Breaking News
Home / Amharic / አባ ገዳ መወገድ ያለበት ጎጂ ባህል ! ABAGEDA Brutal primitive Culture to be banned.

አባ ገዳ መወገድ ያለበት ጎጂ ባህል ! ABAGEDA Brutal primitive Culture to be banned.

አባ ገዳ በአሁኑ ጊዜ በጣም ተኳኩሎና ተጋኖ ይነገርለታል። በእዉነት አባገዳ አሁን እያጋነኑና እያንቆለጳጰሱ እንደሚነግሩን ነዉ ወይ ? ለዚህ አሁን ላለንበት ዘመንና ትዉልድስ ይጠቅማል ወይ ? ከሚሉት ዋና መሰረታዊ ጥያቄዎች በተጨማሪ በውስጡ ስለነበሩት ባህላዊ እሴቶችም መመርመር አለብን አይ አሁን ይሄ የለም ይሄ ቀርቷል የሚለዉ አይሰራም፣ የሁኔታዉ አለመፍቀድ እንጅ የገዳ አካል አይደለም ማለት አይደለም፣ አይቻልም። በአባ ገዳ አንድ ሴት ባል ከሞተባት የባል ወንድም ወይም የባል የቅርብ ዘመድ እንዲያገባት ይፈቅዳል። በዚህ አይነት በአባ ገዳ (polygamy ) ማለት ብዙ ሚስት ማግባት ይፈቅዳል ማለት ነዉ። ባል ሲሞት ወንድም እንዲያገባት የሚያዝዝ ከሆነ፣ ወንድም ሚስት ሊኖረው ስለሚችል መቸም ሚስትህን ፍታ አይለውም። ሌላዉ ማንም ወንድ ጦሩን በሩ ፊት ለፊት ተክሎ ገብቶ ደስ ካለቸዉ ሴት ጋር ያገባችም ሴት ብትሆን ጉዳዩን መፈፀም ይችላል የሚባልም ነገር አለ። በዚህ ጊዜ ቤት ዉስጥ ወንድ መኖሩን የሚገልጥ ምልክት ጦሩን በር ላይ ተክሎ ይገባል። ይሄም ባል ድንገት ከመጣ ሚስቱ ከወንድ ጋር መኖሩዋን የሚናገርና እንዳይገባ ምልክት የሚሆን ነዉ። ባል ይሄን ህግ አልፎ ገብቶ በሰዉየዉ ላይ ጉዳት ካደረሰ ግን በአባገዳዉ ህግ ይቀጣል። በዚህ ሁኔታ ልጆች አባታቸው ማን ነዉ ? ይሄ የእኔ ጥያቄ ነዉ ? ሌሎችም ብዙ በአባ ገዳ ስራት ሲፈፀሙ የነበሩና የሚፈፀሙ ነገሮች አሉ። ሌላዉ በአባ ገዳ አንድን ወንድ ጀግና የሚያሰኘዉና ጀግና ሊያስብለዉ የሚችለዉ ዋና መመዘኛ የሌላውን ነገድ ሰዉ መግደልና መስለብ መሆኑ ነዉ። ብዙ ሰዉ የገደለ በአባ ገዳዉ የተከበረና መሪም የመሆን እድል ይሰጠዋል፣ ያስችለዋል። ወንዶች በጋብቻ ጊዜ የወንድ ብልት ሰልቦ አምጦ እንዲያሳይ መደረጉ ሌላዉ ነዉ፣ ሌላዉ በአባ ገዳ የተለመደ ንርዉ።

~ሞጋሳና ጉዱ ፌቻ።

የሞጋሳ ስራት የተጀመረዉ በቦረናና በባሬንቱ ነገዶች ነዉ። እነዚህ ነገዶች የሚወሩት ግዛት እየሰፋ በሄደ ጊዜ የእነሱ ቁጥር እያነሰ በመሄዱ፣ በቁጥራቸዉ ማነስ ምክንያት ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ የወረረሩትን ሙሉ በሙሉ ከመግደል ይልቅ ባሪያና ገባር ቢያደርጉት የበለጠ ጠቃሚ ነዉ ብለዉ ስለወሰኑ፣ የጉዱ ፌቻና የሞጋሳን ሥራት በስራ ላይ አዋሉ። በሞጋሳና በጉዱ ፌቻ የሚይዙትን ሕዝብ ባህሉን፣ ቋንቋዉንና ማንነቱን በማጥፋት ስሙን ሁሉ በመቀየር በምንም ታምር ወደ ነበረበት ወደ ሁዋላ እንዳይመለስ በማድረግ ነበር፣ በሞጋሳ የሚወርሱት። እንዲሁም ሁኖ ግን ይሄ ሕዝብ እንደሚባለው ወዲያው ኦሮሞ አልተደረገም በመጀመሪያ #ገርባ ነበር የሚባለዉ #ገርባ ደግሞ አገልጋይ ማለት ነዉ። #ገርባ ኦሮሞ በፈለገ ጊዜ የሚሸጠዉ ባሪያ ማለት ነዉ።

በነገራችን ላይ አንድ የኦሮሞ ብሔርተኛ ብዙዎች የምናዉቀዉ #በቀለ_ገርባ ይቺን ገርባ የት አገኛት በእውን ገርባ ይሆን እሱ ራሱ? ብየ አሰብሁ።

ምንጭ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን ” The Oromo of Ethiopia: A history, 1570_1860″ በሚል መጽሐፍ ገጽ 126. ያንቡ።

ይህ የተወረሰና ማንነቱን ያጣ ኦሮምኛ ተናጋሪ የማኅበረሰብ ክፍል #ገርባ የኦሮሞ የግል ንብረት ነበር እንጅ እኩል ኦሮሞ አልነበረም። በገዳ ሥራትም ለመሳተፍ የሚፈቀድለት አልነበረም። አብዛኞች የባሪያ አቅራቢዎች ሞቲ/ የኦሮሞ ገዥዎች/ የሆኑት ነበሩ። በሞቲዎችና በአባገዳዎች ለሽያጭ የሚቀርቡትም አገልጋይ የነበሩት ገርባዎች ነበሩ። በዚህ የአባ ገዳ ወታደራዊ ስራት በተደረገዉ መስፋፋት ወደ 28 የሚሆኑ የራሳቸው ማንነት፣ ቋንቋ ባህል የነበራቸው ነገዶችን አጥፍቷል። ይህ ነዉ የአባ ገዳ አቃፊነት፣ አሁንም በግድ መማር፣ በግድ የእነሱን እንድንቀበል ማስገደድ ማለት ሌላ ትርጉም የሚሰጠዉ አይደለም ሌላዉን ከመጨፍለቅና ከማጥፋት የተለየ። አሁን አዲስ አበባ ወቅቱ በሚፈቅደዉ መሰረት በሞጋሳ እየተወረሰ ነዉ፣ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠዉ አንችልም። በኢትዮጵያ ሥራተ ትምህርት በታሪክ በትክክለኛው ማንነቱ ስለ አባ ገዳ መነገሩ ተገቢ ነዉ፣ ታሪክን በሚያስተምር መልኩ ከዚያዉጭ ግን ተመርጦ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በትምህርት ሥራቱ ላይ መጫን ተገቢ አይደለም አይጠቅምም።

 

source: ጌታቸው ሙላቱ /Getachew Mulatu

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.