Breaking News
Home / Amharic / የአማራዉን የህልዉና ትግል ሊታደጉ የሚችሉ ማስጠንቀቂያዎች ! ሻለቃ ዳዊት

የአማራዉን የህልዉና ትግል ሊታደጉ የሚችሉ ማስጠንቀቂያዎች ! ሻለቃ ዳዊት

የአማራውን የህልውና ትግል ሊታደጉ የሚችሉ ማስጠንቀቂያዎች

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማስጠንቀቂያዎችን በማጤን፣ የአማራ ህዝብን እና ጠቅላላ አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ እያንዳንዱ የፋኖ አባልና መሪዎች ተረድተው፣ አካሄድን ማስተካከያ ጊዜው አሁን ነው። ፋኖቻችን ለአማራ ሕልውና ታሪካዊ መስዋእትነት እያስመዘገቡ ነው። ትግሉን እዚህ ስላደረሱት የአማራ ሕዝብ ታላቅ ባለውለታ ናችው። ይህን የመሰለ ውጊያ በቅርብ ታሪካችን ስላልነበረና፣ ከራሳችን የምንማረው ብዙ ስሌለለ በሂደት እይተመካከርን፣ እያስተካከልን ስንሄድ፣ ባነሰ ጊዘና መስዋእትነት ድል እንጎናጸፋለን። ይህ ባይሆን፣ ለሚደርሰው ጥፋት የፋኖ መሪዎችም እኛም ተጠያቂዎች እንሆናለን። መገንዘብ ያለብን አንኳር ማስጠንቀቂያዎች የሚከተሉት ናቸው፥

  1. በኦሮሙማ መንግስት የአማራውን ህልውና ለማጥፋት በመደረግ ላይ ያለውንና ሊደረግ ስለታቀደው፤
  2. የአማራ ፋኖ በሚያካሂደው የህልውና ትግል ውስጥ ያለውን ክፍተት፤ በተለይ ለሁለት የተከፈለውን የፋኖ የትጥቅ ትግልን ስለተመለከተ፤
  3. የፋኖ ትግል አሸናፊ ሆኖ አዲስ አበባ እንደሚገባ የተገነዘበው አቢይ አህመድ፣ ይህንን የፋኖ ግፊት ለመመከት “ጦርነቱ ከአማራ ክልል እንዳይወጣና እንዲራዘም” ታላቅ ስትራተጂ በመተግበር ላይ ያለውን እውነታና ፋኖውች እንዲከፋፈሉ እያደረገ ስላለው፤
  4. በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጦርነትና፣ በመፈፀም ላይ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ከዓለም ኅብረተሰብ ለመሸፉፈን እና፣ በኢትዮጵያ አንድነትና ድንበር ላይ የጎረቤት አገራት ጦርነት ሊከፍቱብን እንዳቀዱ ለማስመሰልና ህዝብን ለማነሳሳት፣ አቢይ አህመድ ከኢንተርናሽናል ህግ ውጭ በቀሰቀሰው የጠብ አጫሪነት በአካባቢው ያለውን ውጥረትና የኃይል አሰላለፍ ስለመመርመር፤
  5. ይህ አዲሱ የኃይል አሰላለፍ የአማራን የህልውና ትግልን እና ኢትዯጵያንም እንደ ሀገር ወደ መበታተን እንዳያደርሳት ያለውን ሴራ በመመርመር፣ አማራን ከእዚህ አፍጥጦ ከመጣው የተወሳሰበ ጥቃት ለማዳን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የአማራ ፋኖ አንድነት፣ አማራጭ የሌለው መሆኑን ለፋኖዎች ሁሉ ስለማሳሰብ፣ በውስጥም በውጭም ላሉ የአማራ ትግል ደጋፊዎች፣ በተለይ በዳያስፓራ ሆነው በቅንነት ፋኖን ለሚያገለግሉና እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እፍራሽ ሚና ስለሚጫወቱ።

ይህ የግል አመለካከት ነው፤ ስድቡን ዘለፋውን ትታችሁ እንደሃሳብ ተውያዩበት፤ አማራጭ ሃሳብ ካለም አቅርቡ፤ ስድብና ዘለፋ ላለንበት አገራዊ ችግር መፍትሄ አይሆንም።

ኢትዮጲያ እንደ ሀገር ያለችበት ሁኔታ

በዓለም አቀፍ መለኪያዎች ኢትዮጵይ በአሁኑ ወቅት የደቀቀች እገር (Failed State) ናት።

“A failed state is a state that is unable to perform the two fundamental functions of a sovereign nation-state in the modern world system: it cannot project authority over its territory and people and it cannot protect its national boundaries.”

Failed States 2024: Afghanistan, Democratic Republic of the Congo, Ethiopia, Haiti, etc.

በዓለም አቀፍ መለኪያዎች፣ ኢትዮጵይ በአሁኑ ወቅት የደቀቀች እገር ( Failed State) ናት። በኤኮኖሚ ቀውስ፣ በደህንነት ስጋት፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በህዝብ አግልግሎት እና ጠቅላላ መንግስታዊ አስተዳደር መጥፋት፣ ወጣቱ በግድ እየተመለመለ በማያምንበት ጦርነት የሚማገድበት፣ በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በግላጭ የሚካሄድበት፣ ህግና ስርአት ፈፅሞ የወደመበት፣ በቅርብ የዓለም ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የጭካኔ አይነት የሚፈፀምበት፣ በኃይማኖቶች ላይ ዘመቻ የሚካሄድበት፣ የዓለም መሳቂያ-መሳለቂያ መሪ ተብዬው፣ አቢይ አህመድ፣ በዚች ሙልጭ ያለች ድሀና የጦርነት አውድማ በሆነች አገር ውስጥ፣ የቢሊዮን ዶላር ቤተ መንግሥት የሚሰራበት፣ የወደቀች፣ አገር- ለመሆን እየተቸገረች ያለች ትመስላለች። አገሪቱንም ከውጭ ጠላት መመከት የማይቻልበት ደረጃ እየተደረሰ ነው። ሉኧላዊነቷንም አጥታ፥ በዩናይትድ ዓረብ ኤሚሬትስ እና በዓለም ባንክ፣ ጥብቅ በሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ቅርቃር ውስጥ ገብታ የምትንፈራፈር አገር ሆናለች። ህዝቧ ግን እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አምላኩን እየተማፀነ ነው።

የፋኖ አነሳሱና ግዳጁ

ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በአማራ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈጸም፣ ኢትዮጵያን የሚጠሉ ህወኃቶች በትረ መንግስቱን ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ ፀረ-አማራ ታሪኮችን ወደ ተቋማትና ፖሊሲዎች በመለወጥ፣ አማራውን ፍዳውን ሲየሳዩት፣ ሲገሉትና ዘሩን ሲያጠፉ ከርመዋል። በመቀጠልም፥ ፋሽስቱ አብይ አህመድም፣ ጡት አጥብታ በጉዲ ፈቻ ካሳደገችው ወያኔ በልጦ፣ አማራን በዋና ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጣፋትና የዘር ማፅዳት ዘመቻወን ከጀመረ ከሁለት አመት በላይ አለፈ። ለዚህ ምላሽ የአማራ ህዝብ ከዓመታት የዘር ተኮር ጥቃት በኋላ፣ ከአብራኩ ክፋይ በሆኑ ልጆቹ- ፋኖዎች የህልውና ትግሉን አቀጣጥሏል። በዚህ ትግል የፋኖ ስኬት፣ በሁሉም አማራ አንድነት ላይ የተመሰረተ፣ ጭቆናን ለመቋቋም፣ ህልውናውን ለማስከበር፣ የወደፊት እጣ ፈንታውን ለማስጠበቅ፣ በአንድነት መቆም ብቻ ነው።

የአማራ የህልውና ትግል እዚህ የደረሰውና የሚረጋገጠው፣ ስሜቱ በተነሳሳው፥ ቀዳሽ-አራሽ-ተኩዋሽ፣ ተማሪ-አስተማሪ፣ እናት-አባት፣ ወንድም-እህት፤ መንደራቸውን፣ ከተማቸውን፣ ትምህርትቤታቸውን እና ቤተሰባቸውን ጥለው በዘመቱ ፋኖዎች ነው። በዓለም ታሪክ ውስጥ፣ በዚህ ፍጥነት፣ እንዲህ ያለ የፋኖ አይነት ንቅናቄ ታይቶ አይታወቅም። በአፍሪካ በፀረ-ኮሎኒያሊዝም የነጻነት ትግሎች ውስጥ አንኳን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደዚህ ያለ ደረጃ የደረሰ ትግል የለም። እዚህም የደረስው በገዛ ፈቃዱ ወጥቶ፣ መሪውን መርጦና ተቀላቅሎ፣ የራሱን መሳሪያ አንግቶ፣ ራሱ በፈቀደው ስብስብ ውስጥ ገብቶ፣ ተደራጅቶ፣ ተዋግቶ፣ ሞቶና ቆስሎ ነው። ትግሉንም ዳር ሊያደርሰው የሚችለው እራሱ ብቻ ነው። ከመንደሩ ሲወጣ ሕይወቱን ሊሰዋ የተዘጋጀበትን ምክንያት አጥርቶ ያውቃል። ዋናው ግቡ የአማራን ህልውና ማስከበርና ማስጠበቅ ነው። ጠላቱንም ጠንቅቆ ያውቃል፤ ይህ የአቢይና የኦሮሙማ ስርአት ካልወደቀ አማራ ህልውናውን ሊያረጋግጥ እንደማይችልና በኢትዮጵያም ላይ ፍትህና እኩልነት ያለበት ስርአት ሊፈጠር እንደማይችል ይረዳል። ስለዚህም ነው የትግሉን ግብ አዲስ አበባ ያደረገው።

አቢይ አህመድ ፋኖን እንደማያሽንፍ ተረድቷል፤ የሁለት አገር ዜጎች የሆኑ፣ ከቤተመንግስትም የማይወጡ፣ የውጭ እገር ወታደራዊ አማካሪዎች እንዳሉት ታውቋል። ከፋኖ ጋር ያለውን ጦርነት በተመለከተ፣ የእነሱ ምክር የአማራ ትግል ከአማራ ምድር እንዳይወጣና ጦርነቱም እንዲራዘም ማድረግ ነው። የፋኖ ትግል አላማ ደግሞ ጦርነቱን ከአማራ ክልል ማውጣት ቢሆንም አሁን እንደሚታየው ፋኖ አቢይ የሚልክለትን ጦር ከመውጋት አልፎ ወደ አዲስ አበባ ሊዘምት የሚችልበት ሁኔታ ውስጥ አይደለም ያለው። በአቢይ በኩል ሂሳቡ ግልፅ ነው – (Containment and blocking the

expansion of the war.) ይህንን ማድረግ ከቻለ በገንዘብና በስልጣን ጥሜት የሚገዙ ሰዎችን እየመረጠ የአማራ ፋኖን በመከፋፈልና በማዳከም፤ እንዲሰላች በማድረግ ፋኖን መበተን እችላለሁ የሚል ግምትአለው። አምባ ገነኖች መውደቂያቸው ሲቃረብ የሚችሉትን ሁሉ አድርገው አጥፍተው ይጠፋሉ። ጦርነቱን ለማሸነፍ እንደማይችል ስለሚያውቀው፣ ጦርነቱን በማራዘም ለመቆየት ነው ምኞቱ። ጦርነቱ አማራ ምድር እስከሆነ ድረስ በመከፋፈልም ሆነ በመሰላቸት፣ ድርድር እያለ አንዳንዶችን በማሞኘት፣ ጊዜ ሊገዛ እንደሚችል ያምናል። ፋኖ እዚህ ወጥመድ ውስጥ እየገባ መሆኑ ምልክቶች ይታያሉ።

የምዕራባውያን መንግስታት ፓሊሲን በተመለከተ

አሜሪካና ማዕራባውያን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ተረጋግቶ የነሱን ጥቅም የሚያስከብር መንግስት እንዲቋቋም ብቻ ነው የሚፈልጉት። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፋኖ ያሸንፋል ብለው ስለማያምኑ፣ ያለውን ማቆየት የመረጡ ይመስላል። በቅርቡ ይፋ የሆነው ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት ጋራ የሚሰራ ድርጅት (American Enterprise Institute, AEI) ረፖርት እንዲህ ይላል፥

“የእትዮጵያ መንግስት ፋኖን ለማሸነፍ ችሎታ ያለው አይመስልም። በኃይል ብቻ አሸንፋለሁ ብሎ የተነሳው እንደማይሰራ ተገንዝቧል። ፋኖ ጠንካራና የማይበገር ኃይል ሆኖበታል፤ በውጊያ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአስትዳደር መዋቅሮችን የመዘርጋት ችሎታውንም ፋኖ አሳይቷል። …. The Ethiopian government is likely unable to defeat the Fano insurgency militarily. The Ethiopian government’s military-centric approach to the insurgency, including a state of emergency & sweeping powers to federal troops, has eroded local trust. Despite efforts, the insurgency remains resilient. Fano has even set up local administrations to maintain influence.”

ከሪፖርቱ ውስጥ አንድኛው አነጋጋሪ የሆነው ነጥብ፥

“ፋኖ ማእከላዊ አስራር ሰለሌው እና በውስጡም የተከፋፈለ ስለሆነ፣ አንድ የተጠናከረ የፖለቲካ ኃይል እንዳይሆን ወደ ኋላ እየጎተተው ነው። አንድነትና ግልጽ የሆነ የመታገያ መድረክ ሳይኖረው የፌደራል መንግስቱን ለመተካት አማራጭ ሆኖ ለመገኘት እየሞከረ ነው። የአመኔታና የእርስ በርስ መከፋፈሉ ትልቅ እንቅፋት ሆኖበታል።”

“Fano’s decentralized structure and internal divisions are holding back its potential to become a political force. Without unity or a clear platform, it’s struggling to position itself as a viable alternative to the federal government. Trust issues and varying goals among factions remain major obstacles.”

ምዕራባውያን የሚያዳምጡት የተለያዩ የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ ድምፆችን ነው፤ አንድ የአማራ ድምጽ ስለሌል፣ የጸና አስተያየት የላችውም። በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና የዘር ጭፍጨፋም ያውቃሉ። ግን የውጭ ፓሊሲአቸውን ለመመስረት ሚዛኑ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ነው፤ በዓለም ውስጥም ብዙ አምባገነን መንግስታትን ይደግፋሉ። ጥቅማቸውን እስካስከበሩላቸው ድረስ፣ ሁሉ ነገር በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ እያዩ፣ ኃይል ያለውንና ስትራተጂክና ኤኮኖሚያዊ ጥቅሞ ሊያስገኝላቸው የሚችለውን ብቻ ነው የሚረዱት።

የአቢይ ስርአት በአማራ ላይ ያደረስውን የዘር ማጥፋትና ትላልቅ ጥፋቶች ሙሉ በሙሉ ቢረዱም፣ በአሁኑ ሁኔታ ከእሱ የተሻለ ሌላ ስርአት በኢትዪዮጵያ ውስጥ ሊመሰረት ይችላል ብለው የሚያስቡ አይመስለም። ከብዙ አቅጣጫ፣ በተለይ ከኢትዮጵያውያን የሚያዳምጡት የተለያየ ድምፅ ነው። እማራውን ብቻ ብንመለከት በዳያስፓራ ውስጥ የተከፋፈለ ድምፅ እንዳለ ይረዳሉ። ስቴት ዲፓርትመንት ዛሬ አንድ አማራ ገብቶ ተነጋግሮ ሲወጣ ሌላው አማራ ነኝ ባይ መጥቶ የሚናገረው ሌላ ነው። በፋኖ ትግል ላይ በሶሻል ሚዲያና በሌሎችም ሚዲያዎች ላይ የሚነገረውን እና የሚጻፈውን ያውቃሉ። የአማራን ህልውና በተመለከተ አንድ የሆነ ድምፅና ጠንካራ ኃይል የለም።                                                                                    ከላይ እንደተገለጸው፣ ፋኖ አማራጭ ይሆናል ብለው የሚገምቱበት ደረጃ አልደረሱም። የፋኖ ጥንካሬ የሚመዘነው ትግሉን ከአማራ ምድር አውጥቶ ወደ አዲስ አበባ እንዲጠጋ በማድረግ ብቻ ነው የአቢይን ድክመት መላው ዓለም ሊረዳ የሚችለው። የዚያን ጊዘ ሁሉም አቋም ይወስዳል፤ ይህ የማያጠራጥር ነው።

የዩናይትድ ዓረብ ኤመረትስ ጉዳይ

ከዓረብ ዓለም የአቢይ ታላቅ ተባባሪዋ ኤመረትስ ነች። ዩናይትድ ዓረብ ኤመረትስ በመላው እፍሪካ መረቧን እየዘረጋች ነው። ኢትዮጵያንም የምትፈልገው የእርሻ መሬቶችን ለማግኝትና በሌሎችም ወደፊት ለሚመጡ የኢንቬስትመንት እድል ቀዳሚ ተዋናይ ለመሆን ነው። ኤመረትስና ሳውዲ ጠቅላላ የእርሻ ምርት ከውጭ ስለሚያመጡ የተረጋገጠ የእህል ማምረቻ መሬቶች ከብዙ አፍሪካ አገሮች እየገዙ ናቸው። በሶማሊላንድ በርበራ ያለውን ወደብ የምታስተዳድርና፣ በኢትዯጵያና በሶማሊላንድ መሀል የተደረገውን ስምምነት የገፋፋችና ያዘጋጀች ኤመረትስ ነች። ቢሳካ ወደቡን የሚያስተዳድር የኤመረትስ ኩባንያ DP World ይሆናል።

“Dubai Port International (DPI) founded in 1999, currently known as DP World, is an Emirati multinational logistics company based in Dubai. It specializes in cargo logistics, port terminal operations, maritime services and free trade zones.”

ኤመረትስና አቢይ በሱዳን ጦርነት የሚደግፉት የዳርፋሩን ጄኔራል፣ General Mohamed Hamdan Dagalo (RSF) እዛዥን እንጂ፣ Generla Abdel Fattah al-Burhan፣ የሽግግር ምንግስቱን መሪ አይደለም። ኤመረትስ በሱዳን ያላት አንደኛው ጥቅም፣ በዓለም በወርቅ ማዕድን ታላቅ ከሚባሉት አካባቢዎች አንዱ የሆነውን፣ በዳርፋር ሱዳን የተከማቸውን ወርቅ መበዝበዝ ነው። እስክ ዛሬ ኤመረትስ ይህንን ወርቅ በማምረት ጄኒራሉን ሀብታም እድርገዋለች። እንድ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ዓ.ም. ብቻ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ ገዝታለች። ብዙ የጦር መሳሪያ በGulf of Guinea በኩል በChad አድርጋ እያስገባችም ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ “ዋግነር” ተብሎ የሚታወቀውን የሩሲያ ተቀጣሪ ወታደር ድርጅት (mercenary) ኤመሬትስ እየከፈለች ከጄኔራሉ ጎን ሆነው እንዲዋጉ አድርጋለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋግነር በሩሲያ መንግስት ተወርሶ ‘አፍሪካ ኮር’ ተብሎ ስራውን ቀጥሏል። ግን የሩሲያ አሰላለፍ ከሽግግር መንግስት ጋር ስለሆነ በሱዳን የዚህ መርስነሪ ስራ ግልፅ አይደለም። ያፈተለከውም ወሬ እንደሚገልጸው፣ ኤመረትስ ይህንን የመርስነሪ ድርጅት ኢትዮጵያ ለማስገባት ከአቢይ ጋር ተነጋግረውበታል ይባላል። የዚህ ድርጅት መሪዎቹ                                                                                              በዜግነት ሩሲያውያን ይሁኑ እንጂ ተዋጊዎቹ ከአፍሪካ ምድር የተመለመሉ ናቸው።

የአፍሪቃ ቀንድ ወዳጆች፣ የገልፍ ካውንስል አባላት የነበሩ፣ በየመን ላይ አብረው የዘመቱ ሳዑዲንና ኤመረትስን አቃቅሯል። ዛሬ ግብፅ፣ ሳውዲና ኤርትራ፣ሶማሊያ ጄኔራል አል-ቡርሃን ከሚመራው፣ የሽግግር መንግስቱ ጋር ናቸው። አቢይና ኤመረትስ ደግሞ ከጄኔራል ሀምዳን ዳጋሎ ጋር ስለሆኑ፣ ይህ አስላለፍ ኢትዮጵያንም ይመለከታል።

የሶማሊያ ጉዳይ

ሶማሊያን በተመለከተ አስላለፉ ተመሳሳይ           ነው። የሶማሌ-ላንድና የኢትዮጵያን መንግስት ስምምነት የሚቃወሙና፣ አቢይ በግድም በውድም ሶማሌ-ላንድ እገባለሁ እያለ፣ ለወረራ ተዘግጅቶአል ብለው የሚይምኑት ኤርትራ፣ ግብፅና የሶማሊያ መንግስት፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ አንድ ጠንካራ አቋም እንዲይዙ እድርጎአቸዋል። ግብፅ ወደ 10,000 ወታደርና መሳሪያ አስገብታለች። የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ ያደረገችው ስምምነት ህገወጥ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ስለወሰነ የዚህ ህገ ወጥ መንግስት የሠላም ጠባቂ                                              ኃይል ከአገሬ ምድር ይውጣ ስላለች ግብፅ ያስገባሁት ጦር የሚወጣውን የኢትይጵያን ሠራዊት ለመተካትና ኢትዮጵያ በኃይል ሶማሌ-ላንድ ብትገባ ለመከላከል ነው ብላለች። ለማናችውም የተበብሩት መንግስታት የሰላም ጥባቃ ተልእኮ በዚህ አመት ሲያልቅ የኢትዮጵያ ሠራዊት መውጣቱ አይቀርም ነበር። ኤርትራም የሶማሌን ጦር ለማሰልጠን ሠራዊት አስገብታለች። የሶማሌም ሠራዊት ለመሰልጠን ኤርትራ ገብቶአል። በዚህ ሳምንት የሶስቱ አገሮች ፕሬዚዳንቶች በአሥመራ ከተማ መሰብሰባቸው ይህንኑ አቋማቸውን ለማጠናከር ነው። በግልፅ ከተነገረው ባሻገር ያልታወቀው የንግግራቸው አጀንዳና ውሳኔዎች፣ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አገሮችን ሊያሳስብ ይገባል። በአማራ ትግል ላይ የሚያስከትለውም ተፅእኖ ከመገመት ባሻገር በአሁኑ ወቅት ብዙ መናገር እይቻልም። አቢይ የሚያስወራው በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ሊፈፀምብን ነው ብሎ ብሔራዊ ስሜትን በመቀስቀስ ከዋናው ትግል ለማሳሳት ነው የሚፈልገው፤ ይህንን ጠብ ጭሮ፣ ከአፍሪካ አንድነትና ከተባበሩት መንግስታት ህግ ውጭ፣ አንድ የሶማሊ አካል ከሆነ የአስተዳደር ክፍል ያለሶማሌ መንግስት እውቅና መደራደር አይቻልም። ቱርክ ከሶማሊያ ያለው ግንኙነት እይተጠናከረ መጥቶአል። ዋና ጥቅሟ ነዳጅ ፍለጋ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የተፈጠረው ውዝግብ ቱርክ ለሶምሊያ ሙሉ ድጋፍ የመስጠት አቋሙዋን አጠናክሮታል።

ሶማሊያ በመንግስት ከሚታወጅ ጦርነት ይልቅ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ሁለት ጉልህ አማራጮች አሉዋት። እነዚህም ሁለት አማራጮች ሶማሌ ውስጥ ውይይት ተድርጎባቸዋል፥

  • አንደኛው አልሽባብን መደገፍና ከሶማሌ ወጥቶ ኢትዯጵያ ውስጥ የጀመሩትን እንዲያጠናክሩ ማድረግ ሲሆን፤
  • ሁለተኛው ደግሞ የታላቁዋ ሶማሊያን ምኞት እውን ለማድረግ በምእራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ንቅናቄ ስም (Western Somalia Liberation Front – WSLF) በሲያድ ባሬ ዘመን የተከፈተውን ጦርነት የዚህ ድርጅት ተቀጣያ የሆነውን Ogaden National Liberation Front (ONLF) እንደገና ማንቀሳቀስ ነው።

ኦጋዴን የኢትዮጵያ አካል መሆኗን በተመለከተ ረዥም ጥናት “ክህደት በደም መሬት” በሚለው መፅሀፈ ላይ ተገልጿል። እነዚህ አማራጮች፣ በተለይ በግብፅ ድጋፍ ከተሰጣቸው፣ ለኢትዮጵያ ህልውና አደገኛ ናቸው። ግብፅ ለኢትዯጵያ አትተኛም፤ በኦርሞ ክልልም Islamic Republic of Oromia የሚል አቋቁማ ንቅናቄዎች ማስጀመሩዋ ይታወሳል። ይህንን ሁሉ የጠላት አሰላለፍ ሊመክተው የሚችለው አንድነትና፣ አማራን ማእከል ያደረገ፣ ሁሉን ያቀፈ አዲስ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት ነው። ከሶማሊ ሪፓብሊክ ግዛት ያፈነገጠችውን፣ በተባበሩት መንግስታት ያልታውቀችውን አገር እውቅና መስጥት፣ እንደ ሲያድ ባሪ ጊዜ፣ ኦጋዴን የሶማሊያ አካል ነው ብሎ እውቅና እንዲስጠው ለመጠየቅ መንገድ መክፈት ነው። ይህ እንዳይሆን በአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ፥ “ሁሉም ከቅኝ ግዛት አስተዳደር የተላቀቁ አገሮች፣ ከቅኝ ገዢዎቻቸው የተረከቡትን ድንበር እንዲጠብቁ” ስምምነት ተደርሶአል። ይህ ስምምነት ባይኖር ኖሮ አፍሪካ ከባድ ትርምስ ውስጥ ትገባ ነበር፤ በአፍሪካ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጎሳዎች (ትራይብስ) ይኖራሉ። ግን አፍሪካ ያሉት 54 አገሮች ብቻ ናችው። እንደ ኢትዮጵያ ሕገ መንግስትና የዘመኑ ፖለቲከኞች ትረካ አፍሪካ በሺዎች

የሚቆጠሩ መንግስታት ይኖሯት ነበር። የጅቡቲ መንግስት ለዚህ ሁሉ አስታራቂ ሀሳብ ይሆናል በሚል፣ ኢትዯጵያ በአሁኑ ጊዜ ለወደብ መጠቀሚያ ከምትከፍለው በጣም ዝቅ ያለ ክፍያ እንዲሆን አዲስ ስምምነት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ ነኝ ብትልም የአቢይና የኤመረትስ ዓላማ ለየት ያለ ስለሆነ እልተቀበሉትም።

“Djibouti’s government has proposed granting Ethiopia exclusive access to one of its ports, a significant diplomatic move aimed at reducing tensions in the Horn of Africa. This offer is seen as a strategic response to Ethiopia’s ongoing pursuit of direct sea access, which has been a longstanding issue since the country became landlocked following Eritrea’s independence in 1991. Djiboutian Foreign Minister Mahamoud Ali Youssouf revealed this proposal during an interview on the sidelines of the Forum on China-Africa Cooperation in Beijing. He stated that the plan has been submitted to Ethiopian authorities and that Djibouti expects a favorable response soon. The offer includes granting Ethiopia “100% management” of a harbor at Tadjoura, located along Djibouti’s coast. This move, if accepted, could alleviate the strain caused by Ethiopia’s diplomatic efforts to secure access to other ports, such as Somaliland, which has sparked regional disputes.”

https://intpolicydigest.org/djibouti-offers-exclusive-port-access-to-ethiopia-in-bid-to-ease-regional-  tensions/

ይህ የአቢይ አሃመድ አሰላልፍ ግራ የሚያጋባ፣ ያገሪቱን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል፣ አገሪቱን ለበለጠ                        መፈራረስ የሚያጋልጥ፣ ብረት ያነገቡትን የሚጋቢዝ           መሆኑን አዋቂዎች ይዘግባሉ። በሠላማዊ ጉርብትና መኖር ሲቻል፣ የሥልጣኑን ጊዜ ለማራዘም ጦርነቶችን የሚጋብዘውን አቢይንና ስራአቱን ባስችኳይ ማጥፋት ጌዜ የማይስጠው የፋኖ ግዳጅ ነው።

ለምሳሌ፣ “But perhaps most concerning is how Ethiopia’s actions seem to be giving terror groups in the region the space they need to grow, recruiting large numbers of young men under the guise of defending an Islamic cause. The Ethiopian regime appears to have aligned itself with extremist positions held by Somali religious terrorists and secessionists. Abiy Ahmed’s government, seemingly unaware of the peril it’s inviting, has jeopardized not only its national security but also the stability of the region.”

የኬንያ ጉዳይ

በኬንይም በኩል የሚሰማው ጥሩ አይደለም። የኬንያ ባለስልጣኖች በቴሌቪዥን (KTN) ሲወያዩ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ አስተዳደር የኬንያ ኦሮሞ ኮሚኒቲ ጀምሮ በርበራንና ሞምባሳን ያጠቃለለ የኩሽ ግዛት (Empire) ለማቋቋም የአቢይ ዋና አጀንዳ ስለሆነ ራሳችንን ለመጠበቅ መሰናዶ መደረግ እንዳለበት መንግስትን አሳስበዋል። ይህ ደግሞ ያልታሰበ ስጋት ነው፤ ከዚህ በፊትም በዚያ አካባቢ የተነሳውን የአልሽባብን ንቅናቄ ለመግታት የኢትዮጵያ መንግስትና የኬንያ ምንግስት ስምምነት አድርግው ነበር። ይህ ፍጥጫ የጋራ ጠላት የሆነውን አልሽባብን ለመመከት አያስችልም።

መደምደሚያ

ይህንን ስርአት ገርስሶ አማራን ያማከለ ሁሉን አቃፊ ጠንካራ መንግስት ሊያቋቁም የሚችለው ፋኖ ብቻ ነው። ስለሆነም ፋኖ እንደ ጠንካራ ኃይል ሆኖ ለመውጣት ፈተናዎች አሉበት። ዋንኛው በመሪዎች በኩል ያለው መለያየት ነው። ፋኖ እራሱን ነው መምራት ያለበት። ሲመሰረት ንቅናቄ ሲጀምር በእራሱ አለቆች፣ አብረውት ከተሰለፋ ከሞቱ ከቆሰሉ መሪዎቹ ጋር ነው። የፋኖ ሰራዊት አዲስ አበባ ገብቶ ጊዚያዊ መንግስት ለማቋቋም፣ በፋኖ እዝና በየደረጃው ያሉ ሌሎች መሪዎች ጊዚያዊ መንግስት ምስረታ የሚያደርስ አቅምም እውቀትም አላቸው። ይህንን ሀላፊነታቸውን አሳልፈው በመስጠት ለአመራርነት በቀረቡ ተወዳዳሪዎች መሀከል በተፈጠረው ልዩነት ጠቅላላ የፋኖ ኃይል ለሁለት ተሰንጥቆአል። ልዩነቱ የፋኖን ሠራዊትን አይመለከተውም። የፋኖ ሠራዊት ከመላው አማራ ፋኖ ጋር ለመስራት ነው ከነበረበት መንደርና ከተማ ገንፍሎ የወጣው። የወጣውም ለግዳጅ ነው፤ ከወጣበት ግዳጅ ጋር ባልተያያዙ ምክንያቶችም ዛሬ ትልቁ የፋኖ ስጋት አንድነት ማጣቱ ሆኖ ተገኝቷል። ስልዚህ ነው ፋኖ የራሱን ወታደራዊ ካውንስል (ሚሊታሪ ካውንስል) ከአራቱም ክፍለ ሃገር ካሉ እዞች በተመረጡ ፋኖ አባላት አቋቁሞ፣ በነሱ አስተባባሪነት፣ ሳይለያይ ስራውን መስራት ይችላል፤ ይህም ካውንስል በተለዋዋጭ ቦታዎች ዋና መምሪይውን አድርጎ ያስተባብራል። የክፍላተ ሃገራት እዞች አንድ መሆን የለባችውም። አንድ ቢሆኑ ይመረጣል፤ ግን አድካሚና የበለጠ ከፈፋይ ሊሆን ይችላላ።አላማቸው አንድ ሆኖ በፋኖ ካውንስል (ሚሊታሪ ካውንስል) አስተባባሪነት መስራት እስከፈቀዱ ድረስ እነሱን አንድ ለማድረግ ጉልበትና ጊዜ መባከን የለበትም። ሠራዊቱ በክፍለ ሀገር በጎጥ ሳይለያይ የራሱን ሚሊታሪ ካውንስል አቋቁሞ በውጭም ብውስጥም ባሉ ባለሙያዎች እየተደገፈ እንዲሰራ ይደረጋል። ስርአቱን ገርስሶ በፋኖ አመራር ጊዚያዊ መንግስትም ያቋቁማል።

ከካውንስሉ ጋር የሚሰራ የፖለቲካ መምሪያ አሁን ባሉትና አዲስም ሊመጡ በሚችሉ አዋቂዎች ይቕቕማል። መምሪያው ከበላይ ሳይሆን ከጎን ሆኖ ከካውንስሉ ጋር እይተናበበ ይሰራል። ፖለቲካ መምሪያው ይሚያተኩረው ዲፕሎማሲ፣ በአማራውና በመላው ሃገር ውስጥ ሕዝቡን ማነቃቃት፣ እርዳታ ሰስብሰባ፣ ለጊዝያዊ መንጊስት ጥናትና ዝግጅት ማድረግ፣ የሎጂሲክስ አቅርቦት፣ ወዘተ – ይህ ራሱን የቻለ ስራ ነው።

ፋኖ አንድነቱም ሊረጋገጥ የሚችለው፣ አሸናፊነቱም  ሊረጋገጥ የሚችለው፣ በእዚህ አይነት የስራና ሃላፊነት መከፋፈል ነው። በጠቅላላው አንዱ ካንዱ በላይ ወይም በታች ሳይሆን፣ የፖለቲካ መምራያውና ሚሊታሪ ካውንስሉ ጎን ለጎን መስራት ወሳኝ ነው። ሰራዊቱ ተባብሮ የሚሰራው በሚሊታሪ ካውንስሉ አስተባባሪነት ብቻ ነው። ከዚህ የተሻለ አንድ የሚይደርግ መንገድ ካለ፣ ወይም በዚህ በቀረበው ሃሳብ ላይ ሁሉም እዞች ተውያይተውበት አንድ የአማራ ሠራዊት እንዲኖር ማድረግ የእዝ አዛዥች ሃላፊነት ነው። አለበለዚያ፣ የያዝነው አካሄድ የአቢይ መንግስት ወጥመድ ውስጥ እየከተትን ነው። አቢይ ያለ የሌለውን ኃይል እያሰማራ ነው። በአቢይ ምክንያት በአካባቢው አሰፍስፎ የሚጠብቀውን የጠላት ስምሪት ለመቋቋም የማይቻልበት ደረጃ ተደርሶ፣ አማራ እንደ ህዝብም፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የሱዳን እጣ እንዳይደርሳት እሰጋለሁ።

Four takeaways from the Critical Threats Project Report published recently about Fano and Ethiopia:

  • The Ethiopian government is likely unable to defeat the Fano insurgency The Ethiopian government’s military-centric approach to the insurgency, including a state of emergency & sweeping powers for federal troops, is eroding local trust. Despite efforts, the insurgency remains resilient. Fano has even set up local administrations to maintain influence.
  • The escalating insurgency & violence in Amhara is eroding any remaining support for the government. Insecurity has fueled crimes like kidnapping & civilian targeting, sparking protests. The recent tragic killing of 25 protestors in Gondar has only intensified grievances fueling the Fano
  • Fano’s decentralized structure and internal divisions are holding back its potential to become a political Without unity or a clear platform, it’s struggling to position itself as a viable alternative to the federal government. Trust issues and varying goals among factions remain major obstacles.
  • Fano’s insurgency is intensifying tensions in Ethiopia, particularly with Tigray and Recent clashes over disputed areas highlight the growing risk of ethnic conflict as both Amhara and Tigrayan forces vie for control. Calls for withdrawal & disarmament further escalate tensions.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.