Breaking News
Home / Amharic / የምስራች ለመላዉ የዐማራ ማኅበረሰብ !

የምስራች ለመላዉ የዐማራ ማኅበረሰብ !

የምስራች ለመላዉ የዐማራ ማኅበረሰብ

በአዉሮፓ የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት በአማራዉ ትግል ላይ በተናጠል ስናደርግ የነበረውን ያልተቀናጀና የተበታተነ እንቅሳቃሴ ዉጤቱን በመገምገምና በአማራዉ ላይ የተጋረጠዉን የህልዉና
አደጋ ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት አንድ የጋራ ተልዕኮ ያለዉና በተማከለ ደረጃ የሚመራ ሁለንተናዊና የማያቋርጥ ትግል ለማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት እንደሚያስፈልግ በመረዳት ለወራት ስንመክርና
ስንዘጋጅ ቆይተን እነሆ በአውሮፓ የዐማራ ማኅበራት ፌዴሬሽንን በማዋቀር በነሐሴ 5 ቀን 2023 ዕለተ ቅዳሜ የመስራች ጉባዔዉን ያካሂዳል። በመሆኑም በመላዉ አዉሮፓ የምትገኙ የዐማራ ልጆች
በምትኖሩበት አገር በሚገኙ የፌደሬሽኑ የዐማራ ማኅበራት ስር በአባልነት በመታቀፍ የዐማራዉን ህልዉና ለማስቀጠል የተጀመረዉን ተጨባጭ ትግል በመደገፍ የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

የተጋረጠብንን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስ በዐማራነት ተደራጅቶ ከመታገል ዉጭ አማራጭ የለንም!

ህልዉናችን በትግላችን!
በአዉሮፓ የዐማራ ማኅበራት ፌደሬሽን

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.