Breaking News
Home / Amharic / ሰበር ዜና – የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ማስፈራሪያ አዘል ጫና እየተደረገባቸው ነው::

ሰበር ዜና – የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ማስፈራሪያ አዘል ጫና እየተደረገባቸው ነው::

~~~~~~
የዋሽንግተኑ የሕዳሴ ግድብ ድርድር ተራዘመ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ማስፈራሪያ አዘል ጫና እየተደረገባቸው ነው::
፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፬፬፬፬፬፬፬፬፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲
ባለፉት ሁለት ቀናት በአሜሪካ ዋሽንግተን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሀ አሞላልና የድርቅ ማካካሻን በሚወስነው መመሪያ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ኢትዮጵያ ፣ ግብጽና ሱዳን በውጭ ጉዳይና በውሀ ሚኒስትሮቻቸው እንዲሁም በቴክኒክ ባለሙያዎቻቸው አማካይነት ሲመክሩ ቢቆዩም በሁለቱ ቀናት ውይይት ከስምምነት መድረስ አልቻሉም።

አሜሪካና የአለም ባንክ ‘ በታዛቢነት ‘ በተገኙበት የሁለት ቀኑ የዋሽንግተን ስብሰባ ግብጽ ከአሜሪካና አለም ባንክ ጋር በመሆን የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተከታታይ አመታት ድርቅ ቢከሰት እንዴት ውሀ ይልቀቅ በሚል ለኢትዮጵያ ያቀረቡት እቅድ ያላስማማቸው ጉዳይ ነው።

በግብጽ ፣ በአሜሪካና አለም ባንክ በኩል ለተከታታይ አመታት ድርቅ ቢከሰት ውሀ እንዴት መለቀቅ አለበት በሚል ያቀረቧቸው ሁለት አማራጮች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚነካና ግብጽን የውሀው አዛዥ የማድረግ አቅም ያለው መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ መዘገቧ ይታወሳል።

ሆኖም ዛሬ በደረሰን መረጃም የሁለት ቀኑ ውይይት የሚታሰበውን የፊርማ ስምምነት ማሳካት ስላልቻል የዋሽንግተኑ ስብሰባ የሶስቱ ሀገራት ተወካዮች ሳይበተኑ እንደገና በዚያው በዋሽንግተን ይቀጥል ተብሏል። ውይይቱ የሚቀጥለው ለዛሬ ብቻ ነው ወይስ ለቀጣይ ቀናት ግን የታወቀ ነገር የለም።

ዋዜማ ራዲዮ ከዋሽንግተን የወጡ መረጃዎችን ያገኘች ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ የቀረበላትን የውሀ አያያዝና የድርቅ ማካካሻ ውል እንድትፈርም በተደራዳሪዎች ላይ ማስፈራሪያ አዘል ጫና እየደረሰባቸው ነው። ስምምነቱ ላይ ኢትዮጵያ ካልፈረመች የሚከተሉ ተጽእኖዎች (Consquences) ሊኖሩ እንደሚችሉ በግብጽ ባለስልጣናትና በአሜሪካና አለም ባንክ ለኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች እየተነገራቸው መሆኑንም ነው የሰማነው።

ሆኖም ከኢትዮጵያ ልኡካን መካከል የተወሰኑት ስብሰባው ተቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ እንመለስ የሚሉ እንዳሉም ነው የተነገረው። ውል መፈረም ካለበትም አሁን እየተፈጠረ ባለው ጫና ውስጥ ተኩኖ ሳይሆን እንዲሁም አለማቀፍ ህጎችም ስለማይፈቅዱ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ሰፊ ምክክር በማድረግ መሆን እንደሚገባው ከልኡክ ቡድኑ ውስጥ የተወሰኑት አባላት አቋም ሆኗል። [ዋዜማ ራዲዮ]

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.