Breaking News
Home / Amharic / 50 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ህገ-መንግስቴ ነው ብሎ የማይቀበለው ሰነድ መሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት።

50 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ህገ-መንግስቴ ነው ብሎ የማይቀበለው ሰነድ መሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት።

50 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ህገ-መንግስቴ ነው ብሎ የማይቀበለው ሰነድ እንዲሁም ሲወጠን ጀምሮ አማራን ለመጉዳትና ለማጥፋት ተጠንቶ የተዘጋጀው የትህነግ-ኦነግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ በስፋት መሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት።

ምንም አይነት “የተቀደሰ” አመክንዮ ቢቀርብ እንኳ አማራን ለመቅበር የተዘጋጀን ፀረ-አማራ ሰነድ ላለማሻሻል አሳማኝ ምክንያት አይሆንም። የአማራ ህዝብ በጨዋነት ስለታገሰ ብቻ ይህን የጫካ ህግ ወይም ህገ አራዊት ሁለንተናዊ ቅቡልነት እንዳለው ለማስመሰል የሚሞከርበት መንገድ ከነውረኛነትና አድሎአዊነት የጸዳ አይሆንም።

አማራን የመገፋትና የመገለል ስሜት እንዲሰማው የሚያድርግ ሰነድ እንዳይሻሻል መፈለግ ቀላሉ የፀረ አማራነት መለያ ሆኖ ማገልገል አለበት። ባለፋት 25 ዓመታት ለተፈጠሩ የአማራ ህዝብ ውስብስብ ችግሮች ሁሉ ዋነኛ ምንጫቸው ይህ ፀረ አማራ ሰነድ ነው። አማራ ይሁንታውን ያልሰጠውን ሰነድ ለመቀየር ቢቻል ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር በምክክር ቢሆን ይመረጣል። ካልሆነ ግን የአማራን ፍላጎቶች የሚያካትት ህገ መንግስት አማራ በራሱ መንገድ ይሰራል። የመጨረሻ እጣ-ፈንታችን የሚጻፈው በገዛ እጃችን ነው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.