Breaking News
Home / Amharic / ስለ አማርኛ ቋንቋ ይሄን ያውቁ ነበር?

ስለ አማርኛ ቋንቋ ይሄን ያውቁ ነበር?

➜ አማርኛ አማራ ተብሎ ከሚጠራው የብሔረሰብ መጠሪያ የተገኘ ነው።

➜ አማርኛ የተፈጠረው ላስታ እና አካባቢው ነው።

➜ አማርኛ ከሴም የቋንቋ ዝርያዎች የተገኘ ነው።በሴም ውስጥ ግዕዝ፣ ትግሬ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ አደርኛ፣ ጉራግኛ፣ አርጎብኛ እና ጋፋትኛ ይገኛሉ።

➜ ለአማርኛ ቅርብ የሆነው ቋንቋ አርጎብኛ ነው።(እኔን ጨምሮ ብዙ ሰው ትግርኛ ይመስለዋል)

➜ አማርኛ ልሳነ-መንግስት ቋንቋ ነው።

➜ ክልሎች አማርኛን የስራ ቋንቋቸው አድርገው ይጠቀሙታል።

➜ አማርኛ መነገር የጀመረው በ1000 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነው።(ዓመተ ምህረት ሳይሆን ዓመተ ዓለም ነው)

➜ የአማርኛ ፊደል የተገኙት ከግዕዝ ቋንቋ ነው።27 ከግዕዝ ሲወስድ 7 የራሱን ጨምሯል።ግዕዝ ደግሞ ከሳባ ወስዷል።

➜ የአማርኛ ፅሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውስጥ የወጣው አፄ ቴዎድሮስ ለንግስት ቪክቶሪያ የላኩት ደብዳቤ ነው።

➜ የመጀመሪያው የአማርኛ መፅሀፍ በ19ነኛው ክ/ዘመን በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ በደብተራ/አለቃ ዘነብ “መፅሀፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ” የሚል ርዕስ ነበረው።

➜ የመጀመሪያው የአማርኛ ልቦለድ የታተመው በ1919 ሲሆን ርዕሱ “ጦቢያ” ይሰኛል።ደራሲው አፈ-ወርቅ ገ/የስሱስ ናቸው።

➜ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አማራዎች ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያዊያኖች ናቸው።

➜ አማርኛ በተናጋሪ ብዛት፣ በቃላት ብልፅግና፣ በስነ-ፅሁፍ፣ ጋዜጣ፣ ፊልም እና በመሳሰሉት የበለፀገ ቋንቋ ነው።

➜ በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ከሚነገሩ ቋንቋዎች ከሀውሳና ከስዋሂሊ ቀጥሎ 3ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።በሴም ቋንቋነቱ ደግሞ ከአረብኛ ቀጥሎ 2ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

➜ በዋሽንግተን ዲሲ ከእንግሊዝኛ ቀጥሎ እንደሁለተኛ ቋንቋ የማገልገል ህጋዊ መብት አለው።

➜ በዓለም-አቀፍ እውቅና አግኝተው እንደ አንድ የትምህርት አይነት ከሚሰጡት ውስን ቋንቋዎች አንዱ አማርኛ ነው።

➜ በዓለም አቀፉ ትምህርታዊ ፕሮግራም ከታቀፉት ጥቂት የአፍሪካ ቋንቋዎች በከፍተኛ ደረጃ ከሚሰጡት ቀዳሚው አማርኛ ነው።

➜ ብዙ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች አማርኛ ቋንቋን ያስተምራሉ።

➜ በአፍሪካ ብቸኛው የራሱ ፊደል ያለው ቋንቋ አማርኛ ነው።

➜ በአጠቃላይ አማርኛ ከብሔራዊ ቋንቋነት አልፎ ዓለማቀፋዊ ይዘትን ተላብሷል።

ሼር ብታደርጉት ብዙ ሰው ታስተምራላችሁ።

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.