የአማራ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ እየተጧጧፈ ነው። አክሲዮኑ የሚሸጥባቸው አንዳንድ የባንክ ቅርንጫፎች ከመደበኛ ሥራቸው ይልቅ አክሲዮን መሸጥ ፋታ ነስቷቸዋል።
የውጭ አገር ዜጎችም አክሲዮን እንዴት መግዛት እንደሚችሉ እየጠየቁ ነው። እኔን ብቻ ሁለት የውጭ ዜጎች በተገኘው ቀዳዳ አክሲዮን እንዴት መግዛት እንደሚችሉ ጠይቀውኛል። ለዚያውም እያንዳንዳቸው ወደ 50 ሚሊዮን ብር በማውጣት አክሲዮን ለመግዛት ነው ፍላጎታቸው። ዜግነት እስከ መቀየርም ድረስ የቆረጡ ፈረንጆች ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሌሎች የውጭ ዜጎች በፋይናንስ ኩባንያዎች (ባንክ፣ ኢንሹራንስ…) መሳተፍ እንደማይችሉ ይታወቃል። ነጮቹ እንኳን ሳይቀሩ አዋጭና አትራፊነቱን ተረድተው አክሲዮን ለመግዛት እየቋመጡ ነው።
ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ አክሲዮን ግዙ። ሌሎች ባለሃብቶችም ጭምር። በዚህ አካሄዱ በፍጥነት አክሲዮን ሽጦ ሊጨርስ ይችላል።
By: Wubshet Mulat