Breaking News
Home / News / ዶር አምባቸው ማብራሪያ አንዲሰጡ ወይም ይቅርታ አንዲጠይቁ ተጠይቀዋል !

ዶር አምባቸው ማብራሪያ አንዲሰጡ ወይም ይቅርታ አንዲጠይቁ ተጠይቀዋል !

https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/videos/2302909383064331/?t=13

9 comments

  1. እኛ አማሮች አምባቸው በአምቦ አውርዶን መብታችንን ለኦነግ አሳልፎ ሠጥቶ፣ ለአማራ ሳይሆን ለኦሮሞ ልዩ ጥቅም እታገላለሁ እያለ የሚቀላምደውን በተቃውሞ የማንጠይቅበት ምን ምክንያት አለ? ብአዴን መወገድ አለበት። እንዴት ለኦሮሞ የበላይነት እታገላለሁ ይላል? ይሄ ግለሠብ የትኛውን ህዝብ ነው የሚመራው? አማራስ ከሌሎቹ ህዝቦች ምን ይማራል እስከመቼ ነው እሽሩሩ የምንለው ብአዴንን?

  2. በዶክተር አምባቸዉ ላይ እየተሰጠ ያለዉ ትችት ትንሽ ተጋነነ በተነሳው ሀሳብ ላይ እስማማለሁ። የራሳችን ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ትችት ማውረድ ተገቢ አይደለም። ነገር ግን ዶ/ር አምባቸው ጥያቄውን የመለሰበት መንገድ ብልጠት የጎደለው ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

    አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅምን ነተመለከተ “ኦሮሞ በራሱ ጥረት ሰርቶ መብላት የሚችል ጀግና፣ ሌሎችን አቅፎ የሚይዝ ደግ ሆኖ እያለ ከሌላው የሀገሪቱ ሕዝብ ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ የሚፈልጉ ኃይሎች (ህወሃት መከረኛዋ) ካስቀመጡለት ወጥመድ አንዱ ልዩ ጥቅም የሚባለው ሴራ ነው። ከተማዋ ስትሰፋ በአካባቢው የሚኖር ኦሮሞ አርሶ አደር የበለጠ ተጠቃሚ መሆን ሲገባው በተቃራኒ ተጎጅ ሆኗል። ይህን መታገል ደግሞ ለኦሮሞው ብቻ የምንተወው ጉዳይ አይደለም፤ የአማራ ሕዝብና መንግስት ከጎናችሁ ይቆማል። የኦሮሞ ጉዳት የአማራም ጉዳት ነው። ልዩ ተጠቃሚ ነህ እያሉ ልዩ ተጎጅ ያደረጉትን አርሶ አደር ወገናችን መንግስት እንዲክሰው በርትተን …” ዓይነት ወሬ ቀደድ ቢያደርግላቸው እግሩን ስመው ይሸኙት ነበር።

    ቢሆንም ግን ጫፍ የወጣ ትችት አይጠቅመንም፤ አዴፓና ዶ/ር አምባቸው እንዲማሩበት ወቀሳ ካቀረብን ይበቃል ብዬ አስባለሁ።

  3. አዲስ አበባ የፖለቲካ ቁሌታችሁ ማጣፈጫ አደለችም። አዲስ አበባ ሰው አላት። ነዋሪ አላት። አዲስ አበባ ድንጋይ ወንዝና ሜዳ አደለችም። የኔ የኛ ልትሏት አትችሉም። ማናችሁም ብትሆኑ ሲቸግራችሁ የምትሸጧት ስትፈልጉ የምትገዟት አደለችም። ራሷን በርሷ ማስተዳደር ያለባት ከተማችን ናት። አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት ስንል የአማራ ናት እያልን እንዳልሆነ ይታወቅ። አዲስ አበባ አዲስ አበባ ናት። አማራም አይደለች፤ኦሮሞም አይደለችም። እናም አምባቸው የተባለ ሰው የአዲስ አበባ ጉዳይ ወደሰማይ “ተጓጓለ” “ጓጎለ” እያለ፤ሞቀ ሲለው አምቦ ላይ በ”ልዩ ጥቅም” የሚሸጣት ከተማ አደለችም።

  4. Ambachew said he will fight for the rights of oromo over addis abeba in accordance with the constitution. in the first place this constitution was created by tplf and olf to benefit their own groups. using the constitution they drafted tplf and olf have taken large tracts of land which do not belong to their group into the new killil they created for themslelves.
    on the other hand , amhara is a victim of this constitution, it is a constitution aimed at destroying the amhara. over the last 27 years amhara have been massacred en mass, displaced and evicted , the amhara lands were annexed , and some even given to sudan.
    NAMA should work to correct the wrongs that were done against the amhara. Enough is enough. we have to stand up together to restore our place in the country, By working with all peace loving people of ethiopia we must work for equality , democracy and justice at a national level.
    Ambachew has changed ANDM from being tplf servant to servant of opdo. this is shamefull and a disgrace. it is becoming clear that ANDM cannot lead the amhara people, despite the change of name it has taken. In the coming election, we have a chance to remove these stooges once and for all .

  5. የዶክተር አምባችው ንግግር ሁሉን የአማራ ህዝብ ሊያሳዝን የሚገባ የክህደት ንግግር ነው። ስልጣኑን ያገኘው የአምራ ህዝብ መርጦት ወይም ብቃት ኖሮት ሳይሆን በአመለካከቱ የአብይን መንገስት ስለሚዳገፍ ነው። የስልጣን ጥም ስላለው ወደ ሰልጣን ለመውጣት የአማራን ህዝብ መወጣጫ መሰላል አድርጎ ተጠቅሞበታል። የአማር ህዝብ ንቅናቄ ይህንን በማዎቅ ለወደፊት ትግሉ በአርቆ አሳቢነት መዘጋጀት አለበት። የአማራ ህዝብ ገና ብዙ ፈተና ወደፊት ይገጥመዋል። የአማራ ህዝብ በአራቱም መአዘን በአማራ ላይ ጥላቻ ባላቸው ተከቧል። ከውስጥ ደግሞ እንደ አምባቸው ያለ ከሃዲዎች አሉበት ።

  6. DR. Ambachew,

    እስኪ የትኛውን የአማራ ጥያቄዎችን ነው የመለሳችሁት?
    1. አማራን በጠላትነት የፈረጀው እና ሀገር አልባ ያደረገው ህገ ትህነግ/ኦነግ እንዲቀየር ተጠይቆ ነበር፣
    2. ህዝባችን በየ ቦታው እየሞተ እና እየተፈናቀለ ነው (ወልቃይት፣ ራያ፣ ከሚሴ፣ አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ምንጃር፣ መተከል፣ ሰገን ዞን አማሮ ወረዳ ወዘተርፈ)፣
    3. የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ/ልዩ ጥቅም ጉዳይ አማራን ያላማከለ በአንድ ብርሌ ጠጅ አሳልፋችሁ ሰጥታችኋል፣
    4. አማራ በስልጣን እንዲገፋ ተደርጓል በተለይ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ እንዲሁም በሀገር መከላከያ አካባቢ፣
    5. የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሲካሄድ አማራን ተጠቃሚ እና ዘላቂ መፍትሄ ከማስቀመጥ ይልቅ ድግስ በልታችሁ ትለያያላችሁ ከዚህ ይልቅ ለምሳሌ በኦሮሚያ ክልል ለሚኖረው ህዝባችን አማርኛ ቋንቋ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዲሆን እንዲሁም ውክልና እንዲያገኙ ስምምነቶችን ማድረግ ይገባ ነበር
    6. ክልሉ በኢኮኖሚ ወደኋላ የቀረ ስለሆነ የፈዴራል መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው ግፊት ማድረግ ነበረበት፣
    7. የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቻችን ተገቢውን እንክብካቤ አለማድረግ (ጣናን የወረረ እንቦጭ፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ባርካችን ቃጠሎ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን እድሳት እና ሌሎችም)
    ወዘተርፈ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.