Breaking News
Home / Amharic / አምስት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች አባላቱ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አምስት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች አባላቱ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አምስት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች አባላቱ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ገለፁ።

የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ ዘጠኝ ግለሰቦች በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ቶሌራ አደባ፣ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ዛሬ ማለዳ አመራሮቹ በጋራ ይኖሩበት የነበረው ቤት በፖሊስ የተበረበረ ሲሆን፣ አካባቢውም በፖሊስ ተከብቦ ቆይቷል።

ከዚያም በተለምዶ ሶስተኛ ወደሚባለው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ይገልጻሉ።

• “መንግሥት ጠንከርና መረር ያለ እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል” ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

• “እልም ያለ ሥርዓት አልበኝነት ሊፈጠር ይችላል” ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌ.)

• “በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም” ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሥራ አስፈፃሚ አባላቱ መካከል አቶ አብዲ ረጋሳ እና አቶ ሚካዔል ቦረን የሚገኙ ሲሆን የድርጅቱ የማህበረሰብ ጉባዔ አባል አቶ ኬነሳ አያና፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ያዴ አብዱልሽኩር፣ የዲፕሎማሲ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ እንዲሁም ሁለት ሹፌሮችና ሁለት ጠባቂዎችም ጨምሮ መታሰራቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

አቶ ቶሌራ አክለውም “ዛሬ ማለዳ የአመራሮቹ ቤት መበርበር ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ልናገኛቸው ስላልቻልን የታሰሩበትን ምክንያት አላወቅንም”

አቶ ቶሌራ እንደሚሉት ዛሬ ማለዳ በአባላቶቹና በአመራሮቹ መኖሪያ የተደረገው ብርበራ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዥ የተካሄደ ነው።

እነዚህ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦነግ አመራሮች በጋራ ይኖሩ የነበረው አዲስ አበባ ካራ ቆሬ በሚባል አካባቢ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ቶሌራ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው አካል ማን እንደሆነ እንዳላወቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ደጋግመን ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

ከአንድ ሳምንት በፊት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባወጣው መግለጫ 350 የሚሆኑ አባላቶቹ በአዲስ አበባና፣ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ታፍሰው እንደታሰሩበት አስታውቆ ነበር።

SUPPORT Amhara Movement

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.