ሃገር በቀልም ይሁን አለም አቀፍ ስራው በህጋዊ ጨረታ ስለመሰጠቱ ማብራሪያ ስለመጠየቅ !! አለም አቀፍ ተቋራጩ https://geda.co.uk/about/ ወይስ Geda Construction general Contractor?
#ኢፈርትና_ሱርን ወደ መቀሌ አባሮ ተረኛው #የገዳ ኮንስትራክሽ አዲስ አበቤ ላይ ከተመ ወይስ በህጋዊ ጨረታ ለአለም አቀፉ Geda Construction የተሰጠ ነው ? ከሱር ወደ ገዳ ፣ ከኢፈርት ወደ ገዳ ኢንቨስትመንት ሽግግር ወይስ ሽግሽግ ? የአዲስ አበባ ህዝብን መቀራመት ለዘመናት የዘለቀ የገዢዎች መንገድ ነው ። ከንቲባ ታከለ ኡማም የሃብት ቅርምቱን ለማቀላጠፍ በዶር አብይ የተሾሙ ተረኛ ወይስ …..? ይህ ጥያቄ የህጋዊነትና የፍትሃዊ ሃብት ክፍፍል ጉዳይ እንጂ ከብሄር ጋር ተዛማጅ እንዳልሆነ ከግምት ይግባልኝ ! ኦሮሞን የምንወድበት 1001 ምክንያቶች አሉን ! ተረኝነት ግን አንዱ አይደለም !
ጥያቄ !!
አዲስ አበባ የተጀመሩት ኮንስትራክሽኖች ለገዳ ኮንስትራክሽንም ይሁን ለሌሎች የተሰጠው በህጋዊ የጨረታ ሂደት ወይስ ኢፈርትና ሱር ኮንስትራክሽንን ወደ መቀሌ አባሮ ፣ ተረኛው ዘራፊ ከተሞቻቸን ላይ ከተመ ? የኢንቨስትመቱ ይዘት ፣ የኮንስትራክሽን ስራው በህጋዊና ግልፅ በሆነ መንገድ የተሰጠ ወይስ ካለፉት 27 አመታት የቀጠለ የዘረፋ መንገድ ?
ህዝብ ይህንን ጥያቄ እንደ ቀላል አይወስደውም ! የአዲስ አበባ ህዝብ በከተማው የሚካሄደውን የማወቅ ህጋዊም ተፈጥሯዊም መብት አለው ።
የአለም አቀፉ Geda Construction ሲሆን ይህ ከታች የምናየው Geda Construction General Contractor የአለም አቀፉ አካል ወይል ሃገር በቀል። የጨረታ ሂደቱ በህጋዊ የተፈፀመ ወይስ በጋሮ በር ? ጥያቄው ሃገር በቀልም ይሁን አለም አቀፍ ድርጅት በህጋዊ ግልፅ ጨረታ የተሰጠ መሆኑን የሚጠይቅ ቅን ጥያቄ እንደሆነ ይሰመርበት !
Geda Construction Plc. Is Innovating Researches With It’s Not For Profit Volunteer Scientists .
https://gedaconstructionplc.websites.co.in/index.php