Breaking News
Home / Amharic / ጀነራል ተፈራ ማሞ የት እንዳሉ ታወቀ! ግርማ ካሳ

ጀነራል ተፈራ ማሞ የት እንዳሉ ታወቀ! ግርማ ካሳ

ጀነራል ተፈራ ማሞ የት እንዳሉ ታወቀ #ግርማካሳ[yikes-mailchimp form=”1″]

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት፣ በሕልውናው ጦርነት ውስጥ ተጠርተው እንዲያገለግሉ የተደረጉት፣ ውጤትን ያስመዘገቡና የሕወሃት እና ኦነግ ወረራ እንዲቀለበስ ያደረጉት ፣ በሕዝብ ተወዳጅ የሆኑት፣ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ከሶስት ቀናት በፊት መታፈናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ያም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ አገሪቷን ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ እንድትፀፈቅ አድርጓታል፡፡

ጀነራል ተፈራ በአዲስ አበባ፣ አቶ ዪሐንስ ቧያሌውን ካናገሩ በኋላ ከሰዓት በኋላ ወደ አስር ሰዓት ( 4 PM ) አካባቢ ነበር የታፈኑት፡፡

ኢትዮ360 አደረኩት ባለው ማጣራት መሰረት፣ ጀነራሉ ታፍነው የተወሰዱት አዲስ አበባ ሳር ቤት አካባቢ ባለ እሥር ወይም ማፈኛ ቤት ሲሆን፣ የታፈኑትም የኦህዴድ/ኦነጉ በከር ሻሌ ወንድም በሆነው፣ በኦህዴድ/ኦነጉ በብርጋዴር ጀነራል ጀማል ሻሌ ነው፡፡

ጀነራል፤ ጀማል ሻሌ በመከላከያ ደህንነት መምሪያ፣ የካዉንተር ኢንቴሊጀን ዳይሬክተር እንደሆነ የዘገበው ኢትዮ360፣ ጀነራሉ በቀጥታ ኮማንዶዎች ይዞ ጀነራል ተፈራ ማሞ እንዲያፍን፣ በቀጥታ በአብይ አህመድ በራሱ እንደታዘዙ ይፋ አድርጓል፡፤

የጀነራሉ ስልክ በተለያዩ ሰዓታት እየተከፈተ ይዘጋ እንደነበረና፣ ምን አልባት ማን እንደሚደውል፣ ማን ቴክስት እንዳደረገ ወዘተ የመመርመር ስራ ተሰርቶ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ፣ የአፈናው ዘመቻ ሙሉ ለሙሉ በኦህዱኤድ የተመራ እንደሆነ ነው ኢትይ360 ያሳወቀው፡፡

ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ታፈነው የቆዩት ጀነራሉ ምክንያት፣ በሕዝብ ዘንድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውግዘትና ቁጣ እንደቀሰቀሰ የተረዱት እነ ዶር አብይ አህመድ፣ “ኦህዴድ አይደለም ያፈነው፣ እኛ እጃችን የለበትም” የሚል ውሸት ለማስነገርና ለማጭበርበር፣ በአማራ ክልል ያሉ አመራሮችን ለማስጠቆር፣ ሃጢያቱን፣ ክሱን፣ ቁሻሻዉንም አሳፋሪ ተግባራቱን እነ ይልቃል ከፍያለ ላይ ለማላከክ እንዲመቻቸው፣ ጀነራል ተፈራ ዛሬ ወደ ባህር ዳር መወሰዳቸውን፣ ቀበሌ 9 በሚባል ቦታ መታሰራቸውን ኢትዮ360 አክሎ ዘግቧል፡፡

የአብይ መንግስት የአማራ ክልል ካልተተራመሰ፣ እርስ በርስ ፍጀት ካልተፈጠረ በስልጣኑ መቀጠል እንደማይችል ገብቶታል፡፡ በሰኔ 15 ቀን ከሶስት አመታት በፊት፣ እንዳደረገው አሁንም ከሕወሃት ያልተናነሰ አሸባሪ የዉንብድና ተግባራት እይፈጸመ ነው፡፡

የሚያሳዝነው ግን በአማራ ክልል ለኦህዴዶች ሰይጣናዊ ተግባር ተልእኮ ተባባሪ የሚሆኑ፣ ለኦህዴድ አህያ የሆኑ ይመስል የሚጋለቡት፣ በሃላፊነት ላይ ያሉ የአማራ ብልጽግና የሚባሉ ምናምንቴዎች መኖራቸው ነው፡፡

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.