Breaking News
Home / Amharic / AAA (ቴዎድሮስ ትርፌ) ምን እየሰራ ነው?

AAA (ቴዎድሮስ ትርፌ) ምን እየሰራ ነው?

👉 ይድረስ #Amhara_Association_of_America

የሰሜን አሜሪካው የአማራ ማሕበር (AAA) ነኝ የሚለን ቡድን በትክክል ለአማራ ሕዝብ ህልውና ትግል የቆመ ከሆነ በአስቸኴይ ከአማራ ጠላቶች ጋር ተባብሮ ከስቴት ዲፓርትመንቱ ጋር የተፈራረመውን ጸረ አማራን ስምምነት ስህተት መሆኑን አውጆ አማራን ይቅርታ በመጠየቅ ከስምምነቱ መውጣቱን ያውጅልን!!!!

* ወንድወሰን ተክሉ*

የማብራሪያ ጋጋታህን አቁምና በአጭሩ 1ኛ- ጥፋት አጥፍቻለሁ ብለህ በይፋ ግሉጽ
2ኛ – እራሴን ከስምምነቱ አውጥቻለሁ ብለህ በአደባባይ ግለጽ – ከዚህ የዘለለ የፈጸምከውን ክህደት በቃላትና በማብራሪያ ጋጋታ ልታጸደው አትችልም❗❗❗❗

 

👉 ለጥቅምት 18 ለተጠራው የዌብነር ማብራሪያዊ ጥሪን ተከትሎ የተላለፈ ማሳሰቢያ

እራሱን ለአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም የሎቢ ስራን ለመስራት እንደፈጠረ የሚነግረን የቴውድሮስ ትርፌ AAA ሲቪክ ድርጅት ሰሞኑን እጅ ከፍንጅ የተያዘበትን ክህደታዊ የሆነ ጸረ አማራ ስራን ከስቴት ዲፓርትመንቱ ጋር ሆኖ በአማራ ስም መፈጸሙን አይተናል።

በአጭሩ AAA የፈጸመውን ወንጀል በነጥብ ለማስቀመጥ፦

📌 1ኛ – ድርጅቱ በአንድም የአማራ ሕዝብ ሳይወክል በአማራ ስም ከስቴት ዲፓርትመንቱ ጋር ተፈራርሟል

📌 2ኛ – ድርጅቱ በአንድም የአማራ ሕዝብ ሳይወከል በሕዝባችን ስም ሆኖ ከጸረ አማራ ሃይሎች እንደነ ኤፓክ ኦነግ ትህነግ . . ወዘተ የኮንፌዴራሊስት ሃይሎች ከሚባሉት 17 ድርጅቶች ጋር ሆኖ አማራን ክዶ ከጠላት ጋር ወግኖ ተፈራርሟል

📌 3ኛ – የአማራ ሕዝብ የህልውና ጦርነት ላይ እያለ AAA ግን አንድም አማራ ሳይወክለው እራሱን የአማራ ሕዝብ ጥቅም አስጠባቂ በማለት ከስቴት ዲፓርትመንቱ ጋር በተፈራረመው ባለ 7 ነጥብ ስምምነት መሰረት የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግልና የህልውናን አደጋን አሽቀንጥሮ በመቅበር የህልውናውን ትግል በአንድ ተራ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚዲያ ነጻነት ይከበርና መሰል ተራ ጥያቄዎች ደረጃ አውርዶ ክህደት ፈጽሟል።

📌 4ኛ – AAA የሚባል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ንብረት (የቴድሮስ ትርፌ) በአንድም የአማራ ሕዝብ ሳይወከል የአማራን ትግል በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ስር ይመለሳል ብሎ የሕባችን የህልውና ትግል ለስርዓት ለውጥ ሳይሆን ለቅንጥብጣቢ ጥያቄዎች የሚደረግ ትግል ነው በማለት የመፈራረምን ወንጀል ፈጽሟል

📌 5ኛ – AAA እራሱን የሎቢ ስራ የሚሰራ ተራ የሲቪክ አድቮኬሲ ድርጅት መሆኑን ከተመሰረተበት ቻርተር ውጪ በመውጣት በፖለቲካ ፓርቲዎች ሊሰራና ሊፈጸም የሚገባን ስራን ያለአንዳች ጥቆማ ያለአንዳች ምርጫና ውክልና እብሪት በወለደው ምን ታመጣላችሁ ስሜት የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ በአማራ ስም ከስቴት ዲፓርትመንቱ ጋር የመፈራረምን ወንጀል ፈጽሟል

📌 6ኛ – የአማራን ሕዝብ ተቃውሞና ውግዘትን ተቀብሎ አጥፍቻለሁ ከማለት ማንም ሳይመርጠውና ማንም ሳይወክለው እራሱን የአማራ ተወካይ ጠበቃ በማድረግ በአቅሙ እኔ አውቅላችኋለሁ – እኔ አውቄ የተፈራረምኩትን ከመቀበል ውጪ ልትቃወሙት ልትተቹት አትችሉም አይገባምም በማለት በሕዝባችን እድል እጣፈንታ ላይ እራሱን ብቸኛ አዋቂ አድርጎ አቅርቧል።

📌 7ኛ – ቡድኑ ማለትም በቴውድሮስ ትርፌ የሚመራው AAA በአማራ የህልውና ትግል አደረጃጀት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ዳያስፖራ ቁጭ ብሎ የሀገር ቤቱን ትግል ተቆጣጥሬ እሾፍራለሁ በማለት ፋኖዎችን በሚከፋፍል ሁኔታ ከባልደረባው ጌታቸው መኮንን በየነ እና ከወሰን ይጥና ጋር በመሆን ትልቅ ተግዳሮትና መሰናክልን ለመፍጠር እየታተረ ያለ የኢጎኢስት ስብስብ ነው።

ስለሆነም ይህንን ተግባሩን ተቀባይነት ለማሰጠት ከዚህ በፊት በአዲስ ድምጽ ሚዲያ ቀርቦ ማብራሪ የሰጠ ቢሆንም ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ እነ ማይክ ሀመር የሚሳተፉበትን የዌብነር ውይይት በማዘጋጀት በጥቅምት 18 እንገናኝ ብሎ ማስታወቂያ ማውጣቱ የዚህን ቡድን ዓይን ያወጣ የለየለት ጸረ አማራ የዲያስፖራው ትንሹ ብዓዴን/አብን መሆኑን ከማረጋገጥ የዘለለ ምንም ፋይዳ የሌለው መገለባበጥ መሆኑን ሁላችንም ልናውቅ ይገባል።

♦️ የመፍትሔ ሀሳብ ፦

AAA በእስቸኴይ ጥፋት መፈጸሙን አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ እራሱን ከተፈራረመው ጸረ አማራ ቡድን መውጣቱን ያውጅ❗❗❗

ቡድኑ የመፍትሔ ሀሳቦችን ተቀብሎ እራሱን ማስተካከል የሚፈልግ ከሆነ በአጭሩ AAA አደባባይ ወጥቶ We did a mistake አጥፍተናል። ተሳስተናል። ብሎ መጀመሪያ ጥፋቱን አምኖ መግለጽ አለበት።

ቀጥሎም እኛ ለአማራ ሕዝብ ጥቅም የምንታገልና ለሕዝባችን ሁለንተናዊ ጥቅም የምንሰራ ድርጅት ነን። ይህ ማለት አማራው ያልወደደውን፣ አማራው ያልፈለገውን እና አማራው ይጎዳኛል ያለውን ነገርብ ሁሉ እኛም የማንወደው የማንፈልገው ስለሆነ እራሳችንን ከዚህ ስምምነት አውጥተናል። በማለት በይፋ ማወጅና ማስታወቅ አለበት።

ወደ ሌላ የሎቢ ስራ ከመሰማራቱ በፊት፣ በአማራ ስም በየትኛውም መድረክ እራሱን ከማቅረቡ በፊት መቅደም ያለበት ስራ AAA ያጠፋውን ጥፋት አውቆና አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ ተፈራረምኩት ካለው ከስቴት ዲፓርትመንቱ ስምምነት መውጣቱን ማወጅ የግዴታው ተግባር ነው።

 

ቡድኑ የአማራን ሕዝብ ከማይመስሉ እና ብሎም ከአማራ ሕዝብ ጠላቶች ከሆኑት ጋር በመሰብሰቡ ላደረሰው ፖለቲካዊና ሞራላዊ ጥፋት ሕዝባችንን በይፋ ይቅርታ እንጠይቃለን ብሎ ይህንን ቻፕተር በመዝጋት ወደ አዲስ ቻፕተር ከመሸጋገር ይልቅ ይባስ ብሎ እኛ የሰራነው ትክክል ነው። ዛሬም ነገም የምንሰራው ዓላማችን ነው በሚል እብሪት የወለደው ንቀታዊ አቌም የተፈራረመውን ጸረ አማራን ፊርማ እነ ማይክ ሀመርን አምጥቶ በማስለፍለፍ ትክክል መሰራቱን የሚገልጽ ከሆነ ይህንን ጸረ አማራን ስብስብ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከአማራ ጉዳይ ላይ ሙሉ በሙሉ ተጠራርጎ እንዲወጣ መሰራት ያለበትን ስራ ጠንክረንና በርትተን እንሰራለን።

በቃ። ይህ ነው የሚሆነው❗❗❗

ከአማራ ጠላቶች ጋር ልክ እንደ አብን እና ብዓዴን ከአማራ ሕዝብ ጀርባ የሚዶልት የዳያስፖራው ብዓዴንና አብን አያስፈልገንም❗❗❗

AAA ይህንን ካልፈጸመ የዳያስፖራው ብዓዴንና አብን ነው❗❗❗❗

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.