Breaking News
Home / News / ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ ሥራ ጀመረ ::

ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ ሥራ ጀመረ ::

ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ መጀመሩን የትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተቋርጦ የነበረው የሀገር አቋራጭ፤ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ መጀመሩን የትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሲባል የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ያስታወሰው ባለስልጣኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ግን የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ስድስቱም መናኸሪያዎች አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ገልጿል።

ስለሆነም የሀገር አቋራጭ፣ የአነስተኛና መለስተኛ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ትራንስፖርተሮች ተሸከርካሪዎቻቸው አገልግሎት ለሚሰጡት ህብረተሰብ አስፈላጊና ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበውቅባቸው ማሳሰቡን ከትራስንፖርት ሚኒቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብ መሰረትም የሀገር አቋራጭ፤ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከተሳፋሪ የመጫን አቅማቸው በ50 በመቶ ቀንሰው የሚጭኑ ይሆናል።

በተጨማሪም ማህበራት ሰራተኞች፣ ለአሽከርካሪዎች ፣ ለገንዘብ ተቀባዬች እና ለረዳቶች ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ ማስክ፣ እንዲሁም ሳኒታይዘር (አልኮል) ማቅረብ እንደሚገባም አስታውቋል።

የጫኝና አዉራጅ ማህበራት እና የስነስርዓት አስከባሪ አደረጃጀቶች ለጫኝና አውራጅ እና ለስነ-ሥርዓት አስከባሪዎች ጓንት፤ የአፍና አፍንጫ ማስክ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ነው ባለስልጣኑ የገለፀው።

አሽከርካሪዎችም ተሸከርካሪዎቻቸውን ሥምሪት ከመውሰዳቸው በፊት ከመናሀሪያዉ አስተዳደር ጋር በመሆን የኬሚካል ርጭት ማካሄድ እንደሚገባም አብራርቷል።

በአጠቃላይ የኮረና ወረርሽን ለመከላከል ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ትውልድን እና ሀገርን የማዳን ጥሪ መሆኑን በመግለፅ፤ ይህንን ያላሟላ ትራንስፖርተር ስምሪት ለመውሰድ የሚቸገር መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

Check Also

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት ሐሰተኛ መረጃ !

አማኑኤል ይልቃል የሥራ ድርሻ,ቢቢሲ አማርኛ ዘገባው ከናይሮቢ ከ 8 ሰአት በፊት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም …

ኢትዮጵያዉያን የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ፈንቅለው ገብተው ተቃውሞ አሰሙ !

Ethiopians protest against Abiy Ahmed in Geneva Switzerland!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.