Breaking News
Home / Amharic / ለአማራ ምሁራን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የቀረበ ጥሪ !

ለአማራ ምሁራን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የቀረበ ጥሪ !

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ለኢትዮጵያውያን ምሁራን በተለይም ለአማራ ምሁራን የቀረበ ጥሪ 

በ1998 ዓ.ም የተደረገውን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ተከትሎ፣ መንግስት ባወጣው ይፋዊ የቆጠራ ውጤት፣ 2.5 ሚሊየን የሆነ የአማራ ሕዝብ «ጠፍቷል» ተብሎ ለአገራችን ፓርላማ ሪፖርት መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመንግሥት የታመነው እና «ጠፋ» የተባለው የአማራ ሕዝብ ብዛት 2.5 ሚሊየን ሕዝብ እንደሆነ ቢገለፅም፣ እ.ኤ.አ የ1984፣ የ1994 እና የ2007ን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ያጠኑ ምሁራን የታዳጊ አገሮችን የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ፣ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሔረሰቦች የዕድገት ምጣኔ እና አስቀድሞ የነበረውን የአማራ ሕዝብ ቁጥር መሰረት አድርገው በሰሩት ትንታኔ፣ እ.ኤ.አ 2007 (በ1998 ዓ.ም) በተደረገው የሕዝብ እና የቤት ቆጣራ መኖራቸው የተካደው ወይም ንዲጠፉ የተደረጉት አማሮች ቁጥር ከ3.3 ሚሊየን እስከ 6.2 ሚሊየን ሕዝብ እንደሚደርስ አረጋግጠዋል፡፡

በምሁራኑ ጥናት መሰረት ለአብነት የኦሮሞ ሕዝብን የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ 3.8% በመውሰድ ስሌት ብንሰራ በ1998 ዓ.ም የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ውጤት ላይ 6.2 ሚሊየን የአማራ ሕዝብ የሚጎድል ሲሆን፤ የትግራይ ሕዝብን የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ የሆነውን 2.9% መሰረት አድርገን ስሌት ብንሰራ ደግሞ 3.3 ሚሊየን የአማራ ሕዝብ ከ1998 የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ላይ ጎድሏል፡፡ በ6.2 ሚሊየን ጉድለት እና በ3.3 ሚሊዮን ጉድለት መካከል ያለውን አማካኝ ቁጥር እንኳ ብንወስድ በአማካኝ 4.9 ሚሊየን የሆነ የአማራ ሕዝብ በ1998 በተደረገው የሕዝብ እና የቤቱ ቆጠራ የደረሰበት አይታወቅም። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ባለፉት የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ሆን ተብሎ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እና ወንጀሉ ከፊታችን በሚደረገው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ላይ እንዳይደገም ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። የዚህ ሥራ አንዱ ክፍል አውደ ጥናት ማከናወን ሲሆን በሕዝብ እና በቤት ቆጠራ ጉዳይ ጥናት የሰራችሁ ምሁራንን ለማሳተፍ ዕቅድ ይዘናል።

ስለሆነም፦

1. እ.ኤ.አ 1994 እና 2007 በተከናወነው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ጋር በተያያዘ በአማራ ሕዝብ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራን ውጤት መሰረት በማድረግ የመጀመሪያ ዲግሪያችሁን ወይም የማስተርስ ዲግሪያችሁን ማሟያ ወይም የፒ.ኤች.ዲ የጥናት ጽሁፎቻችሁን የሰራችሁ ምሁራንን፣ የጥናት ውጤታችሁን ሶፍት ኮፒ ወይም በደረቅ ኮፒ እንድትልኩልን።

2. እ.ኤ.አ 1994 እና 2007 በተከናወነው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ጋር በተያያዘ በአማራ ሕዝብ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራን ውጤት ላይ ጥናት እና ምርምር ያከናወናችሁ ምሁራን፣ የጥናት ውጤታችሁን በሶፍት ኮፒ ወይም በደረቅ ኮፒ እንድትልኩልን።

3. ከአሁን በፊት የሰራችሁትን የጥናት ጽሁፍ ከ5 እስከ 10 ገጽ አጠቃላችሁበምናዘገጀው አውደ ጥናት ላይ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ወይም ከ 5 እስከ 10 ገፅ የሚደርስ አዲስ የጥናት ጽሁፍ በአውደ ጥናቱ ላይ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ምሁራንን፣ ከዚህ በታች በምናስቀምጠው ስልክ ቁጥር ላይ ባለ የቴሌ ግራም ወይም የዋትስአፕ አድራሻችን የጥናት ጽሁፋችሁን እንድትልኩልን እና እንድታናግሩን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

4. ከዚህ ቀደም ስለተከናወኑት የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ አስመልክቶ መረጃ መስጠት የምትፈልጉ እማሮች፣ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎቻችን እንድታናግሩን ጥሪ እናስተላልፋለን።

አድራሻዎቻችን፦

በአካል ልታገኙን ለምትፈልጉ አዲስ አበባ አራት ኪሎ ግንፍሌ ድልድይ አጠገብ። በአማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያነ ቤኒሻንጉል ባሉ የየዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን።

በኤሌክትሮን ደብዳቤ አድራሻ፦

nama.amhara@gmail.com  or  amhara1@amharaonline.org

ስልክ ቁጥር፦
+251932515390፣
+251918411354፣
+251913866023፣
+251912050271፣
+251921127540 ወይም
+251911757008 ማግኘት ትችላላችሁ።

አማራ በልጆቹ ትግል ታሪኩን ያድሳል !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.