Breaking News
Home / Amharic / የተነፈሰ ጎማ ብዙ አይራመድም !

የተነፈሰ ጎማ ብዙ አይራመድም !

ምነው ዘመነ ካሤ መወሽከት አበዛ፤ በመንግሥት ደረጃ ያለን አካል ለመጣል ትጥቅ ትግል የሚያደርግ ሰው ወሬ አሉባልታ ካበዛ እየተዋጋ አይደለም።እንደዚህ ዓይነት ብዙ
የሚያወራ ሰው ጠላት በቢሊዮን ገንዘብ ከፍሎ የማያገኘውን መረጃ በቀላሉ ከማቀበሉም በተጨማሪ በሌሎች ጀግኖች ተከሻ ላይ የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆን የአፍ ሮኬት ማፈንዳት ተገቢ አደለም ።

ጠላት ዘመነ የሚናገረውን ዓይነት መረጃ ካገኘ ቢያንስ ፋኖ ተፈረካክሷል እያለ ለኘሮፓጋንዳ ፍጆታ ይጠቀምበታል፤ “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” ማለት ትርጉሙ መረጃን አሳልፎ በመስጠት የሚመጣ ኪሣራ ማለት ነው።
አንድ ትጥቅ ትግል የሚመራ ሰው፤ እያንዳንዷ ቅንጣት በዘፈቀደ የሚናገረው ማንኛውም ነገር ሁሉ ከሚተኩሰው ጥይት በላቀ ሁኔታ ለጠላት ከፍተኛ መረጃ በመስጠት ደረጃ ትልቅ አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑን ያለመረዳት እና ብስለት ማጣት ጎልቶ ይታያል።
ቢያንስ በእነ ዶክተር አንባቸውና በጀነራል አሳምነው ፅጌ መካከል በተመሳሳይ መልኩ አምቻ ጋብቻ፣ ሰሜነኛው ደቡቡ፣ ፋርጣ ሞጣ ጎጠኛ አውራጃኛ እያለ መናኛ በሆነ ምክንያት ብዙ መሥራት የሚችሉ ጀግኖች በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ታይተው እንዲጠፉ በማድረግ ደረጃ ከሠራው ስህተቱ ትልቅ ትምህርት ሊወስድ በተገባ ነበር።
በዚያን ወቅት ሕዝባችን ጨዋ፣ አርቆ አሳቢ አስተዋይ ሆኖ እንጅ ቀጣይነት ባለው ለጠላት በተመቸና በሚፈልገው መልኩ በአንድ ሕዝብ መካከል ዐባይ ማዶና ዐባይ ወዲህ የተከፈተው አጥፊ መንገድና ተደቀኖ የነበረው ከፍተኛ አደጋ ወገን ከወገኑ የሚያጫርስ ካባድ ችግር ላይ የሚጥል እንደነበረ በሚገባ እናውቃለን።
የጀነራል አሳምነው ፅጌ ጠንካራ ከፍተኛ የዐማራ ሕዝብ ተቆሮቋሪነቱ እንዳለ ሆኖ፣ ትልቁ ስህተቱ ጠላት ያለ ጊዜው ያለ ወቅቱ ሊሰማቸው የማይገባቸውን በጣም አንኳር እና ወሳኝ ነገሮች በአደባባይ መናገሩና ጠላት ከሚደረግለት ዝግጅት የጥቃት አደጋ ሳይቀደም ለመቅደም ፈጥኖ ለማምለጥ የወሰደው እርምጃ የሌሎችንም የራሱንም ሕይዎት አጥቶ ዐማራን ያለ ምንም ጠንካራ ተቆርቋሪ ባዶ አስቀርቶታል።
“የተነፈሰ ጎማ ብዙ መንገድ አይወስድም” የሚለውን የዶክተር አንባቸውን ብሂል ሥራ ላይ ማዋል ጠቀሜታው ከፈተኛ ነው። በተለይም በትጥቅ ትግል ደረጃ በየትኛው አጋጣሚ የትኛውንም መረጃ ለመቃረም ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንጅ ጀግና ለመባል ከሚመነጭ ፍላጎት መረጃ በከንቱ አሳልፎ መስጠት የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው።
“ደም እመልሳለሁ” ብለህ ስትናገር ደም የሚመለስበት አካል ጀሮው እየሰማ እጁን አጣጥፎ ገዳዮን አይጠብቅኀም፤ ቢያንስ አጥቂ ቦታ ይዞ ታጥቆ ተዘጋጅቶ ይጠብቅኀል። ትግሉ ደግሞ ደም የመመላለስ ጉዳይ አደለም፤ በሥልጣን ላይ ያለን ግዙፍ በጀት፣ ትጥቅና ስንቅ መድቦ የሚወጋህን አካል መራር በሆነ ሕዝባዊ ድጋፍ ባለው የትግል ውጤት ትክክለኛ ሕዝባዊ መንግሥት የመተካት የዐማራን መብት በዘላቂነት የማስከበር ተጋድሎ ነው።
ያለፈው አለፈ ብለን ብንተወው እስክንድርን አሳንሶ እራሱን አግዝፎ እና አጀግኖ ከእኔ በላይ ማንም የለም የሚለው ቅዥት ሁሉ ለፋኖ ትግል አንዳች ጠቃሚታ የለውም። እስክንድር “አለቃየ ” አለኝ ? እስክንደር “አለቃየ” ያለህ ወይም ካለህ ከትህትና ከወንድምነት ከመከባበር ለትግሉ ሞራል ከመስጠት ከማበረታት አንጻር ከብልህነት የመጣ እንጅ አንተ በእሰክንደር ላይ የተሾምክ አለቃ ማን አደረገህ፤ አሁን ታግሎ ማታገል እንጅ የአለቃና የምንዝር ጉዳይ የሚነሳበት ጊዜውም ወቅቱም አይደለም።
የፋኖ ትግል የሽምቅ ውጊያ ነው፤ በተጠና አቋራጭ ቦታ እና በአጭር ጊዜ በመጠነኛ ቀልጣፋ ኃይል ትልቅ ኪሣራ ማድረስ፤ ይህ ዓይነቱ ትግል ቅንጣት መረጃን አሳልፎ ከመስጠት እጅግ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው፤ ትፋሽክን ዋጥ አድርገህ እንደ እባብ በደረትህ የምትሳብ እንደ ነብር አድብተህ ማጅራት የምትነክስበት እንጅ እይደለም ድምፅህን የምትራመደው የጫማ ኮቲህን የማታሰማበት ለፍዳዳ ሳይሆን ቆምጫጫ የትግል አቅጣጫ ነው።
በዚህ የስነ ልቦና ጥናት በተራቀቀበት ዘመን በሆነ ባልሆነው እየወጡ በከንቱ መዘባረቅ “ከምትናገረው ይፈረድብኀል” ማለት እራስህን ለቀላል የስነ ልቦ ጥናት አጋልጠኀል ማንነትክን ለመረዳት የሚያስችል ቀላል መንገድ ከፍተኀል ማለት ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ በጎጃም ዐማራ ፋኖ ግንባር ቀደም ተጋይ ጀግና የፈረስ ቤቱ ተወላጅን #ዝናቡን የሚያስንቅ ወንድ የለም፤ግን ድምፁ አይሰማም ለምን የሚታገለው ጠላት በወሬ ጋጋታ የሚወድቅ እንዳልሆነ ይረዳል። እውነቱ ይኸው ነው። ዘመነን መምከር የምትችሉ ካላችሁ ብዙ #ከመተንፈስ ተቆጠብ በሉት።

Check Also

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.