Breaking News
Home / Amharic / ከጣሊያን አገር የተላከ መልዕክት

ከጣሊያን አገር የተላከ መልዕክት

እኛ በጣሊያን አገር ሚላን ነው የምንኖረው፡፡ አሁን ላይ በሚላን ህይወት ምን እንደሚመስል ልገልጽላችሁና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ሆኜ እናንተ እኛ ከሰራነው ስህተትና በውጤቱም ከገባንበት አጣብቂኝ ህይወት የምትማሩት ቁም ነገር አለ ብየ ነው ይህንን የምጽፍላችሁ፡፡
አሁን ላይ ሁላችንም በማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ፖሊሶች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ሲሆን ማንኛውንም ከቤት ውጪ ሲዘዋወር ያገኙትን ሁሉ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፡፡ ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡- የንግድ ሱቆች፣ ሞሎች፣ የሽያጭ እቃ ማዕከሎች ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡፡ የአለም ፍጻሜ ነው የሚመስለው! ለኑሮ ተስማሚና ጤና ማህይወት ታስተናግድ የነበረችው ጣልያን ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሰዓታትና ቅጽበት ከጨለማ ውጪ ምንም የሌለባት የተወረረች ከተማ መስላ ነው የምትታየው፡፡ እኔ ራሴ ተመልሼ በዚህች መሬት ላይ እንደ ቀድሞው በህይወት እኖራለሁ የሚለው ተስፋየ ጨልሟል፡፡ እዚህ አገር ህዝቡ ግራ ገብቶታል፣ በመከፋት አንገቱን አቀርቅሯል፤ ተስፋ በመቁረጥም ይህ ሁሉ መዓት እንዴት እንደታዘዘበትና ይህም በቅዠት እንጂ በውን የማይመስል የጭንቅ ወቅት መቼ እንደሚያበቃ ግራ ገብቶት በየቤቱ ተዘግቷል፡፡

ይህ ክፉ ቀን ግን የጀመረው ዝም ብሎ አልነበረም ! አንድ ትልቅ ስህተት ነበር ! ገና የኮሮና ቫይረስ (COVID – 19) አገራችን ጣሊያን እንደገባ በይፋ በተነገረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ህዝቡ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ አኗኗሩን እንደተለመደው ቀጠለ፣ ህዝቡ ወደ ስራ መሄዱን አልተወም፣ ወደ መዝናኛ ቦታዎች እንደ ተለመደው በጋራ ይሄዳል እንደእረፍት ጊዜ ከጓደኞቹ ከሌሎቹም ጋር እንደተለመደው በብዙ ቁጥር መንጎዱን አላቆመም፡፡ ሁሉም መጨረሻውን ሳያስብ ትክክል ያልሆነ የኑሮ ዘይቤውን ቀጠለ፤ እናንተም እንደዚህ እየሆናችሁ ነው !
ልለምናችሁ ! እየቀለድኩ አይደለም፤ እባካችሁ ተጠንቀቁ ! የምትወዷቸውን ሁሉ፣ ቤተሰቦቻችሁን፣ ወላጆቻችሁን፤ አያቶቻችሁን ከዚህ መቅሰፍት ጠብቁ ! ይህ በሽታ በተለይ ለነሱ እጅግ አደገኛ ነው፡፡


እዚህ በቫይረሱ ምክንያት በየእለቱ የ200 ሰዎች ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ሚላን ውስጥ ያለመድሀኒት ስለማይረባ አይደለም፤ ከመድሀኒት ጋር ባለ ብቃት ሚላን ከዓለም ከፊት ተርታ ከሚሰለፉት አንዷ ነች፡፡ ለበርካቶች በየእለቱ ሞት ምክንያት እየሆነ ያለው ደግሞ ለእያንዳንዱ ለቅርብ ክትትል የሚበቃ በቂ ቦታ ባ ለመኖሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብታምኑም ባታምኑም ሀኪሞች ማንን እናትርፍ ሳይሆን ማን ቢሞት ብዙዎችን መታደግ ይቻላል የሚል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል፡፡ይህ ሁሉ የሆነው ቫይረሱ ወደ ዚህ ቦታ መግባቱ በተነገረበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በህዝቡ ዘንድ የነበረው ሞኝነትና ችግሩን ተገንዝቦ ፈጥኖ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ህይወት በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል በማድረጉ ነው፡፡
እባካችሁ ከእኛ ስህተት ተማሩ! የእኛ አገር ትንሽ የህዝብ ቁጥር ያለበት ነው፤ እናም በአገር ደረጃ እጅግ የከፋ ፍጻሜ እንዳይኖረን ያሰጋል፡፡ እባካችሁ በደንብ አዳምጡኝ፡-


• ህዝብ በብዛት ባለባቸው ስፍራዎች አትሂዱ፤
• ብዙ ህዝብ በሚጋራቸው ቦታዎች ላይ ላለመመገብ ሞክሩ፤
• በዚህ ወቅት ብዙ ጊዜ በቤታችሁ ተቀመጡ፤
• ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጡ መመሪያዎችን አዳምጡ፤ አዳምጣችሁም ተግብሩ (እንደቀልድ አትዩአቸው !)
• ከማንኛውም ሰው ጋር ስታወሩ ከአንድ ሜትር በላይ በሆነ ርቀት ላይ ሆናችሁ አውሩ፣ አትጠጋጉ፣ አትተቃቀፉ፣ አትጨባበጡ፤
• ማድረግ ያለባችሁን የመከላከያ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ከሌሎች ስህተትም ተማሩ፤
• በሽታ የመከላከል አቅማችሁ እንዳይዳከም‘ቫይታሚን “ሲ” ተጠቀሙ
• የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመከላከልና ስርጪቱን ለመቆጣጠር ለሚያደርጉት ጥረት አጋዥ ሁኑ
ጣሊያን ውስጥ መላ አገሪቱ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ እንዳለች ቁጠሩት፤ 60 ሚሊዮን ህዝቧ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው እነደማለት !ታዲያ ህዝቡ በመጀመሪያ ላይ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን አዳምጦ ተግባር ላይ ቢያውል ኖሮ ይህ ሁሉ መጥፎ ቀን እንዳይመጣ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡
እናም እባካችሁ ሳይመሽ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችሁንና የምትወዷቸውን ሁሉ ጠብቁ !!!
መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ
ከአንድ ጣሊያናዊ/ት ወዳጅ (Jsca)


ይህ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንቂያ ደወል ነውና እንጠቀምበት !
ይህንን መልእክት ለሚወዱት ወይም ለሚቀርቡት ሊሠማኝና ለሌላም ወንድምና እህቶች ሊያስተላልፍ ይችላል ለምትሉት 20 ሰው አስተላልፉ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.