Breaking News
Home / Amharic / ወደ ሀገራችን መልሱን

ወደ ሀገራችን መልሱን

  • የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የስነ ልቦና ቀውስና ችግር የሚሰማን ከሆነ ይህም ችግር ችግራችን ነው። ……….. ወደ ሐገራችን መልሱን !!!

    ኮሮና ቫይረስ በተቀሰቀሰባት የቻይናዋ ውሃን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምፃችን ይሰማ እያሉ ነው።በቻይና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማሕበር በማሕበራዊ ሚድያዎች የአስወጡን ቅስቀሳ ጀምረዋል። ተማሪዎቹ መንግሥት ወደ ሃገራቸው እንዲመልሳቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው።በውሃን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 300 ገደማ እንደሆነ ይገመታል።አብዛኛዎቹ በስጋት ውስጥ እንዳሉና ከተማዋም ፀጥታ የዋጣት እንደሆነች ይናገራሉ።

    ተማሪዎቹ የምግብና መጠጥ ውሃ እጥረትም አጋጥሞናል ይላሉ።በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለፈው ሳምንት ጉዳዩን በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገረው ተማሪዎቹን ማስወጣት ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ምግብና መጠጥ እየቀረበላቸው ነው።ተማሪዎቹ ግን በእንቅስቃሴ አልባዋ ከተማ መኖር ለሥነ-ልቡና ቀውስ እያጋለጣቸውም እንደሆነ ይናገራሉ። #MinilikSalsawi

Check Also

ኢትዮጵያዉያን የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ፈንቅለው ገብተው ተቃውሞ አሰሙ !

Ethiopians protest against Abiy Ahmed in Geneva Switzerland!

መንገዱ በጀግናው ስም ተሰይሟል !

እንባየም ሳላስበዉ ይፈሳል። ብቻ እንደዛሬ ሁኘ አላዉቅም። እግዚአብሔር አምላክ ልቤን አበረታዉ።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.