የስልጣኑ ነገር!!
የነጻ አውጪ ልጅ ነጻ አውጪ ይሆናል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ የአንድነት መሰረቱ የሸዋ አማራ ኢትዮጵያን ነጻ ያወጣታል። የነገስታት ሐገር ሸዋ ፣ የመኳንንት ሐገር ሸዋ ፣ የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ነው።
አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ነገስታቶች መሰረታቸው ሸዋ ነው። ለምሳሌ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት በ960 አ ም በዮዲት ጉዲት ከወደቀ በኋላ ስልጣኑን የዛግዌ ስርዎ በ1000 አ ም ተቆጣጠረ። የወደቀውን የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት ከ310 አ ም በኋላ በ1270 አ ም መልሰው ያቋቋሙት አጼ ይኮኖ አምላክ መሰረታቸው እና ትውልዳቸው በቡልጋ አውራጃ በሸዋ ክፍለ ሐገር ነው። አጼ ይኮኖ አምላክ የዛግዌን ስርዎ መንግስት በ1270 አ ም ገልበጠው ሞዓ አንብሣ ዘ ምነገደ ይሁዳ ብለው ከመሰረቱ በኋላ የሐበሻ ታሪክ በጽኑ አለት ላይ ተመሰረተ።
ሙሉ ሸዋ መሰረቱ አማራ ነው። የዛሬው የሸዋ ኦሮሞ እየተባለ የሚጠራው ኦሮማይዝድ (Oromized) የሆነ ነገዱ አማራ የሆነ ህዝብ ነው። ሸዋ ውስጥ ኦሮሞ የሚባል ብሔር የለም። የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሸዋ ኦሮሞ ታሪኩን እየመረመረ አማራ መሆኑን ይረዳዋል።
የሸዋ ህዝብ የአለም ህገ- መንግስት ፈጣሪ እና የእኩለነት ፍልስፍና መስራች ነው። ለምሳሌ የታላቁ ንጉስ የአጼ ምኒልክ ህገ መንግስት ብንመለከት በዛን ዘመን የሰው ልጅ እኩልነትን መሰረት ያደረገ ሰው በሰውነቱ እንጂ በሀብቱ አይከበርም የሚለው አባባል የአጼ ምኒልክ ቃል ነው ።
ሸዋ የኢትዮጵያን መሪ በቅርቡ ትወልዳለች። የሸዋው ንጉስ ኃይለ መለኮት የሸዋ ንጉስ ሆነው በሚያስተዳድሩበት ጊዜ አንድ ቀን ህልም እዩ ፣ ህልማቸውም የልጃቸው ጥላ(shadow) ከራሳቸው ጥላ(shadow) በልጦ ያዩታል። አሽክሮቻቸውን ጠርተው ህልማቸውን የሚፈታ ሰው እንዲያቀርቡላቸው አዝዘው አንድ መነኩሴ ቀረቦ ህልማቸውን ፈታላቸው ። የህልማቸው ፍቺ ሲተረጎም ልጃቸው ከሳቸው የበለጠ ሐገር እንደሚያስተዳደሩ ነገሯቸው። ያን ጊዜ የልጃቸውን ስም ምኒልክ (ሸዋ ምን ይልክ) በለው አወጡለት ይባላል ።
በመሰረቱ የአጼ ምኒልክ አመጣጥ ከናታቸው ጀምሮ ታሪካዊ ነው። እናታቸው የአጴ ምኒልክ የአያታቸው የንጉስ ሣህለስላሴ ገረድ ነበሩ እና አንድ ቀን በህልማቸው እትኔ ላይ ጸሐይ ወጥቶብኝ አየሁ ብለው ተነግረዋል ይባላል።
ወደ ዋንው ቁም ነገር ስመጣ የኢትዮጵያ የአንድነት መሰረት የሆነችው ሸዋ በድንገት መሪዋን ትወልዳለች ለማለት ነው።
የሸዋ ህዝብ በዘር ያልተከፋፈለ ነገደ አማራ ሲሆን ሸዋ የኢትየያ ዋልታ እና ማገር ለመሆኑ ታሪክ ምስክር ነው ።