Breaking News
Home / Amharic / HR6600 ትርጉሙ በአማርኛ ይሄ ነው። አንብቡት !

HR6600 ትርጉሙ በአማርኛ ይሄ ነው። አንብቡት !

HR6600 ትርጉሙ ይሄ ነው።

 

117ኛ ምክር ቤት
2ኛ ስብሰባ
HR 6600
 

በኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሠላም እና የዴሞክራሲ ጥረቶችን ለመደገፍ፡፡

………
በተወካዮች ምክር ቤት
ጥር 27፣ 2014 (እ.ኤ.አ. ፌብሪዋሪ 4፣ 2022)
አቶ ማሊኖውስኪ (ራሳቸውን፣ የካሊፎርኒያዋን ወ/ሮ ኪም፣ አቶ ሚክስ እና አቶ ምክካውልን ወክለው) የሚከተለውን የሕግ ረቂቅ
አቅርበዋል፤ ረቂቁ ለውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ እንዲሁም ከዚያ በተጨማሪ ለፍርድ ቤት አካል፣ ለገንዘብ አገልግሎቶች እና ለወታደራዊ
አገልገሎቶች ኮሚቴዎች ተመርቷል፤ የሚመለከተው ኮሚቴ ባለው ሥልጣን ሥር የሚወደቁት የረቂቁ ድንጋጌዎች ለእያንዳንዱ ጉዳይ
የሚታዩበት ጊዜ በቀጣይ በአፈ ጉባኤ የሚወሰን ይሆናል፡፡
……………
የሕግ ረቂቅ
በኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሠላም እና የዴሞክራሲ ጥረቶችን ለመደገፍ፡፡
ይህ በምክር ቤት በተሰበሰቡት የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና የተወካዮች ምክር ቤት ይደንገግ፡፡
ክፍል 1፡ አጭር ርእስ
ይህ ሕግ ‹‹የኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሠላም እና ዴሞክራሲ ሕግ›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
 

ክፍል 2፡ የፖሊሲው መግለጫ

 

የአሜሪካ ፖሊሲ እንደሚከተለው ነው፡-
(1) የኢትዮጵያን የእርስ በእርስ ጦርነት እና ሌሎች ግጭቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉትን በዓለም አቀፍ ደረጃ
እውቅና የተሰጣቸው ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ ዘር
ማጥፋት እና ሌሎች አረመኔያዊ ድርጊቶችን ለማስቆም የሚደረጉ ጥረቶችን መደገፍ፣
(2) በኢትዮጵያ መረጋጋት ለማስፈን እና የኃይል ጥቃትን ለማስቆም የዲፐሎማሲ፣ የልማት እና የሕግ መንገዶችን በሙሉ
መጠቀም፣
(3) በኢትዮጵያ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸው ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣
በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ ዘር ማጥፋት እና ሌሎች አረመኔያዊ ድርጊቶችን የሚፈጸሙ ሰዎችን ተጠያቂ
እንዲሆኑ የሚያደርጉ ጥረቶችን መደገፍ እና
(4) ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማምጣት የሚደረጉ አካታች ብሔራዊ ውይይቶችን

ማበረታታት፡፡

 

ክፍል 3፡ የማረጋጋት ጥረቶችን ሰብዓዊ መብቶችን እና ዴሞክራሲን መደገፊያ ዘዴ (ስትራቴጂ)

 

(ሀ) በአጠቃላይ – ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ አስተዳዳሪ፣ ከገንዘብ መሥሪያ ቤት ኃላፊ (ሴክሬተሪ ኦፍ ዘ ትሬዠሪ) እና
ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፌደራል ክፍሎች እና ኤጀንሲዎች ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀት – የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ
(ሴክሬተሪ ኦፍ ስቴት) የኢትዮጵያን የእርስ በእርስ ጦርነት እና ሌሎች ግጭቶች ለማስቆም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ
እውቅና የተሰጣቸው ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ ዘር ማጥፋት እና
ሌሎች አረመኔያዊ ድርጊቶችን የፈጸሙ ሰዎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን፣ ሰብዓዊ መብቶችን እና
እርቅን ለማበረታታት የሚደረጉ ጥረቶችን የሚደግፍ ዘዴ (ስትራቴጂ) ይቀርጻሉ፡፡
(ለ) አላባውያን – በንዑስ ክፍል (ሀ) ላይ አስፈላጊ መሆኑ የተገለጸው ዘዴ የሚከተሉትን ጨምሮ ዘዴው የሚፈጸምበትን እቅድ ማካተት
አለበት፡-
(1) ከተባበሩት መንግሥታት፣ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአውሮፓ ሕብረት እና ከሌሎች ቀጠናዊ አካላት፣ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ
አጋሮች ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ማዳበር፣
(2) ጽኑ እና አጣዳፊ ሰብዓዊ ቀውስን ለማሸነፍ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሚመለከት መፍትሔ መስጠት፣ (ስደተኞችን፣ በአገር
ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎችን፣ ለጉዳት የተጋለጡ ሰዎችን እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በርስ ጦርነት እና በሌሎች ግጭቶች
ምክንያት በኃይል እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ሰዎችን ጨምሮ) ለጉዳት የተጋለጡ ሰዎች ያልተገደበ ተደራሽነት እና ሰብዓዊ እርዳታ
እንዲያገኙ ማረጋገጥ፣
(3) በኢትዮጵያ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት እና ሌሎች ግጭቶች ለማስቀጠል ወይም ተጽእኖ ለማድረግ የግጭቱ አካል ለሆነ
ማንኛውም ወገን የሚደረገውን የውጭ የቁሳቁስ ድጋፍ ለይቶ ማወቅ እና ማስቆም፣
(4) በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸው ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣
በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ ዘር ማጥፋት እና ሌሎች አረመኔያዊ ድርጊቶች ፍትሕ እና ተጠያቂነትን መደገፍ
እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ማጠናከር፣
(5) እንደ አስፈላጊነቱ ግለሰቦቹን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ድንገተኛ እቅዶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲ
ሠራተኞችን እና የአሜሪካ ዜጋዎችን እንዲሁም የአሜሪካ ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪዎችን ደህንነት እና ጥበቃ ማረጋገጥ፣
(6) የጥላቻ ንግግርን እና የኃይል ጥቃት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮችን መጠቀምን ጨምሮ – ከአሜሪካ ውጭ በሚፈልቁ በኢትዮጵያ
የእርስ በእርስ ጦርነቱ እና ሌሎች ግጭቶች እንዲቀጥሉ በማድረግ ላይ ያተኮሩ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች የሚያደርሱትን ጉዳት
ለመቀነስ ከማህበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች ጋር በኢትዮጵያ ያለውን የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ መዋጋት፣
(7) ሴቶችን እና ወጣቶችን ጨምሮ ትርጉም ባለው መልኩ የሁሉንም ብሔረሰቦች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በማሳተፍ ግጭት
አፈታትን፣ አካታች ውይይትን፣ እርቅን እንዲሁም በኢትዮጵያ ሠላም ለማስፈን እና የኃይል ጥቃትን ለማስቆም የሚደረጉ
ማህበረሰባዊ መሠረት ያላቸው ጥረቶችን መደገፍ፣
(😎 በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነት እና ሌሎች ግጭቶች መንስኤዎችን ትንተና ጨምሮ በኢትዮጵያ በእርስ በእርስ
ጦርነቱ እና በሌሎች ግጭቶች ለተጎዱት ሰዎች የግጭት አፈታትን እና የሰነ ልቦና እንዲሁም ማህበራዊ መልሶ ማቋቋምን
መደገፍ፣
(9) እንደ አስፈላጊነቱ በኢትዮጵያ በእርስ በርስ ጦርነት ጊዜ የተጎዱ ወይም የወደሙ የሕክምና እና ሌሎች ከጤና ጋር የተያያዙ
መሠረተ ልማቶችን ወደነበሩበት የመመለስ ጥረቶችን መደገፍ፣
 
https://www.youtube.com/watch?v=I6UfWf08DEA

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.