Breaking News
Home / Amharic / ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች÷የቀይ ባህር ተጋሪ ሃገር ሆንን” ወዘተ የሚሉ ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎች !

ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች÷የቀይ ባህር ተጋሪ ሃገር ሆንን” ወዘተ የሚሉ ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎች !

አሁናዊ መረጃ:-

የኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ዘዴዎች በሰበር ዜና “ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች÷የቀይ ባህር ተጋሪ ሃገር ሆንን” ወዘተ የሚሉ ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን በማሰራጨት የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ እንዲሁም ለመውደቅ አንድ ሃሙስ የቀረውን የጦር ወንጀለኛና ፋሺስቱን ዓብይ አህመድ ስልጣን ለማዳን ሲጋጋጡ ታይተው መቀላመድን ከአለቃቸው ባህሪ የወረሱት መሆኑ ብዙዎችን ሲያስገርም ውሏል:: በመሰረቱ ስምምነቱ ከ5 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲነገር የቆየና ይህም በመንግስት መገናኛ ዘዴዎች ጭምር 19 በመቶ የበርበራን ወደብ አልምቶ ለመጠቀም ስምምነት ተደረገ በሚል ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው:: የሶማሌ ላንዱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙሴ ቢሂ ከስምምነቱ በኋላ በግልጽ እንዳጋለጡት የዛሬው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት “ኢትዮጵያ ለባህር ኃይል ሰራዊቷ ማስፈሪያ የሚሆን 20 ኪሎ ሜትር የውሃ ክልል ከሶማሌ ላንድ በሊዝ ለ 50 ዓመታት ለመከራየት ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት የተፈጸመ ሲሆን ስምምነቱ ነጻ ሳይሆን በሊዝ ኪራይ የተከናወነ መሆኑን በተጨማሪም በአንጻሩ ኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዕውቅና ላልተሰጣት ሱማሌ ላንድ ሃገር መሆኗን ዕውቅና እንድትሰጣት /የሃገርነት ዕውቅና እንድትሰጠ/ በማድረግ የተከናወነ ነው” ሲሉ ዕውነቱን አፍርጠውታል:: በጅቡቲ በሶማሌ ላንድ በኤርትራ በኬንያና በሌሎችም ሃገራት ለተወሰኑ ጊዜያት ሌሎች ሃገሮች በሊዝ ወደብ እንደሚከራዩት የተከናወነ እንጂ እስከወዲያኛው የወደብ ባለቤት የሚያደርግ አልያም የቀይባህር ቀጣናን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ አለመሆኑ እየታወቀ ነው ኦሮሙማው ቡድን ዓለም በሚያዳምጠው መገናኛ ብዙሃኑ የወደቀ አስተዳደሩን ስም ለመገንባት ሲሟሟት ያየነው:: መቼም በውሸት ዓለምን ያስናቀ አሳፋሪ ቡድን ነው:: ገና ስልጣኑን ላለማጣት ብዙ ጉድ ያሰማናል::

አሁናዊ መረጃ:- የኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ዘዴዎች በሰበር ዜና “ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች÷የቀይ ባህር ተጋሪ ሃገር ሆንን” ወዘተ የሚሉ ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን በማሰራጨት የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ እንዲሁም ለመውደቅ አንድ ሃሙስ የቀረውን የጦር ወንጀለኛና ፋሺስቱን ዓብይ አህመድ ስልጣን ለማዳን ሲጋጋጡ ታይተው መቀላመድን ከአለቃቸው ባህሪ የወረሱት መሆኑ ብዙዎችን ሲያስገርም ውሏል:: በመሰረቱ ስምምነቱ ከ5 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲነገር የቆየና ይህም በመንግስት መገናኛ ዘዴዎች ጭምር 19 በመቶ የበርበራን ወደብ አልምቶ ለመጠቀም ስምምነት ተደረገ በሚል ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው:: የሶማሌ ላንዱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙሴ ቢሂ ከስምምነቱ በኋላ በግልጽ እንዳጋለጡት የዛሬው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት “ኢትዮጵያ ለባህር ኃይል ሰራዊቷ ማስፈሪያ የሚሆን 20 ኪሎ ሜትር የውሃ ክልል ከሶማሌ ላንድ በሊዝ ለ 50 ዓመታት ለመከራየት ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት የተፈጸመ ሲሆን ስምምነቱ ነጻ ሳይሆን በሊዝ ኪራይ የተከናወነ መሆኑን በተጨማሪም በአንጻሩ ኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዕውቅና ላልተሰጣት ሱማሌ ላንድ ሃገር መሆኗን ዕውቅና እንድትሰጣት /የሃገርነት ዕውቅና እንድትሰጠ/ በማድረግ የተከናወነ ነው” ሲሉ ዕውነቱን አፍርጠውታል:: በጅቡቲ በሶማሌ ላንድ በኤርትራ በኬንያና በሌሎችም ሃገራት ለተወሰኑ ጊዜያት ሌሎች ሃገሮች በሊዝ ወደብ እንደሚከራዩት የተከናወነ እንጂ እስከወዲያኛው የወደብ ባለቤት የሚያደርግ አልያም የቀይባህር ቀጣናን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ አለመሆኑ እየታወቀ ነው ኦሮሙማው ቡድን ዓለም በሚያዳምጠው መገናኛ ብዙሃኑ የወደቀ አስተዳደሩን ስም ለመገንባት ሲሟሟት ያየነው:: መቼም በውሸት ዓለምን ያስናቀ አሳፋሪ ቡድን ነው:: ገና ስልጣኑን ላለማጣት ብዙ ጉድ ያሰማናል::

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.