ለአማራ ህዝብ ደህንነት ዘብ መቆም ካልቻልን እኛ የአማራ ልጆች አይደለንም፤ መንግስት ችግሩን በውይይት ይፍታ”
(የአማራ ልዩ ሃይል አባላት)
~~
ዛሬ በህዝባዊ ሰራዊቱ ፋኖ ላይ ግልፅ ጦርነት ከመታወጁ በፊት ዘመቻው የአማራ ልዩ ሃይል ላይ ነበር። የአማራ ልዩ ሃይል ላይ ያልዘመተ ፖለቲከኛ አልነበረም። ከጃዋር መሃመድ እስከ ኢዜማው ብርሃኑ ነጋ፣ ከህወሃት እስከ ቅማንት ኮሚቴ እስከ አብይ አህመድ ድረስ አንድ ላይ በተመሳሳይ ወቅት #ይፍረስ ብለው ነበር።
የሁሉም ፍላጎት የነበረው የአማራ ህዝብ ራሱን የሚጠብቅበት የራሱ ሃይል እንዳይኖረው ማድረግ እና ማንም እየተነሳ እንዲያተራምሰው ማድረግ ነበር። በርግጥ የአማራ ልዩ ሃይልን አፍርሰናል ብለው ነው የሚያምኑት፤ አለ የተባለው ልዩ ሃይልም ከኦሮሞ ልዩ ሃይልና ከትግራይ ልዩ ሃይል አንፃር በጣም ትንሽ እንዲሆን መደረጉን አይካድም፤ ባልተነቃበት መንገድ የአማራ ልዩ ሃይል እንዲፈርስ ለማድረግ ተሞክሯል። የአማራ ልዩ ሃይልም ፈርሷል ተብሎ ተደምድሟል።
አሁን አለ ብለው ያሰቡትና ልባቸውን የሚያርደው #ፋኖ የተሰኘው ህዝባዊ ሃይል ነው። የፋኖን መራራ ክንድ በጎንደር፣ በከሚሴና በአጣዬ የቀመሰው ፀረ አማራ ሃይል አማራን እስከ ወዳኛው አዳክሞ ለመግዛት ፋኖ ላይ መዝመትንና ፋኖን መደምሰስን ብቸኛ መንገዱ አድርጎ ወስዶታል፤ የአማራው ወጣት አልገባውም እንጂ መላው የአማራ ጠላት ፋኖ፣ መላው የአማራ ልዩ ሃይል ፋኖ፣ መላው የአማራ ገበሬ ፋኖ፣ መላው የአማራ ሚሊሻ ፋኖ ነው። ወገኑን ለመጠበቅ የማይቆም የአማራ ልጅ የለም።
አከተመ!
ይህን የተረዳው የአማራ ልዩ ሃይል የፌደራሉ መንግስት ከፋኖ ጋር አለብኝ ያለውን ችግር በድርድር የማይፈታ እና ወደ ጦርነት የሚገባ ከሆነ ወገናችንን ለመጠበቅ “እኛም ፋኖ ነን” ብሏል።
አዎ! ሁሉም አማራ ፋኖ ነው!
አለባቸው ግርማ
#ክተት!