Breaking News
Home / Amharic / አብን ታፍነው የታሰሩ ሰላማዊ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ያሳስባል።

አብን ታፍነው የታሰሩ ሰላማዊ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ያሳስባል።

*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ትናንት መጋቢት 01/2011 ዓ/ም በጋዜጠኛና ሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ አዘጋጅነት የተጠራውን ስብሰባ ታድመው በሰላም ወደየቤታቸው ሲመለሱ በፖሊስ ተደብድበውና ታፍነው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ያሳስባል። ዜጎች የመረጡትን ሃሳብ በሰላማዊ መንገድ የመግለፅ መብታቸው ገደብ የማይጣልበት መሆኑንም ንቅናቄያችን ያስገነዝባል።

በዚህ አጋጣሚ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሳቸው ጉዳይ ላይ ራሳቸው ወሳኝ የሚሆኑባቸውን አማራጮች ለመምከር ያደረጉትንና ለወደፊትም የሚያደርጉትን ውይይትና ትግል፤ ኦዴፓ መራሽ የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሚያደርጓቸው ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችና በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ ተንኳሽ ቡድኖች ላይ ያሰሙትን ተቃውሞ፤ አዲስ አበባ በሕገወጥ ከንቲባና ካቢኔ መመራቷን በመቃወም ያሰሙትን ተቃውሞ እንዲሁም የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ ሆነ ብሎ ለማዛባት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኩል የተደረገውን በመቶ ሺሆዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለፈቃዳቸው በማስገደድ በሕገወጥ መንገድ ማስፈር ላይ ያነሱትን የበረታ ነቀፋ፥ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚደግፍ መሆኑን ይገልፃል።

Check Also

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት ሐሰተኛ መረጃ !

አማኑኤል ይልቃል የሥራ ድርሻ,ቢቢሲ አማርኛ ዘገባው ከናይሮቢ ከ 8 ሰአት በፊት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም …

ኢትዮጵያዉያን የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ፈንቅለው ገብተው ተቃውሞ አሰሙ !

Ethiopians protest against Abiy Ahmed in Geneva Switzerland!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.