Breaking News
Home / Amharic / የካንጋሮ ፍርድቤት ዉሎ !

የካንጋሮ ፍርድቤት ዉሎ !

“በልደታ ፍርድ ቤት ታሪክ ተፈፀመ! ”
➖➖➖
▸▸▸ « የግራ ዳኛው የዋስትና መብቱ ውድቅ መሆኑን አንብበው ጨረሱ። በዚሁ ሁነት ውስጥ በፍትህ ችሎት አዳራሽ የነበረው ታዳሚ ከፍተኛ ፀጥታ ሰፍኗል።
የመሀል ዳኛውም (በእነ ታላቁ እስክንድር ነጋ ክስ የቀኝ ዳኛ የነበረው የመሀል ዳኛ ረቡማ ነው) አጁን በአፉ አስደግፎ እያየ ነበር።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ፀጥታውን ነቅተው እየጠበቁ ነው። ውሳኔውም ተነቦ አለቀ። 24’ቱም ተከሳሾች ከመቀመጫው ተነሱ! ከፊት ለተቀመጡት ዳኞች ጀርባቸውን ሰጥተው ዞሩባቸው! ዳኞቹም ደነገጡ!
የፌደራል ፖሊስ አባላትም ከመቀመጫቸው ተነሱ! መሳሪያቸውን ማቀባበል ጀመሩ! የችሎቱ ታዳሚና ቤተሰቦችም ምን እየሆነ ነው
በሚል ስጋት ውስጥ ገባን! በመቀጠልም 24’ቱም እስረኞች ለአንድ ደቂቃ ድምቅ ያለ ጭብጨባ አጨበጨቡ!
ችሎቱ ተናጋ! ቀጥለውም ሶስት ጊዜ አማራ! አማራ!! አማራ!!! ብለው ፎከሩ! አንዳች ነገር ሰውነቴን ወረረኝ። አስከትለውም ልክ እንደ ፋኖ የስልጠና መርሀ ግብር አንተ ማነህ!? …. አለ ከእስረኞቹ አንዱ! ሁሉም በአንድ ድምፅ «አማራ!»
አሉ ደግሞ ማነህ አላቸው!? አማራ!! አማራ!! ሶስተኛውንም ደገሙት። ለሰከንዶች የተከሳሾች ጭብጨባ ቆመ! ፀጥ አለ። …..
ቀጥሎም የተከሳሽ ቤተሰቦች ማጭበጨብ ጀመሩ! ነገሩ ተቀየረ ዳኞችና የፌደራል ፖሊሶች ፊታቸውን ወደ ታዳሚው አዞሩ! ጭብጨባውም ለደቂቃዎች
ቀጠለ …በመቀጠልም ተከሳሾችና የተከሳሽ ቤተሰቦች በጋራ አዳራሹ እስኪናጋ ድረስ አጨበጨቡ። ከዲቂቃዎች በኃሏ ዳኞቾ አንገታቸውን ደፍተው ወጡ!!
አዳራሹን ሙሉ ለሙሉ በተከሳሾች ቁጥጥር ስር ዋለ። ቀጥሎም አንደኛው ተከሳሽ ያቅራራ ይፎክር ጀመር…… “አማራ ነን ነባር ህዝቦች ባለታሪክ ባለገድል” የሚለው የአማራ መዝሙር እየተዘመረ ወጡ-ወጣን ከዚህ በኃላ
የሆነው የአማራ ባህሉ ነበር። »
Solomon Alamenia ስላካፈልከን የችሎት ውሎ እያመሰገንኩ “የብልፅግና አባል ሳይሆን የብልፅግና ተመራጭ ለመሆን የበቃውን ሰውዬ” ሰላም ባለማለትህ በእውነቱ ታሪካዊ ስህተት ፈፅመኃል::
 
ለህሊናችን ብለን ቤተሰቦቻቸዉን እንርዳ !
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.