ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን የሚያገናኘው መንገድ ቄሮዎች ነን በሚሉ ወጣቶች ሼኖ አካባቢ በመዘጋቱ መንገደኞች እየተጉላሉ መሆናቸው ታውቋል።
ዛሬ ከቀኑ 10:00 ገደማ ጀምሮ መንገዱ መዘጋቱን ተጓዦች የገለፁ ሲሆን፣ በስፍራው የምትገኘው የአሥራት ዘጋቢም ይህንኑ አረጋግጣለች። መንገዱን የዘጉት ወጣቶችን የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በዝምታ እየተመለከታቸው እንደሆነም ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከተጓዦች መካከል ለግሸን ደብረ ከርቤ ንግስ በዓል ቆይተው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት በከፍተኛ ቁጥር ይገኙበታል። ቄሮ ነን የሚሉ አካላት ኢሬቻን አክብረው ወደ ከሚሴ የሚመለሱ ግለሰቦች ደብረ ብርሃን ላይ ታስረዋል፣ እነሱ ካልተፈቱ መንገዱን አንከፍትም ሲሉ መደመጣቸው ተሰምቷል። አሥራት ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው፣ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያደርስ ይሆናል።
በሌላ በኩል፣ ኤፌሶን/አጣዬ ትናንት የጀመረው ተኩስ ቀጥሎ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ማድረሱን ከስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች ጠቁመዋል።
አሥራት ሁኔታውን እየተከታተለ መረጃዎችን የሚያደርስ ይሆናል።