Breaking News
Home / Amharic / የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም – Leaked News አፈትላኪ ዜናዎች !

የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም – Leaked News አፈትላኪ ዜናዎች !

“የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም…..!”

ዮሃንስ ይባላል።ከሃገሩ ገና በልጅነቱ ነው በደርግ ዘመን የተሰደደው። አባቱ የህክምና ዶክተር እናቱ ደግሞ ጤና ጥበቃ ይሰሩ ነበር። አሜሪካ ሃገር በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተማረ ሲሆን ብሩህ አእምሮ ስለነበረው ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ይገባል።

በኮምፕዩተር ሳይንስ በከፍተኛ ማዕረግ በ1998 የተመረቀ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ብቃቱን በመመልከት የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ኤጄንሲ(NSA NATIONAL SECURTIY AGENCY) የሽብር መከላከል ክፍል ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ ጀመር።

ከዛም እራሱን በትምህርትና ብቃት እያሳደገ ላለፉት 19 አመታት በብዙ የስራ እርከኖች አልፏል። በ2018 አ.ም ከኤጀንሲው ጋር የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ግሉ ዘርፍ በተለይም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ለተለያዩ ኩባንያዎች በአማካሪነት ይሰራል።

እጅግ ታላቁ ዜና እዚህ ጋር ይመጣል።ዮሃንስ(ጆን) ባለፈው ሳምንት ሜሪላንድ አንድ የሰርግ ፕሮግራም ላይ ለጓደኞቹ በሚስጥር መልክ ያወራው ወሬ እጅጉን አነጋጋሪ ሆኗል። ነገሩ እንዲህ ነው።

ዮሃንስ እስከ 2017 በኤጀንሲው በሚሰራበት ወቅት ማንኛውም የስለላና የደንህነት ተቋም ለማህበረሰቡ አስጊ ናቸው የሚላቸውን አጠራጣሪ ግለሰቦች (watch list) ውስጥ ይገባሉ።

ይህም ዝርዝር ከአክራሪነት፣በፅንፈኝነት እንቅስቃሴ ውስጥ አሉ ተብለው በስለላ ሰራተኞች ትንተና(Assessment) የታሰቡ ሰዎች ያሉበት ሲሆን ይህም መረጃ በአሜሪካ ባሉ ሁሉም የደህንነትና ህግ አስከባሪ አካላት (CIA,FBI,Homeland Security,DEA….) ይተላለፋል። እናም በተለይም ዮሃንስ ሲሰራበት በነበረው ክፍል ውስጥ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል (counter terrorism division) አጠራጣሪ ግለሰቦች(watch list) ውስጥ የአንድ ፅንፈኛ ስምን ይመለከታል።

ይህም ሰው ሀጂ ጀዋር መሀመድ ሆኖ ይገኛል። በዝርዝሩ መግለጫ ላይ እንደተመለከውም እንዲህ ይላል።” በአሜሪካ መንግስት በአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ከሚገኘው የግብፁ ሙስሊም ብራዘርሁድ ቁልፍ ሰዎች ጋር የሚያደርጋቸው ሶስተኛ ወገናዊ ግንኙነቶች ና በተለይም ካይሮ ውስጥ በ2015 በሙስሊም ብራዘርሁድ ቢሮ ከተለያዩ ሃላፊዎች ጋር መገናኘቱ በትንተናችን መሰረት A-” ስኬል ውስጥ ገብቷል። ጥብቅ ክትትልም ይደረግበት” ብሎ ፅሁፉ ይናገራል። በትንተና አሰራሩም መሰረት A- ማለት ለአሜሪካ ደህንነት የሚያሰጋና ጥብቅ ክትትል የሚያዝ ስኬል ነው።

እንደ ጀዋር ያሉ በዝርዝር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የሃገራትን ደህንነት የሚፈታተኑና አሜሪካንም የሚያሰጉ ሆነው ከተገኙ በፀረ ሽብር ህግ ሊታሰሩ ይችላሉ።

አፈትላኪ ቀደም ሲል ጃዋር ግብጽ ጋ ያለውን ድብቅ ግንኙነት ማስነበቧ ይታወቃል፤እንዲሁም ጃዋር ከግብጽ በተጨማሪ ከአረብ ሀገራት የሚደረግለትን የብዙ ሚሊዮኖች ብር እገዛ አሜሪካ በዓይነቁራኛ የምትከታተለው ሲሆን በቅርቡም ጠቅላይ ሚ/ር አብይ ከሚድሮክ ጃዋር የተቀበለውን የ5ሚሊዪን ብር ጉርሻ አንስተው ጃዋር ላይ ቢጫ ካርድ እንደመዘዙ ለማወቅ ችለናል፡፡በመሆኑም ይዋል ይደር እንጅ ጃዋር ለፍርድ መቅረቡ አይቀሬ መሆኑን የሊክድ ኒውስ ሁነኛ መረጃ ያትታል፡፡

Check Also

የኮሎኔል አብይ አህመድ አስገራሚ የትምህርት መረጃዎች ! የትኛው ነው ትክክል?

ሻለቃ ውብ አንተን ስሙት።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.