ወሳኝ መረጃ!
የሱዳን መከላከያ ሰራዊት መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በኩል በመግባት ስናር በተባለ የኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የእርሻ ልማት ካምፕ ዙሪያ ሰፍሯል።
ይህም የሆነበት ምክንያት፣ በዛሬ ዘገባው ዓሻርቅ አል-ዓውሳት (Asharq al-Awsat) የሚባለው ለንደን እንግሊዝ በዓረብኛ ቋንቋ የሚታተም ጋዜጣ እንዲህ ይገልጸዋል፣ 👉የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የነበረውን ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት መስማማቱንና፣ በሱዳኖች አጠራር “አልፋሽቃ” የሚባለው ይሄ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር የነበረው መሬት በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሱዳን እንደሚመለስ ጋዜጣው አስረድቷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ኢታማዦር ሹም አደም መሐመድ መሆናቸውንም አክሎ ዘግቧል፡፡