Breaking News
Home / Amharic / Message from Ethiopian Medical Doctor . ዘብሔረ አምሀራ

Message from Ethiopian Medical Doctor . ዘብሔረ አምሀራ

አዲአበባ ዬኒቨርስቲ ሜዲካል ፋካሊቲ ፡ ውስጥ ዶር ፕሮፌሰር አስራት ፡ እጀን ይዘው አስተምረውኛል ፡

ከዛ ባለፈ በህክምና ሙያ በአሜሪካው Yale Universty ድረስ ገብቸ የልብ ስፔሻሊስትነት
(Cardiologist ) ተመርቄ አሜሪካ ዜጎችን አክማለሁ ።

የዶር አብይ ፖለቲካ ታማኝ ቢሆን አገሬ ገብቸ ለልብ ህሙማን እርዳታ ባደረኩ ነበር ።

ዳሩ ግን አንዱ ዘር ሌላውን በቆንጨራ ሚገልበት ፡ አንድነት ነን ብለው ለአመታት የሰበኩኝ ፓርቲዎች በውሸት መደመር አገር ቤት ገብተው በአንድ ቀን የኦነግ የሞተ ስልብ ደጋፊ ሁነው ሳገኛቸው ፣ እጅግ ሞራሌ ተነካ ፡ አማራ ብሆንም አማራነቴን እስከዚህ ቀን አላውቅም ነበር ፡ ዛሬ ማንነቴን እኔ ሳይሆን እነሱ አሳወቁኝ ። ካሳወቁኝ በኋላ ግን ። እንዲህ አሰብኩ ፡ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል አማራዊነትን ማስቀደም ተገቢ ነው አልኩ ። ዞር ብየ ሳይ ለካስ ሌሎች ሀኪሞችም ፡ Like Dr. Abebe Kassahun ከኔ ከአመታት በፊት ነገሩ ገብቷቸው ሲታገሉ ኑረዋል ፡ እጅግ በጣሞ አፈርኩ ። ወዲያውም ተፅናናሁ ። 
ዶር አስራት ህክምና ብቻ ሳይሆን ፓለቲካንም በተለይ ለአማራ ደህንነትና መኖር መሞትና መዳን እንደሚያስፈልግ አስተምረውን አልፈዋል ከዚህ ቀን በኋላ እኔም ሆነ ሌሎች አማራ ዶክተሮች ለምናደርገውየ ፖለቲካ አስተዋፅኦ ዝቅ ያለ ግምት እንደማትሰጡን ተስፋየ ከፍ ያለ ነው ።
ዶር አገኘሁ

Check Also

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት ሐሰተኛ መረጃ !

አማኑኤል ይልቃል የሥራ ድርሻ,ቢቢሲ አማርኛ ዘገባው ከናይሮቢ ከ 8 ሰአት በፊት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም …

ኢትዮጵያዉያን የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ፈንቅለው ገብተው ተቃውሞ አሰሙ !

Ethiopians protest against Abiy Ahmed in Geneva Switzerland!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.