ከሳሙኤል ሃይሉ
የአብይ ትዕግስት እና ጥሎ ያለፋቸው ጥቁር ነጥቦች….
………ሁለት መንግሥት አለ እያለ ሕገወጥነትን በሚያበረታታ እና ሕዝብ መንግሥት ላይ ያለውን እምነት የሚሸረሽር ቅስቀሳ የሚያደርገው ጃዋር መሐመድ በተባለ ፅንፈኛ አክቲቪስት እና የጽንፈኞች መሪ ላይ የታየው ከልክ ያለፈ ትዕግስት ከዋነኞቹ ጥቁር ነጥቦች አንዱ ነው ፣
………የቡራዩ የዘር ጭፍጨፋን እና ጉዳዩን በይፋ ያቀናበረው ፀጋዬ አራርሳ የተባለ ፅንፈኛ አክቲቪስትን ዛሬም ድረስ ሽፋን በሚሰጠው OMN ፣ የሻሸመኔ ዘግናኝ ዘቅዝቆ የመስቀል የአደባባይ ግድያ ፣ በባሌ ፍርድ ቤት ደጃፍ ላይ ገጀራ እና አጠና ይዞ የፍትህ ሥርዓቱ ላይ እምነት በሚያሳጣ እና ሕዝቡን የሚያሸብር የጎረምሳ ስብስብ ላይ አብይ ያሳየው ሕግ ያለማስከበር ግዴለሽነት ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም ፣
……….የረገጡትን መሬት በሙሉ የግል ንብረት ለማድረግና ለመዝረፍ ሁሉም የኔ በሚል ቅስቀሳ በመነዳት አዲስ አበባ ወሎ ድሬዳዋ ኬኛ በማለት የሕዝብ ሰላም ከሚያናጉ ግለሰቦች ፣ ዜጎችን ሰፋሪ እያሉ የመኖር ዋስትና ለማሳጣት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር ተባባሪ በመሆን ያወጣው ድርጅታዊ መግለጫ እና ያሳየው ሃላፊነት የጎደለው አሳፋሪ ተግባር ገራሚ ነበር ፣
………ቋንቋህን ከማይናገር ዕቃ አትግዛ እያለ በመቀስቅስ ሕዝብ ከሕዝብ የሚለያይ እና የሚያጋጭ የሃገሪቱን ህገመንግስት የሚፃረር የጥላቻ ቅስቀሳ በተደጋጋሚ የሚያደርገው አቶ በቀለ ገርባ የተባለ የቋንቋ መምህር ላይ የሚታየው ዝምታ ተጨማሪ ጥቁር ነጥብ የጣለ ነበር ፣
………የአስመጪና ላኪ ፈቃድ ኦሮሞ ለሆኑ በብዛት እንዲሰጥ ፖሊሲ መቀረጽ አለበት እያለ ቅስቀሳ በማድረግ በህዝቦች መሐከል መቃቃር እና ግጭት የሚያነሳሳ ዶክተር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኜ የተባለ አደገኛ ፅንፈኛን የሀገር አምባሳደር አድርጎ በመሾም የታየው ተግባር ለሕዝብ ያለን ንቀት በይፋ ያሳየ ነጥብ ነው ፣
……..ክልል መንግሥታት ሀገር ለመሆን የቀራቸው የዓለም መንግሥታት እውቅና ብቻ ነው እያለ በህዝቦች መሐከል ልዩነትን የሚገፋፋ እና የሕዝብ ሰላም እና ፀጥታ የሚያደፈርስ ተግባር ላይ ዘወትር የሚሳተፈው ሕዝቅኤል ጋቢሳ የተባለ ምሁርን ዝም ማለት ትርጉሙ ኦሮሞ ስትሆን እንዳሻህ መሆን ትችላለህ ማለት ሆኖ አልፏል ፣
……..ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መብት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የሚንቀሳቀሰው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የምክር ቤቱ አባላት ላይ በተቀናጀ መልኩ እየተካሄደ ያለው የመብት ገፈፋ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣እስር፣ የፈጠራ ክስ እና ማዋከብ በአብይ የይፋ ጦርነት አዋጅ የመመራቱ ሚስጥር እና ለፅንፈኞች ሽፋን እና ድጋፍ የመስጠት ፖለቲካዊ አሻጥር እና መንግሥታዊ አድልኦ መቼም ከማይረሱ የአብይ ጉልህ ጥቁር ነጥቦች አንዱ ነው ፣
……..የአማራን አቅም ለማዳከም እና ከተቻለም ለማጥፋት በጽንፈኞች እየተካሄደ ላለው ዘመቻ መሣሪያ በመሆን የሃገሪቱን የፀጥታ እና ደህንነት ሃይል በመጠቀም አማሮችን ማፈናቀል ፣ ማሰር እና ማዋከብ ፣
……..የመንግሥት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች እና የልማት ተቋማት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እና የስራ ቅጥር ፣ የንግድ እና በአጠቃላይ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ወታደራዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በአንድ ብሔር የበላይነት ለማስያዝ ውስጥ ውስጡን የሚሰራው ድምፅ ያጠፋ አካሄድ
………በሀገሪቱ ሕዝብ እየገደሉ እያፈናቀሉ ፣ 17 ባንክ ውስጥ በቢሊዮን ብሮች እየዘረፉ ፣ በይፋ የጦር ሃይል የታጠቁ እና ማሰልጠኛ አቋቁሞ የሚንቀሳቀስ የኦነግ አንጃዎች የፈፀሙትን ከባድ ወንጀል ያለፍርድ ቤት ውሳኔ ከተጠያቂነት ነፃ በማድረግ በእርቅ ስም የተደረገው አሳፋሪ ተግባር ፣
………በየጊዜው ሀገሪቱ ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች ከተገደሉ በኋላ የግድያ ወንጀሉ ምርመራ ተድበስብሶ የሚቀርበት ድራማዊ ተግባር ጉድ እያሰኙ ካሉ ነጥቦች የሚጠቀስ ነው ፣
………በቡራዩ ዘር ለይተው ጭፍጨፋ ያደረጉ አካላትን ለህግ ከማቅረብ ይልቅ ድርጊቱን ለመቃወም የወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ ሰብስቦ በማሰር በበረሃ እስር ቤት እንዲሰቃዩ የተደረገበት ሁኔታ አብይን በጥርጣሬ መዝገብ ያሰፈረ ድርጊት ነበር ፣
………ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ እያንዣበበ ያለው አደጋ ፣ በጋዜጠኞች ላይ እየተፈፀመ ያለው እስር እና ወከባ የአብይ መንግሥት በዚህ ፍጥነት እንዲህ ፍፁም አምባገነን ይሆናል ተብሎ ያልታሰበ ክስተት ሆኗል፣
ከላይ ለተጠቃቀሱት አሳዛኝ እና አሳፋሪ ሁኔታዎች አብይን የዳረገው እውነታ ምናልባት ጫፍ የረገጡ የኦሮሞ ፅንፈኞችን እብደት ለማስታመም የሄደበት ከሕግ እና ከመርህ ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ እንደነበር መገመት ይቻላል። ከሀገራዊ ችግኝ ተከላ ፣ ከጽዳት ፣ ከኤርትራ ጋር የተፈጠረ ሰላም፣ የሱዳን እርቅ ፣ ሕወሓት-ኢህአዴግ የፈፀማቸው ጥፋቶችን ለማረም የተወሰዱ በርካታ የማስተካከያ እርምጃዎች ፣ የቤተመንግስት እድሳት ፣ የሀይለሥላሴ ሐውልት ፣ የዳያስፖራ በነፃነት መግባት መውጣት ያሉ ብዙ መልካም የሰራቸው ስራዎች የመኖራቸውን ያህል ብዙ የማይረሱ እና በትዝብት መዝገብ ላይ በቋሚነት የሰፈሩ ጥቁር ነጥቦችም የአብይ መንግሥት የታሪክ አካል ሆነዋል። ከተጨማሪ ጥቁር ነጥብ እንዲጠበቅ እየመከርኩ እና እየፀለይኩ በዚሁ ላብቃ።
ሃሳብ ካላችሁ በ comment ፃፉልኝ.