Breaking News
Home / Amharic / የአበበ ገላው ነገር። በአቻምየለህ ታምሩ።

የአበበ ገላው ነገር። በአቻምየለህ ታምሩ።

የአበበ ገላው ነገር. . .

አበበ ገላው በትናንትናው እለት በከፈተው የዩቱብ ሱቅ በኩል ባሰራጨው ቃለ መጠይቁ ዐቢይ አሕመድ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ግንቦት ወር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” እንዳለው እና ይህ የዐቢይ አባባልም እንደ ኤሌክትሪክ እንደነዘረው፣ ዐቢይ አሕመድን በጥርጣሬ ዐይን እንዲያየው እንዳደረገውና ውስጡ እንደነቀለቀው ነግሮናል። ምንም እንኳን ዐቢይ አሕመድ በሚሊዮን አመታት ውስጥ አማራ ኢትዮጵያን እንዳይመራ የነገረውና ውስጤ ቀረ ያለውን ጉዳይ በደንብ እንዲገባው በአማርኛ ብቻ ሳይኾን አጽንኦት ለመስጠት የእንግሊዝኛ አገላልጽ ጭምር በመጠቀም ቢነግረውም ቅሉ አበበ ገላው ግን ነገሩ የአፍ ወለምታ ስለመሰለው ወደ አደባባይ ሳያወጣው እስካኹን ድረስ ጸጥ ብሎ እንደቆየ ሊያስረዳን ሞክሯል። ይገርማል!

አበበ ገላው በትናንትና እለት “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ የሰጠውን ሸቀጥ እንካችኹ ሊለን የሚቃጣው ዐቢይ አሕመድን እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. በግንቦት ወር አግኝቶት “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ካለው በኋላ ዐቢይ አሕመድን በጥርጣሬ ዐይን ተመልክቶት ስለሱ ሳይተነፍስ ከርሞ ትናንትና መናገር የጀመረ እንጂ ዐቢይ አሕመድን ሲያመልክ የከረመ፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ሲል ኦዴፓ ያወጣውን መግለጫ ዐቢይ አሕመድን የሚነካበት ስለመሰለው መግለጫው የኦሮምያ ክልል ተብዮው እንጂ የፓርቲው የኦዴፓ አይደለም እያለ ሲጃጃል የከረመው፤ የውሸት የትምህርት ማስረጃው የእውነት እንደኾነ ሽንጡን ገብሮ ከእኔ ጋር ሲከራከር የነበረ አይመስል። ልብ በሉ! አበበ ይህንን ሁሉ ያደረገው ዐቢይ አሕመድን አግኝቶ “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years !” ካለው በኋላ ነው።

እኔ እንደማስበው አበበ ገላው በደጅ ጥናት ተሳክቶለት ዐቢይ አሕመድን ካገኘው በኋላ የእንግሊዝኛ አጽንኦት ጨምሮ “ከእንግዲህ አማራ ኢትዮጵያን አይመራም” ካለው በኋላ ምንም ሳይመስለው ስለ ዐቢይ አሕመድ ልዕለ ሰብዕ መሆንና በውሸት ያከማቸውን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ ለማስረዳት ሲጋጋጥ የነበረው ትናንትና ሊነግረን እንደሞከረው “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ዐቢይ በቤተ መንግሥት የነገረው ገር የአፍ ወለምታ ስለመሰለው “አፉ” ብሎት ሳይኾን በሀሳቡ ስለሚስማማ ነው።

የአበበ ገላው እናት ድርጅት የኾነው ግንቦት ሰባት የኦባማን መመረጥ ተከትሎ በርዕሰ አንቀጹ ቁጥር 27/2001 ዓ.ም. ላይ እንዳወጀው ድርጅቱ የሚታገለው የፖለቲካ ስልጣንን ለአስርተ መቶዎች አመታት እየተፈራረቀ ሲገዛ ከነበኖረው ከአማራና ከትግሬ ወደ ኦሮሞውና ደቡቡ ለማሸጋገር እንደኾነ አውጇል። ስለዚህ የአበበ ገላው ጠቅላይ ሚኒስትር የተሰየመው ከኦሮሞ ስለኾነና አበበና ድርጅቱም የታገሉት ከእንግዲህ በኋላ አማራ ኢትዮጵያን እንዳይገዛ ስለኾነ እሱና ድርጅቱ የታገሉለት አላማ ስለኾነ አማራ በሚሊዮን አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን እንደማምመራ ሲነገረው የትግሉ ፍሬ ስለኾነ የሚስማማበት እንጂ ዛሬ ለዩቱብ ሸቀል ሲል ሊነግረን እንደሚሞክረው ውስጡን የነቀነቀው የአፍ ወለምታ አልነበረም።

አበበ ገላው የአፍ ወለምታና አስተሳሰብ የተለያዩ መኾናቸው የሚያውቅ አይመስልም። የአፍ ወለምታ በንግግር በሀል በድንገት አንዳልጦ የሚገባ አንድ ቃል እንጂ በአንድ ሙሉ የአማርኛ አረፍተ ነገር የተነገረና የእንግሊዝኛ አጽእኖት የታከለበት አስተሳሰብ አይደለም። በሌላ አነጋገር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም” የሚለው አረፍተ ነገር እና “Not in a million years!” የሚል አጽእኖት የተጨመረበቱ አገላለጽ መሰረታዊ አስተሳሰብ እንጂ የአፍ ወለምታ አይደለም። ዐቢይ አሕመድ “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ለአበበ ገላው የገለጽለትም መሰረታዊ አስተሳሰቡን እንጂ አፉ አንዳልጦት የሳተው የአፍ ወለምታ እንዳልኾነ አበበ ገላውም ያውቀዋል።

አበበ ገላው ይህንን የዐቢይ አሕመድ መሰረታዊ አስተሳሰብ ከፈረሱ አፍ ከሰማ በኋላ አምልኮተ ዐቢይ አሕመድ ውስጥ ገብቶ የውሸት የትምህርት ማስረጃውን ሳይቀር ለመከላከል ሲራኮት የከረመው የዐቢይ የትምህርት ማስረጃ የውሸት መኾኑ ሲጋለጥ አበበ ገላውና ድርጅቱ ግንቦት ሰባት የታገሉለት የፖለቲካ ስልጣንን ከአማራና ከትግሬ ወደ ኦሮሞውና ደቡቡ የማሸጋገር አላማቸው እንዳይደናቀፍ በማሰብ ነው።

አረመኔው ዐቢይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የዘር ፍጅት፣ ማፈናቀል፣ ዘረፋና አማራ አያሳየኝ ብሎ ወደ ማሰቃያና ማጎሪያ ቄራ ማጋዝ የጀመረው ዛሬ አበበ ገላው መናገር ሲጀምር አይደለም። አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ በመደበለት ሪፑብሊካን ጋርድ እየተጠበቀ [ምንም እንኳን አበበ ይህንን ከዐቢይ አሕመድ እንዳገኘው ጥቅም ባይቆጥረውም] ከዲሲ- አዲስ አበባ ሲንሸራሸርባቸው በከረመባቸው ያለፉት አመታት ሙሉ የአማራ ሕዝብ አማራ አያሳየኝ ባለው ዐቢይ አሕመድ የጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጥፋትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ሲካሄድበት ነው የኖረው።

በነዚህ ዓመታት ውስጥ አበበ ገላውና መሰሎቹ አረመኔው ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲያካሂደው የከረመውን የጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጥፋትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በመቃወማችን በጽንፈኛነት ሲከሱን ነበር። ይህንን አበበ ራሱ ለዐቢይ አሕመድ ጻፍኹት ባለው ኢሚል ላይም አንስቶታል። ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያቋቋመውን የስናፍጭ ቅንጣት ያህል የመንግሥትነት ጠባይ የሌለው የኦሮሙማ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የዘር ማጥፋት፣ የቅሚያ፣ የሥርቆትና የወንጀል ድርጅት የሚቃወሙ የአማራ ተወላጆችን አበበ ገላው እንደ ጽንፈኛ ነው የሚያያቸው።

ባጭሩ አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ግንቦት ወር “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ሲል ነገረኝ ካለበት አመት ወዲህ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አረመኔው ዐቢይ አሕመድ አማራ አያሳየኝ ብሎ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋ፣ ገፈፋና የጅምላ እልቂት ሲካሄድበት በኖረባቸው አመታት ውስጥ ዝም ብሎ ከርሞ ዛሬ የአማራ ሕዝብ እውነተኛ የኅልውና ተጋድሎ ሲጀምር ዐቢይ አሕመድ ከአራት አመታት በፊት “ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አማራ አይመራም፤ Not in a million years!” ብሎኝ ነበር በማለት “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ዛሬ እንደነገረው አድርጎ ሸቀጡን ይዞ በዩቱብ ብቅ ያለው የሚያንጠለጥለው አዲስ ማተብ ፍለጋ እንጂ አማራ በሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ስልጣን እንደማይዝ ለአበበ ገላው በነገረው ወቅት ያልነበረውን አዲስ አመል ዛሬ ስላመጣ አይደለም።

አበበም ለዩቱቡ ሱቅ ማድመቂያ ዛሬ ፈልፍሎ እንደደረሰበት አዲስ ግኝት ኹሉ ከአራት አመታት በፊት ነገረኝ ያለውን አምስት አመታት ሙሉ በተግባር ሲለውጥ የባጀውን አረመኔነት ዛሬ “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ይዞት ብቅ ማለቱ ለዩቱብ ሽቀላ እንጂ ባለፉት የዐቢይ አሕመድ አምስት የጭካኔ አመታት ውስጥ አማራን በሚመለከት በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ከዐቢይ የተለየ አስተሳሰብ ስለነበረው አይደለም። በእውነቱ አበበ ገላው ዐቢይ አሕመድ ነገረኝ ካለው የተለየ አስተሳሰብ ቢኖረው ኖሮ ጋዜጠኛነት ተምሬያለኹ እያለ ከአራት አመት በላይ የኾነውን ቀንድ ነገር ይዞ እንደ ሰበር ዜና “የቤተ መንግስቱ ሚስጢር!” የሚል ርዕስ ሰጥቶ እንደ ትኩስ ጉዳይ እንካችኹ ሊለን ከአራት ዓመታት በኋላ ባልመጣ ነበር።

የኾነ ኾኖ አበበ ገላው ዛሬ ላይ ደረስኹበት የሚለው አቋም የብልጣብልጥነትና ለዩቱብ ሽቀላይ ተብሎ ሳይኾን ወደ ውስጡ አይቶ የደረሰበት ሚዛን ቢሆን ኖሮ ከሁሉ በፊት አዲስ አበባን የኦሮሞ ናት ያለው ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ኦዴፓ ሳይኾን የኦሮምያ ተብዮው ክልል ነው፤ በዐቢይ አሕመድ ላይ እኔ ጥያቄ የለኝም፤ ሌሎችም ሊኖራቸው አይገባም፤ ዐቢይን የመሰለ ብቃት ያለው መሪ ኢትዮጵያ ኖሯት አያውቅም፤ ዐቢይ አሕመድ በወያኔ ዘመን ስልክ መጥለፍ የለብንም ብሎ ስለ እኛ ከነ መለስ ጋር ተጣልቶ ከኢንሳ ተባሮልናል፤ የአንድ ክፍለ ከተማ ሕዝብ አፈናቅሎ በ49 ቢሊዮን ብር በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት ቅንጡ ቤተ መንግሥት እየገነባ ያለን አረመኔ ቤተ መንግሥት ሳይኾን ትናንት ቢሮዎች ነው የሚያስፈልጉን ብሎ የሚያስብ የሕዝብ መሪ፣ የሕዝብ ጉዳት የሚጋራ መሪ ወዘተ… እያለና የዐቢይ አሕመድን የውሸት የትምህርት ማስረጃ ለመሸፈን “የሚስጥሩ ቁልፍ” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ዶክተምተሪ በማዘጋጀት ያሳሳተቸውን ሰዎች ይቅርታ ጠይቆ ራሱን ለሕዝብ ፍርድ ማቅረብ ነበረበት።

_________
ይህ ትር እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. ኀምሌ ወር የዐቢይ አሕመድ የትምህርትና ወታደራዊ ማስረጃ የውሸት እንደሆነ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የጻፍኹት ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።

https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/pfbid02cNkRRipZ3NgwKm1JaG54A5YTniFd54XyhfW8hPTneA8fEwHmF67nVF1HRwYpgziMl

ይህ ጽሑፍ በድጋሜ እ.ኤ.አ. በ2020 ዓ.ም. በድጋሜ ታትሟል፤ ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል።

https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/pfbid0LVEeE4uWjN5Q351yNCPAA25N8zbTfQZSVGoBFC9AhGoSt9o2bCQ1cCkS1TR3xsuLl

ይህን ተከትሎ ሌሎች ሰዎች ጭምር የዐቢይን የትምህርት ማስረጃ ውሸትነት ስላስተጋቡት ይህንን በመቃወም አበበ ገላው ዶክመንተሪ ፊልም አዘጋጅቶ ተከሰተ። ማስረጃ አሰባስቤ አጠናሁት ባለው የዐቢይ አሕመድ የትምህርት ማስረጃ የዐቢይ አሕመድ የትምህርት ዝግጅትና ዲግሪዎቹ ውሸት እንደሌለት በከፍተኛ አድናቆት የታጀበ ውዳሴ ዐቢይ ይዞ ብቅ አለ። ይህንን አበበ ገላው ጠለቅ ብየ አጠናኹት ያለውን ዶክመንተሪ ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል፤

https://www.facebook.com/agellaw/posts/pfbid021GXX2yndbCWprXYBMP8EMi3NPARAi1SsgUejMugYEDxYv4ucYdWDVvFW9YgEapAZl

አበበ ገላው “የሚስጥሩ ቁልፍ” ሲል ያዘጋጀውን ዶክመንተሪ ተከትሎ እኔ የሰጠኳቸው መልሶችና አበበ ገላው የሰጣቸው ግብረ መልሶችን የሚከተሉትን ትሮች በመጫን ማንበብ ይቻላል፤

1. https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/pfbid02kHm2nmcQpNESTDK4meRrYenJ9twBBK45jQTLE8Y5XqN4PfMD2yYczTqPjA1DPq32l

2. https://www.facebook.com/profile/1223030691/search/?q=%E1%8A%A0%E1%89%BB%E1%88%9D%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%88%85%20

3. https://www.facebook.com/agellaw/posts/pfbid02geL3gQSjVeX9o391V4eRHaghYfBUaaWg3jnBXmHzqtNrpAqk6QwZQq4FaS6fV3oRl

  • 4. https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/pfbid02bRVKjAvbHeBTeBjfB9Y5VaKbZhJTDrSdF8dYqWcaQ69E7wspaCeibyMpkcUMMdSDl
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.