Breaking News
Home / Categories (page 5)

Categories

ለውጭ ምንዛሪ ክምችት ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ::

ለውጭ ምንዛሪ ክምችት የተለየ መፍትሔ ካልተገኘ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር ሌላ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ 31 March 2019 ዮሐንስ አንበርብር የልማት ባንክ የማይመለስና አጠራጣሪ ብድር 18.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል በሦስት ወራት 344 ሚሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል በቀጣዮቹ ወራት በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ካልተገኘ በስተቀር፣ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በዘለለ የኢኮኖሚውን ፍላጎት ማስተናገድ እንደማይቻልየብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ መጋቢት19 ቀን 2011 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት። የባንኩ ገዥ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ለውጭ ገበያ ከምታቀርባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ1.64 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አመልክተዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በ2010 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው መጠን ጋር ሲነፃፀር በ9.4 በመቶ ያነሰ እንደሆነገልጸዋል። ከግለሰቦችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተላከ የሐዋላ ገቢ በአጠቃላይ 3.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ አስረድተዋል። በተቃራኒው ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸው ምርቶች 10.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉን፣ ይህም ወጪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.3 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጣው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ለነዳጅ ግዥ የተከፈለው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ አስታውቀዋል። በተጠቀሱት ወራት ወደ አገር ለገቡ ሸቀጦች የተከፈለው የውጭ ምንዛሪና ወደ ውጭ ከተላኩ ሸቀጦች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መሀል የ8.9 ቢሊዮን ዶላርየንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሚታይ የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ የተገለጸው ጉድለት የተሸፈነው ከአገልግሎት (በዋናነት ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት)፣ከውጭ በሐዋላ ከተላከ ገቢና ከውጭ ከተገኘ ዕርዳታና ብድር መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት የ2.6 ወራት ፍላጎትን ለመሸፈን ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ገልጸዋል።  የንግድ ማኅበረሰቡ የውጭ ምንዛሪ በተመለከተ የሚያቀርበውን እሮሮ በመጥቀስ የምክር ቤቱ አባላት ስለመፍትሔው ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን፣ የባንኩ ገዥበሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ያለው የውጭ ምንዛሪ መጠን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስና የግሉን ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ የሚችልበትሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።  እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ እየዋለ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከተለያዩ አገሮች ጋር ተነጋግረው ማምጣት የቻሉት2.7 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥረት እንደተገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመሳሳይ ጥረት ተደርጎ በቀጣዮቹ ወራት ተመሳሳይ ሀብትካልተገኘ ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ እንደማይቻል ገልጸዋል። “ይህ ካልሆነ ልናደርግ የምንችለው ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለነዳጅና ለመድኃኒት ግዥ ብቻ በጥንቃቄ ማዋል ነው፤” ብለዋል። ከዚህ በመለስ ኢኮኖሚውንለማንቀሳቀስ የአምስትና የአሥር ዓመታት ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ አስረድተዋል።  በተመሳሳይ ቀን ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ መንበረ ሥልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አረንቋ ውስጥ ወድቆእንደገጠማቸው ገልጸዋል። …

Read More »

Ethiopia wins Patent ownership rights over Teff seed.

News:Ethiopia wins Patent ownership rights over Teff seed used for making Injera against a Dutch national… በጤፍ ላይ የፓተንት ባለቤትነት መብት አለኝ ብሎ ሲሟገት የነበረው የኔዘርላንድስ ነጋዴ አገሩ ላይ ዘሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት ተፈረደበት:: የጤፍ የባለቤትነት መብት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው:: እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ:: ላደረጋችሁልን ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናለን:: …

Read More »

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.