Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ትግል ላይቀለበስ ተጀምሮኣል !

የአማራ ትግል ላይቀለበስ ተጀምሮኣል !

የሆነው ሁሉ ነገር ለመልካም ነው። ከመከራ በስተጀርባ ታላቅ ክብር አለ። ጊዜያዊ ድል ጊዜያዊ ነው ዘላቂ ድልም ዘላቂ ድል ነው። መጓጓት ለ አርቲፊሻል ድል ሳይሆን ለእውነተኛው ድል ነው፤ ጥቁር ህዝብን በቃሚንተ፤ በዘለቄታ ነፃ ያወጣ መንፈስ ጊዜያዊ ዳንኪራ ሊያሰበረግገው የመንፈስ ትጥቁን ሊያስፈታው አያችልም። 
አማራነት መንፈሳዊ ጥበብ ነው። ይህ መንፈሳዊ ጥበብ የሚያሰጋቸው ደግሞ ዘመናቸውን ሁሉ ሰርተውበታል። እኛም አለን እነሱም አሉ። በእኛ ውስጥ ያለው መንፈስ የኩበት ድርድር ስላልሆነ መፍለቁ እያዬዩት ነው። አቅማችን ተፈሪ ስለመሆኑ ሐሤትን በገፍ ይሸልምናል። ለዚህ ነው ከሁለት ሰው ውጪ መጥራት በማይቻልበት አገር እመራለሁ በሚለው በኦህዴድ አንድ ሰው በተነሳ ቁጥር እሚደናበሩት። እኛ መንፈሳችን የሚመነጨው ከጸጋችን እንጂ በቀን ከሚገነባ በሌሊት ከሚፈርስ ሰብዕና አይደለም። 
በእኛ ውስጥ ያለውን ነገር አሳምረን እናውቀዋለን። ችግሩ ይህን ስንገብርበት የኖረነው በሌላ መስመር ስለሆነ ነው። እኛ ለራሳችን መዋለ መንፈሳችን ማዋል ስንጀርም እያዩን ነው። አንድ ነፍስ ታዳጊ ወጣት ምን ያህል የህሊና ብቃት እንዳለው እያዩት ነው። አማራነት የማስተዋል ጥበብ ጥገቱ የላስታ አለት ነው። በምልስት ዋክሽሞችን ይሰቧቸው፤ እነ ዋክሽም ወሰኔ ምን አቅም እነደነበራቸው። ብዙ ነገር የነበራቸው ናቸው። 
ታሪክን ከስሜን ብቃት አውጥቶ የግሬራ ሟተት ማድረግ አይቻልም። ምክንያቱም አለችም የለችም ለምትባለው ኢትዮጵያ መሰረቱ ያነ ነውና። ይህ ያልተገለጠላቸው ከእነቦኮሃራም ጋር ይደልቁ። እኛ ግን ምን እንዳለን፤ ምን እንደምንችል ምንስ ፈጣሪያችን እንደፈቀደልን ስለምናውቅ በተሰጠን ልክ መጥነን መራመድ እንችላለን። ጥጋብ የማይችለው ያልነበረበትን ክብር በድንገት ሲያገኘው ነው።
እነሱ ባልሆኑበት ሆናችሁልን ስላልናቸው አላዋቂ ሳሚ ሆነው እንዲህ ይዝረከረካራሉ። አላውቁትም አማራነት ማለት ሲያጠፉት በ እጥፍ ድርብ ለምቶ እንደሚያድር። አማራነት በርቶ የሚያለቅ ሻማ አይደለም። በእኔ ብቻ ያለውን አቅም መገደብ አያቻላችም አይደለም በሚሊዮንች ያለውን። የተሰጠን ጸጋ አለ። ያን ጸጋችን ስለ እናት አገራችን ስንል አድክመናዋል። አሳስተናዋል። እሷኝ ለማዳን መጀመሪያ ራስን ማዳን ዘግይቶም ቢሆን ገብቶናል። አማራን ጠልቶ ኢትዮጵያ የለችም። የባጀው የ አብይወለማ ዲስኩር እንግዲህ በዚህ ፈተና ውስጥ እንዴት እንደወደቀ እያዬን ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊነትን ለመበወዝ እንደባተለ ተመልከተናል። ማናቸውም ቀውስ የዶመግራፊው ትልም ማሳኪያ ተቋም ነው። 
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ዛሬ በራሳችን ዙሪያ በስክነት፤ በርጋታ፤ በማስተዋል ወደ ተግባር አቅማችን ለመቀዬር መሰናዶ ላይ ነን። ጠ/ሚር ሄኦርድስ አብይ አህመድ አብይ ሲያለቋቸው፤ ክብር ሲሰጧቸው፤ ሲያሞግሷቸው፤ ሲሾሟቸው የባጁትን አሰተውለናል። ሲያቃልሏቸው፤ ሲንቋቸው፤ ሲያጣጥሏቸው የባጁትን የትኛው የማህበረሰብ ልጆች እንደሆኑም አስተውለናል። 
እኔ እሳቸው ከፍ ብለው እንዲታዩ በረቂቅም በይፋም ብዙ በታም ብዙ ደክሜያለሁ እንደሳቸው ደም ቆጠራ ላይ ስላንበርኵኝ። ለ ለእኔ ምቾት የሚሰጠኝ አቅም ነው። አሁን ደግሞ በራሳቸው ጊዜ እንዲህ እንኩት ብለው ደም አስክሯቸው ሲወድቁ ማዬት ድል ነው ለቅኖች፤ ለዬዋሆች። መስሏቸዋል አሁን በጊዜያዊነት ዓለም አቅፍ ማህበረሰቡን አታለው ከጉያቸው ያስገቡ። እኛ የጤፍ ጠላ አይደለንም። እኛ ጣዝማ ነን። 
እኛ ብርቃችን አይደለም ወንበር፤ ሥልጣን፤ ዙፋን፤ ዝና። የተፈጠርንብት ነው። ስለዚህ ብርቅ ለሆነባቸው ለሳቸው እንዲህ ያባትታቸው። ከህግ በላይ ለሆኑ ወጎኖዜ ለሚሏቸው ያላቸውን ትእግስት ለአማራ ልጆች ለምን ለማድረግ እንደተሳናቸው መሰረታቸው ይነገረናል። ክርስትያን የሆኑበት ምክንያት በክርስትና ውስጥ ለመኖር ሳይሆን ለሌላ የታሪክ ግርዶሽ ነው። 
አማራ ላይ የዘመቱት ደግሞ ፈሪ ስለሆኑ ብቻ ነው። ሁሉም ነገር ያባትታቸዋል። መባተት ያቅም ድህነት ነው። አቅም ድሃ ከሆነ ኮሽታው ሁሉ ያስበረግገዋል። እሳቸው አሁን አሸንፌዋለሁ፤ በቁጥጥር ሥር አሰገብቼዋለሁ እያሉ በደም ጽዋ ሰክረዋል። ብዙ ሰው ነው በገፍ የተጨፈጨፈው። ያጨፋጨፉበትም እርስ በእርሱ ነው። አይምሰላቸው እዮር ስለሚለከው ማዕት ግን አላሰቡትም።
ከዋዜማው የሹመታቸው ሌሊልት ጀምሮ ብዙ የሰማይ ታምራት ታይተዋል። ወደፊትም ይቀጥላል። በፍቅር ወስጥ መግደልን ፈጣሪ አልፈጠረም። በፍቅር ውስጥ ሸፍጥን ፈጣሪ አልፈጠረም፤ በፍቅር ወስጥ ቋሳን ፈጣሪ አልፈጠረም። ኢትዮጵያ የምትፈለገው ለቅኝ ግዛት ነው። ለነፃነቷ የተደረገው ታገድሎን መዳፋቸው ውስጥ እንዳስገቡ እና እንደ ቧንቧ ውሃ መዘውር እንደሚቻሉት ያስቡታል። አይምሰላቸው ኢትዮጵያ አምላክ አላት።
በምላጃ ኢትዮጵያ አልተመሰረተችም፤ ኢትዮጵያ አቅም ባለው የላቀ ጥበብ ነው የተገነባችው። ኢትዮጵያም ከወገብ በላይ እና በታች በሸነሸኗት ድውይ መንፈስ አልተበጀችም፤ ኢትዮጵያ ገኃዱን ዓለም እና መንፈሳዊ ዓለም በቅንነት በተካኑ እጬጌዎች የተገነባቸው አገር ናት። ኢትዮጵያ አፈላላሎ ወይንም የሽሮ ተከተክ አይደለችም። ኢትዮጵያ በስከኑ ሊቀ ሊቃውናትት እንዲያውም ወደ ነብይነት በተጠጉ ፆምጸ ጸሎት ሰጊድ ሱባኤ በቅኖች የተገነባች አገር ናት። 
ኢትዮጵያ በሸርና በሸፍጥ ተሸብልላ የተፈጠረች አገር አይደለችም። ኢትዮጵያ መታመንን በአምላካቸውም ወይንም በ አላህ ምርቃት፤ ረድኤት እና በረከት በቃሉ የተፈጠረች አገር ናት። ከአማራ በላይ ለኢትዮጵያ ቀናተኛ አምላክ አላት። ይህን ተጻሮ የሚቆመው ዲያቢሎስ ብቻ ነው። የዲያቢሎስ መጨረሻ ደግሞ ይታወቃል። አማራ ኢትዮጵያ ከማለት በሰተቀር ሌላ የሚወጣለት ሳህ የለውም። ሚሊዮኑ የ አብይወለማን ፎቶን ለጥፎ የጸጋ ስግደት ሲሰግድ ባጅቶ ባሩድ መታዘዙ፤ ካቴና መተዘዙ ፍርድና ዳኝነት የፈጠሪ ስለሆነ ነገ በዬደጁ ሁሉም ይገኛል።
የምወዳችሁ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ከዘመነኞች ጋር ሳይሆን ከእውነት ጋር እንቁም። የቤተ መንግሥት ግብረኛነት ከዛው መጸዳጃ ቤት ነው የሚቀረው። ዕውነት ግን የህሊና ስንቅ ነው። አሁን በአብን ላይ የተቃጣውን ነገር አዳምጫለሁኝ። አያሰደነግጠኝም። ስለምን ነው አማልደነግጠው አቅም የለሹ አብይወለማ ዴሞግራፊን ለመስቀጠል ሽብር ማደራጀት፤ ሽብር መምራት፤ ሽብርን ማቀናበር ቀዳሚ ተግባሩ ስለሆነ የሚጠበቀው ስለመሆኑ አበዝቼ በብሎጌ ሰርቼበታለሁኝ። 
እስከምን ያስኬደዋል የሚለው የሚታይ ይሆናል። በዚህ ውስጥ የምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ አማራን አልባ መንፈሷ ችሎ እንዴት ይህን ግዙፍ ኃለፊነት ልተወጣ እንደምትችል የቤት ሥራውን ለሷ እተወዋለሁኝ። ዕውነት የሞግድ ልዩነት አይደለም። እውነት የፈጣሪው ጥበብ ነውና። 
ውዶቼ አትዘኑ፣ አትረባቡሹ፣ አትርበትበቱ፣ አትደንግጡ፣ በጽናት ውስጥ ድል፤ በድል ውስጥ ደግሞ ዘላቂ መኖር ይገኛል። ማልቀስም፤ ማዘንም አይገባም። 
ጦርነቱ የተከፈተበት ቦታ ስለምን እንደተመረጠ ህሊና ላለው ሰው ሆኖ ለተፈጠረ በቂ ግብረ ምላሽ ይሰጣል። አዋሳ ላይ አመራሩ ተደብድቧል። ድሬ፤ ጅጅጋ ላይ የሆነውን አይተናል። አማራ ላይ ግንቦት 7 የሚባል በክፉ ቀን የተፈጠረ ድርጅት የጸነሰው ጽንስ አለቀን ብሎ አማራን ዋጋ አሁን እያስከፈለ ይገኛል። 
የሚፈለገው አማራ መሬት ላይ የአማራ ሊሂቃን ተወዳዳሪ ሆኖው እንዲወጡ ሳይሆን የግንቦት 7 ምልምሎች ተመራጭ እንዲሆኑ ነው። የኢትዮ ኤርትራ የስምምነት አስኳል ይኽው ነው። አሁን ብአዴን ወደ ግንቦት 7 ለማዛወር ያለውን ሽግግር በፈቀዱ እና ባልፈቀዱ ማህል ነው ጦርነቱ የተነሳው። ለዚህም ነው ባለፈው ብአዴን ከመክሰሙ ዋዜማ በነበረው የ ኢህዴግ ሥ/አ/ ዋዜማ የግንቦት 7 አጀንዳ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ይዞ እንዲገባ የተደረገው። አማራ ክልል ከ ኢህዴግ ውጪ ሹመት ተሰጠው የሚባለውም የግንቦት 7 ጠረን ያለበት ነፍስ ብቻ ነው። 
ስለሆነም የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽነሩ የማንን ተልዕኮ ለማሳካት እንደ ተመደቡ ልብ ያለን ሰዎች እናውቃለን። ለጊዜው ተሳክቷል። ብርሌ ከነቃ ግን አይሆን ዕቃ ነው። መንፈሳችን ጫካ ገብቷል። ጫካው ግን እንደነሱ በባሩድ ሳይሆን በሃሳብ ልቅና፤ በእውነት ማህደር እንሞግታለን። አንዱም ነገር እውነት የለበትም። እውነት ያለውማ ምልዕትን አንደበት ዘግቶ በራሱ ቧንባ ብቻ ተንፍሱ አይልም ነበር። እውነት ከጠ/ሚር ሄሮድስ አብይወለማ ቤት የለም። ለዴግራፊ ፍለስፍና እናሟሟታለን ያሉትን ለመፈጸም መንገድ ያሉትን ሁሉ አድርገዋል። 
ውሸት ገበር ስሌለው ንፋሱ ራሱ ነገ ይገልጠዋል። ለዚህ ያደሩ የ እብለት አጋፋሪዎችም በቁማቸው እዬሞቱ ሲኖሩ የሚታዩ ይሆናል። ሌላው ግን ህወሃት ሊመጠባህ ነውና ለውጡ ደግፍ ግን የማያዋጣ መንግድ ነው። 100 ሺህ ህዝብ ለተፈናቀለ፤ ቅርሱ ለተቃጠለ፤ 44ሺህ ልጆቹ ከትምህርት ገባት ለተገለሉ፤ በሺህ የሚቆጠሩ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለተጉላሉ ዛሩ ደግሞ ጭፍጨፋ ለሚካሄደብት ህዝብ ለውጥ ሳይሆን ምጽዕት ነው። ውስጡም እሾሕ ነው። ስለዚህ ባለን አቅም ሁሉ ተቋቁመን ስሜን ጠል ፖለቲካን መልክ ለማስያዝ እንተጋለን። የ ኢንፈሬሪቲ ኮንፕሌክሱ ምንጩ ያነ ነውና። 
አሁን እዬጨፈጨፈ ያለው ዓለምን እያወናበደ ያለው ኦህዴድ ነው። ተደማጩ እሱ እንጂ ህወሃት አይደለም። ስለዚህ አጥብቀን እንሞግተዋለን ኦዴፓ ኦህዴድን፤ በሃሳብም እንፋለመዋለን። ምርኮኛው አቶ አባ ዱላ ገመዳን እና ጄ/ ብርኃኑ ጁላ፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ አቶ ሌንጮ ለታ በጃዋራዊው መርህ ይምራኝ ያለ መቀጠል ይችላል።
ስለሆነም የኦሮሞ የመስፋፋት ሂደት በአጭሩ እንዲቀጭም እንተጋለን። ምክንያቱም አማራ ሰፊ ህዝብ ስለሆነ ነው ሊጨርሱት ያልቻሉት ትንንሾችን በቀላሉ መዋጥ ይቻላቸዋል ልክ እንደ ጌዴኦ። ይህን ደግሞ ደቡብ ላይ እዬሰሩበት ነው። ሱማሌ ላይም ሰርተውበታል። ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ነቅለው ወደ አዲስ አባባ ሲያመጡ ከክልሉ ከባህሉ፤ ከሥነ ልቦናው፤ ከወጉ እና ከልማዱ ለማውጣት ነውና። ስለዚህ በቃን የኦነግ የመስፋፋት ስካር እንላለን! 
አይዞን እንበርታ። ተስፋ ፊት ለፊት አለ። ለፊት ለፊቱ ተስፋ ግን ጽናት፤ ብርታት፤ ጥንካሬ፤ አንድነት ያስፈልጋናል። አማራነት ግማድ ነው። ግማድ ግን ጽናት ኃይል እና ድህነት ነው። ኢትዮጵያም በግርዶሽ ህምም ያልወደዷት፤ ያላቀረቧት አቀረብናት፤ ያላሰቡላት አሰብንላት የሚሏትን አራግፋ እራሷን ነጻ ታወጣለች እንደ ቀደመው። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና። በ አማራ ላይ የባጀውን እሰቡት? ያነን መርምሩት? ያነን አጥኑት? ከህግ በላይ ሆኖ እንክብካቤ ሚደረግለትን የ ኦነግን መንፈስ እዬት፤ መርምሩት አስተውሉት? ዕውነትን ከቦታው ነጥሮ ታገኙታለችሁ።
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል። 
ኑሩልኝ! መሸቢያ ሰንበት።

 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.