Breaking News
Home / Amharic / የመንግስት መከላከያ ተብዬዉ መንገድ እየጠረገ እያስረከበ ነዉ::

የመንግስት መከላከያ ተብዬዉ መንገድ እየጠረገ እያስረከበ ነዉ::

ወያኔ የመጨረሻ ካርዷን መዛለች ፣ ፊቷን ወደ ውጫሌ/ሃይቅና ጭፍራ/ሚሌ አዙራለች #ግርማካሳ
ከዚህ በታች የምትመለከቱት ካርታ ላይ በቀይ የተከበቡት በወያኔ ስር ያሉ ናቸው፡፡ በአረንጓዴ ያሉት በወገን ስር ያሉ ናቸው፡፡ በብርቱካማ ቀለም ያሉት ግልጽ መረጃ ያለገኘሁባቸው ወይም ትኩስ ጦርነት እየተደረጋቸው ያሉ ናቸው፡፡
የሚከተሉት ግንባር ነው ያሉት፡
#የጠለምት ግንባር
#የዋገምራ ግንባር
#የጋሸና ግንባር
#የደላንታ ግንባር
#የውጫሌ ግንባር
#የጭፍራ ግንባር
#የአምባሰል ግንባር
ከነዚህ መካከል የጠለምት፣ የዋገምራ፣ የጋሸና የደላንታ ግንባሮች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ነው፡፡ የዉጫሌው፣ የጭፍራዋን የአምባሰል ግንባሮች ግን ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደሉም፡፡በብርቱካማ ያከበብኳት ዉጫሌ ከፍተኛ ዉጊያ አለ፡፡ በጭፍራም አካባቢም እንደዚሁ፡፡
የወያኔ ታጣቂዎች በአጭር ጊዜ ውጫሌና ጭፍራ ደጃፍ መድረሳቸው አስገራሚ ነው፡፡ ከሁለት፣ ሶስት ወር በፊት በመከላከያ ውስጥ ያለው ሳቦታጅ አሁንም እንዳለ አመላካች ነው፡፡ ምን አልባትም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ግንባሮቹን ለቀው የሚሄዱት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ክተት አታዉጁ ንግግርን ስምተው፣ በዚህ ንግግር የኮድ መመሪያ ተላልፎላቸውም ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ በዝርዝር በስፋት እመለስበታለሁ፡፡
ወያኔዎች ለምን ወደ ደሴ ለመሄድ አሰቡ ? ምን የሚያገኙት ነገር አለ ? መልሱ ቀላል ነው፡፡ ወያኔዎች ያላቸው ብቸኛ ካርድ ደሴንና ኮምቦልቻን በመያዝ ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ በመፍጠር ፣ ወይንም የጅቡቲ አዲስ አበባን መስመር በመዝጋት አዲስ አበባን አንቆ የአብይ መንግስትን ለድርድር ለማስገደድ መሞከር ነው፡፡ ዶር አብይም “እሺ እሺ ወልቃይትን እሰጣቹሃለሁ፣ እናነት ብቻ ከደሴ ውጡልኝ” ብሎ በነርሱ ፍላጎት ለድርድር ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
ወያኔዎች የዘነጉት ነገር ዶር አብይ ለድርድር ቢዘጋጅ የአማራ ክልል ይቀበላል ወይ ? የሚለው ነው፡፡ አይቀበልም፡፡ ስለዚህ ወያኔዎች ዶር አብይ ላይ ጫና በማሳደር ወደ ድርድር እንዲመጣ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ቢሳካላቸውም እንኳን፡፡
ወያኔዎች ያላቸው አንዷን ካርድ እንግዲህ ጥለዋል፡፡ ውጫሌና ጭፍራ ላይ እነርሱን ማስቆም ከተቻለ፣ ወይንም ጭፍራንና ውጫሌን ቢይዙም ወደ ሃይቅና ወደ ሚሌ እንዳይሸጋገሩ ማድረግ ከተቻለ፣ በራሱ ለወያኔዎች ትልቅ ሽንፈት ብቻ ሳይሆን መጨረሻቸውም ነው፡፡ የደሴና የኮምቦልቻ ወጣቶች ቀደም ሲል ወያኔ ሞክራ የነበረ ጊዜ እንዳደረጉት ወያኔን የመመከት ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በጋሸና ያለው ግንባር የሚፈረጥጡ፣ በአሻጥረኛ መኮንኖች የሚመሩ ታጣቂዎች ያሉበት ግንባር ሳይሆን፣ በጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች የሚመሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ ከመከላከያ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ቀላል የማይባል የፋኖና አማራ ልዩ ኃይል አባላት ያሉበት ትልቁና ጠንካራው ግንባር ነው፡፡ በዚህ ግንባር ያለው ኃይል ወደ ወልዲያ ፊቱን አዙሯል፡፡ ያ ማለት እንደ ውሻ ወደ ደሴ እየሮጠ ያለው የሕወሃት ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ይቆረጣል ማለት ነው፡፡ሰዎቹ ተስፋ ቆርጠው ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገቡት፡፡

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.