Breaking News
Home / Amharic / Disaster of Ethiopian Banking system !

Disaster of Ethiopian Banking system !

የባህርዳሯ ነኝ is feeling angry.
I hate Ethiopian banking system! 

ትላንት ያጋጠመኝን ላጫውታችሁ።

ንግድ ባንክ ገንዘብ ለማውጣትና እግረመንገዴንም ወደ ተለያዮ አካውንቶች ገንዘብ ለመላክ ሄድሁ።ለእጅ ገንዘብ የምፈልገውን ወጪ በሚለው ፎርም ላይ ሞላሁና በዛው ጠጋ ብዬ ዳሸንና አባይ ባንክ ገንዘብ ከመላክ የትኛውን ፎርም ነው መሙላት ያለብኝ ስላት፣”ከእኛ ባንክ ወደ ሌላ ባንክ መላክ አይቻልም” ብላኝ እርፋ! ገርሞኝ ዝም አልሁ።
ምን ላድርግ ብየ ስጠይቃት “ብር አውጥተሽ ገንዘቡን መላክ ወደ ምትፈልጊበት ባንክ በመሄድ ገንዘቡን ማስገባት ትችያለሽ” አለችን። ይታያችሁ ዳሸን ባንክ ለማግኘት ቢያስ የ3 ንግድ ባንኮች ርቀት መጓዝ ያስፈልጋል።ዓባይ ባንክማ ከሆነ ጭራሹን ክፍለ ከተማውን ስታስሱ ልትውሉ ነው፣ያም ሆኖ ላይኖር ደግሞ ይችላል።  ያ ማለት ደግሞ ገንዘብ ተሸክሞ ከአዲስ አበባ ሌባ አድነኝ እያሉ አካባቢውን መዞር ሊያስፈልግ ነው።ይሄ እንግዲህ ከንግድ ባንክ ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ መላክ ሲታሰብ የሚገጥመው ውጣ ውረድ ነው።

ሌላውና አስገራሚውና አስቂኙ ነገር ደግሞ ወደ ራሳቸው (ወደ የንግድ ባንክ) አካውንት ገንዘብ ትራስፈር ለማድግ ያለው አስቂኝ ፕሮሰስ ነው።ገንዘብ የሚላክለትን ሰው ስምና የሂሳብ ቁጥር ፅፌ ለነኝህ ሰዊች ከአካውንቴ ገንዘብ እንዲላክልኝ እፈልጋለሁ ስላት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው!? “መጀመሪያ ከሂሳብሽ ገንዘቡን ዊዝድሮው ካረግሽ በሗላ ነው መላክ ምትችይው!” 
ያ ማለት ሌላ የወጭ ፎርም መሙላትና ወረፋ መጠበቅ ነው። አጋጣሚ ሁኖ ወረፋ የደረሰኝ መጀመሪያ ገንዘብ ያወጣሁበት ዴስክ ስር ከተቀመጠች ልጅ ስለነበረ እሷ ደግሞ “ይቅርታ ቅድም እኔ ጋ ገንዘብ ስላወጣሽ ሁለተኛ ማውጣት አይፈቀድልኝምና ሌሎቹ ጋ ሂጅ”  ተመልከቱ እስቲ ከአንድ ባንክ ውስጥ አንዷ ማድረግ ማይፈቀድላትን ሌላዋ ግን ይፈቀድላታል!? ይሄን ስሰማ ከት ብየ ነው የሳቅኩት (አንጀቴ እያረረ!) የጉድ አገር!
እአንድ ሰው በደቁቃዎች መጨረስ የሚችለውን የገንዘብ ዝውውር ስራ ሆን ብለው ለማራዘም የሚሰሩ ነው ሚመስለው። ከራሴ አካውንት ያለን ብር አወጣሁት አላወጣሁት ልዮነቱ ምንድነው? አይነኗ ያለኝን የገንአብ መጠን ካየ ለምን ቀጥታ ከዚያ በመቀነስ ልልክ ወደፈለግኩበት አካውንት አትልክልኝም!? 
በአንደኛነት ለውጥ የሚታስፈልገው ተቋም ቢኖር ባንክ ነው!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.