ጠገዴ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆና በአማራ ልዩሃይል እገዛ ውጊያ በመደረጉ በአማራ ቁጥጥር ስር ሆናለች.!
ማምሻውን ከቁጥር በላይ መከላከያ ከቆቦ እስከ ዋጃ ድረስ ሰፍሯል:: የቆቦ ህዝብ ደስታውን ሲገልፅ አምሽቷል:: ነገ ብዙ ከአማራ የተወሰዱ መሬቶች ከ25 ዓመታት ብኃላ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ዕርስታቸው እንደሚገቡና የአማራ ህዝብ ነፃ እንደሚወጣ ይጠበቃል::
በመቀሌው ኦፕሬሽን በፕላኔት ሆቴል በተደረገ ፍተሻ የልዩ ልዩ አገር ገንዘቦች ሲገኝ የህዋሃት ባለስልጣናት ከሆቴሉ ውስጥ አምልጠው ቢሰወሩም ውጭ ላይ ጥቂቶቹ ሲያዙ ደብረፂዯንን ጨምሮ አብዛኞቹ ጠፍተው ወደ አድዋ እንደሸሹ ተጠርጥሯል::
በዳንሻኽ በኩል ጠበቅ ያለ ውጊያ ገጥሞ የዋለው የትግራይ ልዩ ሃይል ከሰዓት በላይ አብዛኛው እጅ እየሰጠ ወደ አማራ ክልል መግባቱ ተጠቁሟል::