Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫና የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ !

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫና የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ !

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂድ ነው።
#Ethiopia : የንቅናቄው ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰለፍ ጠራ መጥራቱን አስታወቋል።የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የአማራን ሕዝብ እየገጠሙት ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየሁ ነው ብሏል።
በውይይቱ በዋናነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች መዋቅራዊና ሕግ ሰራሽ መገለሎችን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ “በአማራ ክልል” በሚገኙ ከተሞች በመጭው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም በአዲስ አበባ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን ገልጿል።የሰላማዊ ሰልፉን ዝርዝር አፈፃፀሙ በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግም ንቅናቄው በመግለጫው አስታውቋል።
 
በመተከል፣ በኦሮሞና በደቡብ «ክልል»፣ በየቦታው የሚፈሰው የአማራ ደም የኔም ደም ነው!
*****
የሻሸመኔውን፣ የአርሲውን፣ የሀረርጌውን፣ የባሌ የዶዶላውን፣ የመተከሉን፣ የጉራ ፈርዳውን የአማራ ዘር እልቂትና ጭፍጨፋ በተመለከተ እያንዳንዱ አማራ የፓለቲካ አመለካከትና አስተሳሰብ፣ የመኖሪያ አካባቢ፣ የእምነት ልዩነት ሳይኖር በአገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች በሚደረጉ ሰልፎች በመሳተፍ በአማራዊ አንድነት ድምፃችን ለአለም ማሰማት አለብን። መንግስትንም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የአማራን ህዝብ የመጠበቅ ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እናስጠነቅቃለን።
አጋጣሚውን በመጠቀምም በጎርፍ ለተጎዱ፣ በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው ለወደመባቸው፣ ከትምህርታቸው ለተፈናቀሉ አማራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ታግተው ደብዛቸው ላልተገኙ የአማራ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምጽ እንሆናቸዋለን።
ለጣና፣ ለላሊበላ፣ ለጎንደር አብያተ መንግስታት፣ ለአንኮበርና እንጦጦ ቤተ መንግስታትና ቅርሶች መንግስት የገባውን የጥገናና ጥበቃ እንዲያደርግ ድምፃችን እናሰማለን።
በዚህ ሰልፍ ለመገኘት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። አማራ ሆኖ በዚህ ሰልፍ የማይገኝ አማራ ይኖራል ብየ አልጠብቅም። ምንም አይነት ምክንያትም ሆነ ሰበብ በአማራ ላይ በየቦታው ለተፈፀመው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ለማድረግ ድምፃችን ከማሰማት አይከለክለንም።
የሚፈሰው የአማራ ደም የኔም ደም ነው!
 

One comment

  1. Ethiopians open a foreign currency bank account. The National Central Bank of Ethiopia encourages Foreign Currency Accounts.

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.