Home / Amharic / የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብ የኅልውና ጥያቄዎች 6 አበይት ጉዳዮች
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብ የኅልውና ጥያቄዎች 6 አበይት ጉዳዮች
ትኩረታችን ሁሉ ዋኖች ላይ ይሁን!
(ገብርዬ)
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የአማራ ሕዝብ የኅልውና ጥያቄዎች ናቸው ብሎ የለያቸው 6 አበይት ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው።
1) የአማራ ሕዝብ ያልተሳተፈበት፥ ይሁንታውንም ያልሰጠበትና በአማራ ጠል ኃይሎች ተደርሶ ሕገመንግሥት የተባለው ሰነድ የሁሉንም ሕዝቦችና ዜጎች ዘላቂ ጥቅም፣ መብትና ፍላጎት ባስከበረ መልኩ እንዲሻሻል/እንዲከለስ ማድረግ፤
2) የአማራን ሕዝባዊና ግዛታዊ አንድነትና ኢተነጣጣይነት ተፈጥሯዊ መብት ማስከበር፤
3) ሕዝባችን በመልማት ፀጋውና ለአገር ልማትም በአበረክተው አስተዋፅዖ ልክ የሚኖረውን ፍትኃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
4) ሕዝባችን በቁመቱና ወርዱ ልክ በሁለንተናዊ አገራዊ ተሳትፎ እንዲወከል ማድረግ፤
5) በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚኖረው ወገናችን የዜግነት መብቱ እንዲጠበቅለት፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲከበር እንዲሁም ማንነቱንና የማንነት መገለጫዎቹን የማበልፀግ መብቱ እንዲጠበቅለት ማስቻል፤
6) ባለፉት የእልቂት ዓመታት የዘር ማጥፋትን ጨምሮ በሕዝባችን ላይ ለደረሱ በደሎች ይፋዊ መንግስታዊ ይቅርታ ተጠይቆ፥ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈል ማድረግ፤
የሚሉ ናቸው።
የግርጌ ማስታዎሻ፦
አብን ለአማራው ሕዝብ የሚመኛቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ሳይሸራረፉ እንኳንስና ለኢትዮጵያውያን ወንድሞች ለመላው የሰው ዘር ሁሉ እንዲዳረሱ ምኞቱ ነው። በተለይም በአገራችን ፍትኃዊነትና እኩልነት ያለገደብና ወገንተኝነት ለሁሉም ዜጎች ይሰፍኑ ዘንድ በጽናት ይታገላል።
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.