Breaking News
Home / Amharic / ሃገረ መንግስት ምስረታ (State formation) የራሱ ትልቅ ሂደት አለው ።

ሃገረ መንግስት ምስረታ (State formation) የራሱ ትልቅ ሂደት አለው ።

ክቡራትና ክቡራን በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።
ሃገረ መንግስት ምስረታ (State formation) የራሱ ትልቅ ሂደት አለው ። ይሄን ታላቅ ሂደት እንደ ተስፋዬ ገብርአብ ያለ ጦጣም ሆነ እንደ ህዝቅኤል ገቢሳ ያለ ግመሬ ሊረዳው አይችልም ። ይሄን ሂደት ለመረዳት Enlightened ( አብራሄ ህሊና ) ያስፈልጋል። የአለም ታሪክ የጦርነት ታሪክ ከመሆኑ የተነሳ የፖለቲካ ልሂቃን “Peace country has no history.” ይላሉ።
አብርሃም ሊንከን ታላቋ አሜሪካን በጦርነት ጋግሯል ። በትልቅ ድስት አንተክትኮ አዋህዷል ። አሜሪካኖቹ Melting Pot ነን እያሉ ያንቆለጳጵሱታል ። ። ኦቶቫን ቢስማርክ ጀርመንን እንደ ብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ አዋህዶ ፈጥሯል። እምዬ ምኒልክ ደሞ በብዙ ፍቅርና በትንሽ ልምጭ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓል።
አብርሃም ሊንከን በአንድነት ጠበቃ ደግፎ ባቆያት አሜሪካን አገር ሚኒሶታ ግዛት አልያም ቢስማርክ በተዋደቀላት ጀርመን፤ በርሊን ውስጥ ሆት ዶግ እየላፉ የካልዲስን ቡና እንደ ወረደ እያጣጣሙ ምኒልክ በነፍጥና በመስዋዕትነት ያቆማትን አገር ” ኬኛ ብቻ” እያሉና ለመገንጠል እየታገሉ በመሀይም መንጋቸው “ምኒልክ ጨፍጫፊ ነው” ቢሉ አንድም ርባና ቢስ የትውልድ ፖለቲካዊ ርግማን ነው፤ ሌላም አላዋቂነትን በአደባባይ መግለጥ ነው፡፡

ፓስካል ..“የክሌዖፓትራ አፍንጫ አንድ ኢንች ቢረዝም ወይም ቢያጥር ኖሮ፣ የዓለም ታሪክ የተለየ ይሆን ነበር” (If Cleaopatra’s nose, had been an inch longer or shorter world’s histoy would have been changed) በማለት ጽፏል፡፡ ይሄን ድንቅ ፖለቲካዊ አባባል ወደ እኛ አገር ስናመጣው ” የአፄ ምኒልክ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች በአንድ ሰአት ቢዘገዩ ኖሮ ኢትዮጵያም ዳግም አትመሰረትም ነበር ፣ አፍሪካም የነጮች አህጉር ትሆን ነበር።” በማለት አፋችንን ሞልተን መናገር እንችላለን።
“የአፄ ምኒልክ ጥፋት የደንቆሮ ህዝብ ንጉስ መሆኑ ብቻ ነው ። የደንቆሮ ህዝብ ንጉስ መሆን ሃሜት ያመጣል ። የቸሩ ምኒልክን ባህሪ የያዘ ሰው ያፋቅራል እንጅ አያጣላም ። ” ይሄን የፃፈው የ19ኛው ክዘ ምሁር ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ነው።
.
የኦሮሞ ልሂቃንና መንጋቸው አሁንም ኢትዮጵያ እየመራ ያለው ታላቁ ምኒልክ ይመስላቸዋል ። ጧት ላይ ከው ከው ሲሉ ላደናቀፋቸው ድንጋይ ሁሉ ምኒልክን ብሎም አማራን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በዚህ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በርካታ አማሮችንና ንፁህ ኢትዮጵያዊያንን በጠራራ ፀሐይ አንገታቸውን የቀላ የግሪሳ መንጋ ምንም ያላለ ክፍት አፍ ወልዲያ ለሞቱት ኦሮሞወች አዝናለሁ ሲል ስትሰማ ትንሽነቱ ፍንትው ብሎ ይታይሐል፡፡
ሽመልስ አብዲሳ የሚባል ግሪሳ የሚተፋውን የገማ ንግግር የምተነትንበት ጠባብ ጭንቅላት የለንም፡፡
ከአማራነት ትግላችን ግን ፈቀቅ አንልም፡፡

እንደ ፀሃይ ለአለም የሚያበራው የምኒልክ አምላክ በሰላም ያውላችሁ ።

ቬሮኒካ መላኩ

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.