Breaking News
Home / Amharic / የአፄ ሚኒልክ ሀውልት ጎን የቆሸሸ ቆርቆሮ ቤት ተሰራ !

የአፄ ሚኒልክ ሀውልት ጎን የቆሸሸ ቆርቆሮ ቤት ተሰራ !

የዝምታ ውጤቱ እዚህ ድረስ ነው ።
በማናለብኝነት የአፄ ሚኒልክ ሀውልት ጎን የቆሸሸ ቆርቆሮ ቤትን በመስራት ታሪክን የሚያወድም ታከለ የሚባል ከንቲባ በተግባር ስራውን እያሳየ ይገኛል።
ያዲሳባ ወጣት ሆይ የሚኒሊክን ሀውልት ብቻ አፍርሶ የሚቆም መንጋ እዳይመስልህ እየመጣብህ ያለው ነገ በላይህ ላይ ቤትህን ያፈርሰዋል። ትኩረት፦ #አዲስ_አበባ ‼️
-~•<<•>>•~-
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት በታላቁ ንጉሥ #ዐፄ_ምኒልክ መታሰቢያ ሐዉልት አደባባይ ውስጥ ታጥሮ የተቀመጠው የቆርቆሮ ቤት እንዲፈርስ አሳሰበ፡፡

የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ሐዉልት በቅርብ ጊዜ እድሳት ተደርጎ ከተጠናቀቀ በኃላ ለእረጅ ጊዜ ታጥሮ የተሰራዉ የቆርቆሮ ቤት እንዲሁም በግቢዉ ውስጥ የሚታየው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ልብስ እያጠቡ የሚያሰጡ ግለሰቦች መኖራቸው በተደረገዉ ማጣራት ከሕዝብ በመጣ ጥቆማ ለመታዘብ ተችሏል፡፡ ባላደራዉ ይህን የሕዝብ ጥያቄ ከግምት በማስገባት የሚታዩ ስጋቶችን ለመቅረፍ የተሰራው ቤት በፍጥነት እንዲፈርስ በውስጡ የሚታየዉን የፅዳት መጓደል እንዲስተካከል ለአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ዘርፍ በደብዳቤ አሳስቧል፡፡

ይህን ጥያቄ የተቀበሉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ በአጭር ጊዜ ከአመራሩ ጋር በመነጋገር መልሳቸዉን እንደሚያሳውቁ በቃል አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩ፦ በምኒልክ አደባባይ ስለተሰራው ቆርቆሮ ቤት
—————————————————–
በምኒልክ አደባባይ የታላቁ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት ቆሞ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ሀውልቱ የአዲስ አበባ መለያ ሆኖ ከመቆየቱም ባሻገር፣ ከአድዋ ድል ጋር በተሳሰረ የመላ አፍሪካዊያንም ኩራት መገለጫ ሆኖል፡፡ በዚህም ሳቢያ፣ በመላ ኢትዮጵያዊያን ዘንድም ሆነ በአፍሪካዊያን ዘንድ በታላቅ ከበሬታ የሚታይ ነው፡፡

ሆኖም፣ ቀላል ለማይባል ጊዜ ሀውልቱ በሚገኝበት አደባባይ ህገ ወጥ የቆርቆሮ ቤት ተገንብቶ ይገኛል፡፡ ይህ ህገ ወጥ ቆርቆሮ ቤት የታላቁን ንጉሰ ነገስት ክብር ለመንካት ሆን ተብሎ ከመቆሙም ባሻገር፣ የከተማዋን መልካም ገፅታ በእጅጉ አበላሽቶታል፡፡

ይህን አስመልክቶ ህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ የሚገኝ በመሆኑ፣ በህዝቡ ጥያቄ መሰረት ህገ ወጡ ቆርቆሮ ቤት እንዲፈርስና በአደባባዩ ላይ ምንም ዓይነት ህገ ወጥ ግንባታ እንዳይደረግ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

እስክንድር ነጋ

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ
አዲስ አበባ

ድል ለዲሞክራሲ፣ ፍትህ እና እኩልነት‼️

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.