 ፣
– 2:2፦ አባይ ሆቴል ባህርዳር ቀበሌ 04 ፣
– 2:3፦ ተፈሪ መኮነን ሆቴል ባህርዳር ቀበሌ 04 ፣
– 2:4፦ ታደሰ ፔኒሲዮን ባህርዳር ቀበሌ 04 ፣
– 2:5 ፦ ደራ ሆቴል ባህርዳር ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው በግ ተራ እየተባለ የሚጠራው ከሚገኘው ነው ያረፋት ።

3፦ ከጀኔራል አበባው ጋር አብረው በአብይ አህመድ የተመደቡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ዶ/ር ጌታቸው ጀንበሬ እና ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ሲሆኑ ለዚህ ቡድን አስፈላጊውን ነገሮች እያሟሉ ይገኛሉ ።

4፦ የክልሉ አመራር ማለትም በክልል ፣ በዞን ፣ በከተማ ፣ በወረዳ የሚገኙት አመራር አወያይቶ ቀደም ሲል በተገኘው ግብአት ከፋኖ ጋር አንድ ሁኖ በመገኘቱ እና አሁንም የመጨረሻው ስራ ላይ በታሰበው ኦፕሪሽን በተቃራኒው በመቆም ከፋኖ ጋር አንድ ሁነው ከተገኙ የክልሉን መዋቅር ዳይሜጂ አርጎ በወታደራዊ አስተዳደር መተካትና ፋኖን ማጥፋት ነው ዛሬ ሌሊቱን ሀይል ሲያስገቡ አድረዋል ።

5፦ መከላከያ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ስምሪት መስጫና ማዘዣ ካምፕ ከሚሴ አድርጓል።

ሌሎቹ አካባቢዎች ለመከላከያ ደጀን መሆን የሚችል ህዝብ የለም ተብሏል። ይህ ተግባር ደግሞ መከላከያን በአማራ ህዝብ ጭራሽ ጠላት መሆኑን ያረጋግጣል በማለት ህዝቡ ከመከላከያ ተቃራኒ እንደቆመ ይገኛል ።

በተመሳሳይ በጎንደርም የመከላከያ ማዘዣ ጭልጋ እና ላይ አርማጭሆ ትክልድንጋይ የተመረጡ ሲሆን በጎጃም አዊ ዞን እየተጠና ይገኛል ።

የአማራ ህዝብ እንደ አማራ በተመሳሳይ ቀን ተመሳሳይ የህዝባዊ እንቢተኝነት መጀመር ፣ መንገዶችን በየትኛውም ቦታ መዝጋት፣ ለወረራ በተሰማራው ሰራዊት ላይ በመላው አማራ የተናበበ እርምጃ መውሰድ፣ ለወረራ ለተሰማራው ሰራዊት ምንም አይነት ነገር ከህዝብ እንዳያገኝ ማድረግ።

አማራ የሞት ሽረት ትግል በየትኛውም አቅጣጫ ፣ በየትኛውም ቦታ እንቅስቃሴ ማድረግ ታሪካዊ ግዴታው ነው።

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.