Breaking News
Home / Amharic / OMN is sold ! በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ቢሮ ተሸጠ::

OMN is sold ! በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ቢሮ ተሸጠ::

የኦሮሞ ሕዝብ ንብረት ተሽጦ ለጃዋር መንገሻ እየሆነ ነው::
የኦሮሞ ዳያስፖራ መዋጮ ውጤት የሆነው እና በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ቢሮ ተሸጠ::
የኦ.ኤም. ኤን መመስረት ዋና ዓላማው የኦሮሞን ሕዝብ አንደበትና ልሣን ሆኖ እንዲያገለግል ነበር:: በዚህ ረገድ ድርጅቱ በጥቂት ግለሰቦች ፈላጭ ቆራጭነት አድራጊ ፈጣሪነት ጫማ ሥር ቢወድቅም ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል::
ስለዚህ ይህ ሕዝባዊ ድርጅት በተቀደሰ ዓላማው ቀጥሎ በዓለም ላይ ካሉት ተዋቂ ሚድያዎች ተርታ ውስጥ ይገባል ተብሎ ሲጠበቅ : የባላምባራስ ጃዋር መሀመድ የግል ድርጅት እስኪመስል ድረስ ከመንገድ ወጥቶ ርቆ ስለመሄዱ አገርም መንግስትም የሚያውቀው ነው::
ግለሰቡ አያሌ የኦሮሞ ባለሙያዎችን እየገፋ እየገፈተረ ለብቻው ሆኖ እንደ ኤዲተር: እንደ ዳይሬክተር: እንደ ሥራ አስኪያጅ: እንደ ፕሮዳክሽን ማኔጀር : እንደ ሪፖርተር : እንደ ፕሮሞተር: እንደ ፈንድ ሬይዘር : እንደ እንፕሮግራም እንግዳ: እንደ ኮሚንታንተርና እንደ ተንታኝ ሆኖ ሁሉ ቦታ ተቆጣጥሮ ሲፈነጭበትና ሲያፏጭበት ስለነበረ የሚድያ ህልሙ እንዲጨናገፍ መንስኤ ሆኗል :: ግለሰቡ ዛሬ ስሙን እንደ ጭድ ከምሮ ለስልጣን እራሱን እያሯሯጠ ነው ::
ስለዚህ የኦኤምኤን ንብረት ተሽጦ ጃዋርን ለማንገስ እየተደረገ ነው:: ለምን ከተባለ ከጃዋር በስተጀርባ ያለው ቡድን ዕድል ቀንቶት ነገ ኦሮሚያን በእጁ ካስገባ በምዕራብ ኦሮሚያ “የዲዴሳ ማፊያ” በምሥራቅ ኦሮሚያ “የስምጥ ሸለቆ ማፊያ ” በመካከል “የገፈርሳ ማፊያ” ሆኖ ኦሮሚያን ጆፌ አሞራ ሆኖ ለመበጣጠስና ለመቀራመት ያሰፈሰፉ ዶላር አዳኞች ናቸው::
ዛሬ ፕሮፌሰር መረራ ጉድናም በማፊያዎቹ መረብ ውስጥ ገብተዋል :: ልመናው ላይ እንዲያተኩርም ፕሮፌሰሩ የልመና ከረጢታቸውን ይዘው ወደ ላሜቦራው አገር ለመሄድ ተዘጋጅተዋል::
ይህ ዓላማ እንዲሳካ የኦሮሞ ሕዝብ ሠላሙን ማጣት አለበት :: መብቱ መጣስ ይኖርበታል:: ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋራ ያለው ማህበራዊ ቁርኝት ጥርጣሬ ላይ ወድቆ አገሪቷ በማፊያዎች መዳፍ እንድትወድቅ ነው::
የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ ዛሬ ያልታመነልህ ለገንዘብህ ለዓላማህ እና ለህልምህ ኃላፊነት የሌለው እና በገንዘብህ እራሱን ለማንገስ ደፋ ቀና የሚለው ግለሰብ አይታመንምና እራስህን ጠብቅ:: የሚሆነውን ሁሉ በዐይነ ቁራኛ ተከታተል ጭራሮ ለቅመህ ያሳደካቸውን ልጆችህን ለጃዋር መንገሻ ሲባል ደማቸውን እንዲያፈስሱ ጠይወታቸውን እንዲያሳልፉ አታድርግ::

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.