በስልጣን መቆየታችን እንደ ክህደት ያስቆጥርብናል!
የወንጀለኞች ድርጊት ተደጋግሞ ቀይ መስመሩን አልፏል። አሁን ያለንበት ወቅት ጊዜ የሚሰጠን አይደለም፣ እስከዛሬ በሩዋንዳ ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያም በእንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ነገር ተከስቶ አያውቅም ብል ማጋነን አይደለም። ወንጀሉ እንዲፈፀም ምክንያት ከሆነው ሰው እስከ ግብረ አበሮቹና ፈፃሚዎቹ በአስቸኳይ ለፍርድ ካልቀረቡ የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ አስቀያሚ ይሆናል።እኛም መሪ ነን ለማለት አንችልም
ስለሆነም መንግስታችን ቁርጠኛ አቋም ይዞ በህዝባችን የደረሰውን አሰቃቂ ድርጊት በአስቸኳይ ለፍትህ አቅርቦ የማያዳግም እርምጃ ካልወሰደ በስልጣን መቆየታችን እንደ ክህደት ስለሚያስቆጥርብን በፈቃዳችን ስራዉን ሃላፊነቴን ለመልቀቅ እገደዳለሁ።
የኢፊዲሪ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሳህለወርቅ።